0 0
Read Time:51 Second

በኬንያ መዲና ናይሮቢ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ከወራት በፊት ታፍኖ የተወሰደው አቶ ሳምሶን ተክለሚካኤል የት እንዳለ እስካሁን ድረስ አለመታወቁን በመቃወም ሰልፍ አካሂደዋል።

ከሦስት ወራት በፊት ከናይሮቢ ጎዳና ላይ ባልታወቁ ሰዎች ከመኪናው እንዲወርድ ተደርጎ ከተወሰደ በኋላ እስካሁን ያለበት ያልታወቀው በንግድ ሥራ የሚተዳደረው አቶ ሳምሶን ጉዳይ ያሳሰባቸው ቤተሰቦቹ፣ ጓደኞቹ እንዲሁም ሌሎችም በናይኖቢ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ማኅበረሰብ አባላት ናቸው ሰልፉን ያካሄዱት።

– ፍትሕ ለሳሚ፣

-/ሳሚ የት ነው?

– ባለቤቴ ሳሚ የት ነው?

– ጓደኛዬ ሳሚ የት ነው?

– አጎቴ ሳሚ የት ነው?’ የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን ይዘው ኢትዮጵያውያኑ ሰልፍ ወጥተዋል።

የአቶ ሳምሶን ባለቤት ወ/ሮ ሚለን ሃለፎምን ጨምሮ የሃይማኖት አባቶች እና ወጣቶች በናይሮቢ አደባባይ ወጥተው ድምጻቸውን አሰምተዋል።

አቶ ሳምሶን በዚህ ዓመት ኅዳር መጀመሪያ ላይ ነበር በናይሮቢ ከተማ ማንነታቸው ባልታወቁ ሰዎች ከመንገድ ላይ በኃይል ከተወሰደ በኋላ እስካሁን ድረስ ያለበት አልታወቀም።

ከሳምንታት በፊት ለኬንያ ሚዲያዎች ቃላቸውን የሰጡት በኬንያ የኢትዬያጵያ አምባሳደር መለስ አለም ፥ “የኬንያ መንግሥት እና የሕግ አካላት ሳምሶን የት እንዳለ እንዲያሳውቁን ጠይቀናል” ማለታቸው አይዘነጋም።

አቶ ሳምሶን ታፍኖ የተወሰደ ሰሞን የኬንያ ፖሊስ ጉዳዩን በቅርበት እየተከታተለው እንደሆነ የገለጸ ቢሆንም፤ እስከ ዛሬ ግን ከኬንያ ፖሊስ ሆነ ከኬንያ መንግሥት በኩል የተሰጠ ምላሽ የለም።

መረጃው የቢቢሲ ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *