የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ አዲስ አበባ ደረሱ።

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌይ ላቭሮቭ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት አዲስ አበባ ገብተዋል። ሰርጌይ ላቭሮቭ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም ሌሎች የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የሩሲያው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሚኖራቸው ቆይታ በሩሲያ እና ኢትዮጵያ መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ሌሎች ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ ከኢትዮጵያ መንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢቢሲ ዘግቧል፡፡

You may also like...

Leave a Reply

Your email address will not be published.