0 0
Read Time:29 Second

የትግራይ ክልል ምክር ቤት የፌዴሬሽን ምክር ቤት ለጠራው አስቸኳይ ስብሰባ አጀንዳው ቀድሞ ካልደረሰው ክልሉን የሚወክሉ አባላት በስብሰባው እንደማይሳተፉ አስታወቀ።

የክልሉ ምክር ቤት ዛሬ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት በላከው ደብዳቤ እንዳለው ምክር ቤቱ ለነሐሴ 30/2012 ዓ/ም የጠራው ስብሰባው በምክር ቤት አሰራር የአባላት ስነ-ምግባር ደንብ መሰረት አጀንዳው አስቀድሞ ለአባላት መድረስ ነበረበት።

ነገር ግን <<የፌዴሬሽን ምክር ቤት አጀንዳውን ቀድሞ አልላከም ፤ እንዲልክ በስልክ በተደጋጋሚ ቢጠየቅም ፈቃደኛ አልሆነም>> ብሏል።

በመሆኑም <<ምክር ቤቱ ከስብሰባው አስቀድሞ አጀንዳውን የማይልክ ከሆነ ክልሉን የሚወክሉ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባላት አጀንዳውን ቀድመው ባላወቁት እና ዝግጅት ባላደረጉበት ስብሰባ ላይ መሳተፍ አይችሉም>> ብሏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *