1 0
Read Time:54 Second

ፍቅ ር እስከመቃብር
┈┈•✦•┈┈
ደራሲ እና ዲፕሎማት ሀዲስ ዓለማየሁ ለመጀመሪያ ጊዜ በሥራ ምክንያት ከኢትዮጵያ ውጭ የኖሩት ኢየሩሳሌም ነበር፡፡ በኢየሩሳሌም የኢትዮጵያ ቆንስል ሆነው ለሁለት ዓመታት አገልግለዋል፡፡ ከባለቤታቸው ወይዘሮ ክበበፀሐይ በላይ ጋር ተዋውቀው ለጋብቻ የበቁትም በዚህ ወቅት ነበር፡፡በጊዜው ወይዘሮ ክበበፀሐይ ከአያታቸው ጋር ኢየሩሳሌም ይኖሩ ነበር፡፡

ከ15 ዓመታት የፍቅርና የትዳር ሕይወት በኋላ ወይዘሮ ክበበፀሐይ አሜሪካ፣ ኒውዮርክ በህክምና ላይ እንዳሉ አረፉ፡፡ ሀዲስ ዓለማየሁ ከዚህ በኋላ እስከ ሕይወት ፍጻሜያቸው ድረስ ሌላ ሚስት አላገቡም፡፡ የአብራካቸውን ክፋይም አላዩም። ከባለቤታቸው ሞት በኋላ ሌላ ሚስት ለምን እንዳላገቡ በአንድ ወቅት ተጠይቀው ነበር፡፡

በሰጡትም መልስ በጣታቸው ላይ ያለውንና ከባለቤታቸው ሞት በኋላ ያላወለቁትን የጋብቻ ቀለበት እያሳዩ «ይህን ቀለበት ያሰረችልኝ ክበበፀሐይ ነች፡፡ እኔም ለእሷ አስሬያለሁ፡፡ እሷ ድንገት አረፈች፡፡ … ቀለበቱን አልፈታችውም፡፡ ሳትፈታው አረፈች፡፡ ስለዚህ ይህን ቀለበት ከኔ ጣት ላይ ማን ያውልቀው? ካለ እሷ፣ ካለ ክበበፀሐይ ይህን ቀለበት ከጣቴ ላይ የሚፈታው የለም፡፡» ብለዋል።

ከባለቤታቸው ሞት በኋላ መኖሪያ ቤታቸውን የሕጻናት ማሳደጊያ እንዲሆን አድርገዋል፡፡ ቀጨኔ መድኃኔዓለም አካባቢ «ክበበፀሐይ የሕጻናት ማሳደጊያ» በሚል መጠሪያ ተሠይሞ፣ አያሌ ወላጆቻቸውን በሞት የተነጠቁ ሕጻናት አድገውበታል፣ አሁንም እያደጉበት ይገኛል፡፡

ታላቁ ደራሲ ሀዲስ ዓለማየሁ ተወዳጁን መጽሐፋቸውን “ፍቅር እስከ መቃብር”ን በተግባር ኖረውት ያለፉ በመሆናቸው የፍቅርና የፅናት አርአያነታቸውና ተምሳሌትነታቸው ሁሌም ሲታወስ ይኖራል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *