ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ ቀሩ።

0

Gen Tefera Mamo disappeared

0 0
Read Time:1 Minute, 31 Second

ብርጋዴር ጄኔራል ተፈራ ማሞ አዲስ አበባ ውስጥ ከቤታቸው እንደወጡ አለመመለሳቸውን ባለቤታቸው ወ/ሮ መነን ኃይሌ ገለፁ።

©️bbc Amharic

ወ/ሮ መነን ስለ ባለቤታቸው ሲናገሩ ትናንት ሰኞ ግንቦት 08/2014 ዓ.ም. ከቤታቸው 5፡15 አካባቢ የወጡት ከጓደኛቸው ጋር ቀጠሮ እንደነበራቸው ገልፀዋል። ከዚያ በኋላ ግን ወደ ቤታቸው ባለመመለሳቸው ደጋግመው ወደ ተንቀሳቃሽ ስልካቸው ቢደውሉም ምላሽ አለማግኘታቸውን ይናገራሉ።

ጄኔራል ተፈራ ከዚህ ቀደም በአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ እንዲሁም በቅርቡ የክልሉ ልዩ ኃይል አዛዥ ሆነው መስራታቸው ይታወሳል ።እንደ ወ/ሮ መነን ገለፃ ከሆነ ጄኔራል ተፈራ ያገኟቸው ሰዎች በዕለቱ አስከ 10 ሰዓት ድረስ አብረው መቆየታቸውን እና ከዚያ በኋላ እንደተለያዩ ነግረዋቸዋል። ከዚያ በኋላ ግን የደረሱበትን ለማወቅ እንዳልቻሉ ባለቤታቸው ተናግረዋል ።

ጄኔራል ተፈራ ሞሞ ከአማራ ክልል ልዩ ኃይል አዛዥነት ከተነሱ በኋላ በተለያዩ መገናኛ ብዙኃን ላይ በመቅረብ አስተያየታቸውን ይሰጡ ነበር።ወ/ሮ መነን የባለቤታቸውን መጥፋት አስመልክቶ ወደ ፌደራል ወንጀል ምርመራ እንዲሁም አዲስ አበባ ፖሊስ በመሄድ ቢጠይቁም ግለሰቡ “በቁጥጥራቸው ስር እንደማይገኝ” እንደገለፁላቸው ይናገራሉ።በአሁኑ ሰዓትም ባለቤታቸውን ለማግኘት ሊኖሩበት ይችላሉ ወደተባሉ የተለያዩ የደኅንነትና የፀጥታ ተቋማት በመሄድ ፍለጋቸውን መቀጠላቸውን ጨምረው ገልፀዋል።

ጄኔራል ተፈራ ማሞ ባለትዳር እና የአራት ልጆች አባት ናቸው።ጄኔራል ተፈራ የስኳር ሕመምተኛ መሆናቸውን የገለፁት ባለቤታቸው የታዘላቸውን መድኃኒት እየወሰዱ አንደነበር አመልክተው፣ መድኃኒታቸውን ካልወሰዱ አንደሚታመሙ በመጥቀስ ስጋት ውስጥ መሆናቸውን ባለቤታቸው ተናግረዋል።ከሚኖሩበት ባሕርዳር ወደ አዲስ አበባ የመጡት በእግራቸው ውስጥ የሚገኙትን ጥይቶች በተመለከተ የሕክምና ክትትል ለማድረግ እንደነበረም ጨምረው አስረድተዋል።”እስሩን ለምዶታል ያለፈበትም ነው፤ የሚያሳስበን ጤናው ሁኔታ ነው” ብለዋል።

የጄነራሉን መሰወር በተመለከተ የፌደራልም ሆነ የአዲስ አበባ ፖሊስ አስካሁን ያሉት ነገር የለም።የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባል ሆነው ለዓመታት በከፍተኛ መኮንንነት ያገለገሉት ብርጋዲዬር ጄነራል ተፈራ ማሞ ከአስር ዓመት በፊት መፈንቅለ መንግሥት ለማካሄድ አሲረዋል በሚል ከሌሎች ጋር ተከሰው ለዓመታት በአስር ላይ ቆይተዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አስተዳደር ወደ ሥልጣን መምጣቱን ተከትሎም ከእስር ተለቀው በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች ላይ ሲያገለግሉ ቆይተዋል።በቅርቡም የህወሓት ኃይሎች ወደ አማራና አፋር ክልሎች በመግባት ጥቃት በሰነዘሩበት ጊዜ የክልሉን ልዩ ኃይል በበላይነት ሲመሩ የነበሩ ሲሆን፣ ከጥቂት ወራት በፊት ደግሞ ከዚሁ ኃላፊነታቸው እንዲነሱ መደረጋቸው ይታወሳል።

Source:ESAT TV

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *