0 0
Read Time:1 Minute, 46 Second

ግልጽ ደብዳቤ

ለአማራ መስተዳድር አመራሮች

ጉዳዩ፡ እራሱን ከጥቃት በመከላከል ላይ ስላለው የአማራ ሕዝብና የአብራኩ ክፋይ ስለሆነው ፋኖ
ለ30 ዓመታትና ከዚያም በላይ የአማራው ሕዝብ ዘርፈ ብዙ በሆኑ ጥቃቶች፣ የዘር ማጥፋት ወንጀልን ጨምሮ ሲገደል፣ ሲታሰር፣ ንብረቱ ሲወድምና ልማቱ ሲደናቀፍ መቆየቱ ግልጽ ነው። ባለፈው አንድ ዓመት በግልፅና በማን አለኝነት የጦርነት አዋጅ ታውጆበት የዘር ማጥፋት፣ የንብረት ማውደም፣ የአስገድዶ መድፈርና የማፈናቀል ወንጀሎች ተፈጽሞበታል። በመጀመሪያው ጥቃት ወቅት መከላከያ ባልነበረባቸው ወይንም ባሸገሸገባቸው አካባቢዎች ይህን ጥቃት የተጋፈጡትና የመከቱት የአማራው ልዩ ኃይል፣ ሚሊሺያው፣ ፋኖውና ማንንም ሳይለይ ሴቱ፣ ወንዱ፣ ወጣቱና ሽማግሌው ተረባርቦ ነው።
ይህም የሆነው ፋኖ በታሪኩና በባህሉ በየጎበዝ አለቃውና በአካባቢ መሪው እየተመራ አገር ሲጠብቅ፣ ደንበር ሲያስከብር የቆየ ታሪክና ባህል ያለው ሕዝባዊ ኃይል በመሆኑ ነው። ይህ የቆየ ባህላችንም ታሪካችንም ነው። የሕዝብን ኃይል ለሚፈሩ ወራሪዎችና ገዥዎች ሰቆቃ ይሁንባቸው እንጅ እኛ ሁልጊዜም የምንመካበት፣ የምንኮራበት መከታችን፣ የአገር የወገን አለኝታችን ኃይል ነው።

ጦርነቱ እየተጋጋለ ሲመጣ ወራሪው ትህነግ በሰው ብዛትና በከባድ መሳሪያዎች ጋጋታ ታግዞ የአማራውንና የአፋርን ክልሎች ዘልቆ ሲገባ መከላከያ ሰራዊታችን ባለባቸው ከጎን ተሰልፎ፣ በሌለባቸው አካባቢዎች ደግሞ እራሱን ችሎ ሕዝባዊ ኃይሉ ቀዬውን ለቆም ሆነ ሳይለቅ በምሬት ተነሳስቶ ወያኔን ተፋልሟል፤ ለመከላከያ ሠራዊቱ ፋና-ወጊ ሆኖ ተከላክሏል። የወያኔን ቅስም ሰብሯል። በዚህም ዋናዎቹ ተሳታፊዎች የአማራና የአፋር ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሺያና ፋኖዎች ናቸው። ይህ ማለት ደግሞ ወዲያና ወዲህ በማያስብል ሁኔታ የአማራና የአፋር ሕዝቦች ማለት ነው።
ይህን የሚያኮራና አገር ጠባቂ ኃይል ለባለውለታነቱ እውቅና በመስጠት የመከላከያ ሠራዊት አባሎቻችን ሚሊሺያውና ፋኖው አብሯቸው እንደተዋጋ፣ እንደሞተ እንደቆሰለ እና ከደጀንነት አልፎ በግንባር ቀደም ተሰልፎ የጠላትን ምሽግ እየሰበረ እንደታደጋቸው በሃቅ መስክረዋል። የፌደራሉም ሆነ የክልላዊ መንግስት ለመከላከያ ኃይል እውቅናና ሹመት ሲሰጥ ፋኖን እንዳላየ አልፎታል። ይባስ ብሎ አንዳንድ የመንግሥት ባለስልጣኖች ይህን መስእዋትነት ለመዘከር ቀርቶ ለመቀበል እንደተቸገሩ ታዝበናል። በባላንጣ አይን ማየት እንደጀመሩም ያደባባይ ሚስጥር ከሆነ ወራት አልፈዋል። ከሁለት ሳምንታት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለኢትዮጵያ ሕዝብ ባደረጉት ንግግር ጦርነቱ አልቋል፤ ትህነግ አደገኛ የሚሆንበትና ለሌላ ጦርነት የሚያበቃ ቁመና የለውም ብለው መከላከያ ኃይሉ ባለበት እንዲቆም ትእዛዝ አስተላልፈዋል። ጠ/ሚኒስትሩ ይህን ባሉበት ወቅት መከላከያው እንዳያጠቃ ቢከለክሉም የትህነግ ጦር ጦርነቱን አላቆመም። ከያዛቸው አካባቢዎች ተሸንፎ ወጥቷል ይበሉን እንጅ ሰሜን ወሎና ስሜን ጎንደር አሁንም በትህነግ ስር ያሉ አካባቢዎች ናቸው። አፋርንም መልሶ በማጥቃት ላይ ነው። የአማራና የአፋር ልዩ ኃይሎች፣ ሚሊሺያና ፋኖም መከላከላቸውን አላቆሙም። ትህነግ አሁንም መግደሉን፣ ንብረት ማውደሙንና መድፈሩን አልቆመም።
መከላከያው ባቆመበት ቦታዎች ተወስኖ ሕዝቡ ብቻውን እንዲጋፈጥ ተደጋግሞ ተደርጓል፣ ደባ በሚመስል መልክ እየተደረገም ነው። ትህነግ ተሸንፏል ሲባልም ስንሰማ የመጀመሪያ ጊዜያችን እንዳልሆነ ልብ ይሏል።
Download

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *