#መንግሥትም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ በፓትርይርኩ አያያዝ ላይ ጥንቃቄ ያድርግ

0
0 0
Read Time:7 Minute, 10 Second

መጋቢ ጥበብ መንገሻ መልኬ

===>>”እኔ ቅዱስ እንደሆኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ፤”(1ኛ ጰጥሮስ 1፤16)

>>#የቅዱስ ፓትርያርኩን ቃል የግላቸው ነው” የሚለው አነጋገር ከሕገ ቤተ ክርስቲያን አንጻር ስህተትና ግድፈት ነው፤
>>#መንግሥትም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ በፓትርይርኩ አያያዝ ላይ ጥንቃቄ ያድርግ፤


የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ #ተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን #የአበው ቀደምት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ #የነቢያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ #የሐዋርያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ #የቀኖና (የሕግ) ቅድስት ቤተ ክርስቲያን፣ #ጥንታዊ ታሪካዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን በመባል ትታወቃለች።

#የተዋሕዶ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መባሏ፤ ቅድመ ዓለም አብ ያለእናት የነበረ፣ ድህረ ዓለም የመጣ ከእናት የተወለደ መንፈስ ቅዱስ የተዋሐደው በማይመረመር ምስጢር (ከሰው አስተሳሰብ በረቀቀና በከበደ ሕልውና) በአካል ሦስት በመለኮት የተዋሐደ አንድ አምላክ ብላ የምታምን በመሆንዋ ተዋሕዶ ትባላለች።
#የቀደምት አበው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መባሏ፤ በዘመነ አብርሃም ያለ ሕገ ኦሪት፣ ያለ ሕገ ወንጌል፣ ያለ ቀኖና ሊቃውንት፤ በግርዘት ምልክትነት በሕገ ልቦና ሰማይና ምድርን የፈጠረ አንድ አምላክ አለ ብሎ መቀበልና ለእርሱም መታዘዝ እምነተ አብርሃምን መስዋዕተ መልከጼዴን ሃይማኖት አድርጋ የተቀበለች የቀደምት አባቶቻችን እምነት በመሆኗ የአባቶቻችን ሃይማኖት (ሃያማኖተ አበው) ቤተ ክርስቲያን ትባላለች።

#የነቢያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መባሏ፤ ቅድመ ዓለም የነበረው አምላክ ከሐጢያት በስተቀር ሰውን መስሎ ተመሳስሎ ሥጋ ለብሦ በሰው አምሳል እንደሚወለድ ጽላተ ሙሴን አክብረው፣ ትንቢተ ነቢያትን ወይም ሕገ ኦሪትን ተቀብለው፣ ዘመናት ቆጥረው ሱባኤ ይዘው ቤተ መቅደስ ሠርተው፣ መስዋዕት እንስሳትን እየሰው፤ አምላክ ሰው፤ ሰው አምላክ የመሆኑን ዜና፤ ቃል ሥጋ የመሆኑን ብሥራት፤ በተስፋ በእምነት ስትጠብቅ የቆየች ቤተ ክርስቲያን በመሆንኗ የነቢያት ቤተ ክርስቲያን በመባል ትታወቃለች።
#የሐዋርያት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መባሏ፤ በነቢያት ትንቢት የተነገረው አምላክ ሰው ሆነ፤ ቃል ሥጋ ሆነ፤ የሚለው ቃል በማኅጸነ ድንግል በመፈጸሙ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን በኋላ መወለዱ በመረጋገጡ፣ ክርስቶስ ተወልዶ ቀስበቀስ እንደ ሰው አድጎ ሐዋርያትን መርጦ አስተምሮ፣ ሂዱና ዓለም ሁሉ እኔ እንደ ስተማርኳችሁ አስተምሩ ብሎ፣ ተጠምቆ፣ ሊቀ ካህናት ሆኖ፤ ቀድሶ ህብስቱን አማንዊ ሥጋ፤ ወይኑን አማናዊ ደም ( የራሱ ደምና ሥጋ) አድርጎ እንደ ሰጠ፣ መከራን ተቀብሎ፣ እንደ ተሰቀለ፣ ሞቶ ተቀብሮ፣ ከሙታን ተልይቶ ተነስቶ ያረገበትን ቀጥሎም ተከታዮቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ያስተማሩትን ተከትላ የምታስተምር በመሆንኗ የሐዋርያት ቤተ ክርስቲያን ትባላለች፤

#የቀኖና ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መባሏ ኢየሱስ ሊቀ-ካህናት ሆኖ ሐዋርያትን ካህናት፤ ክርስቶስ ሆኖ ተከታዮችን ክርስቲያን እንደ አደረጋቸው ሁሉ ከላይ የተጠቀሱት እምነተ ተዋሕዶ፣ እምነተ አበው፣ ነቢያታዊ ሐዋርያታዊ አስተምህሮ ሳትቀንስ ሳትጨምር የምታስፈጽምበት በየጊዜው የተነሱ አበው ሊቃውንት እንደ ጊዜ ግብሩ ሃይማኖታቸውን ተንተርሰው የደነገጓቸው ሕጋጋት ከተዋሕዶ እምነት ጋር አጠጋግታ ነገር ግን ሳትቀላቅል በቀኖና በሕግ አማናዊ እምነቱን የምታስፈጽም ሕግ ያላት በመሆኗ የቀኖና ቤተ ክርስቲያን ትባላለች።

#ታሪካዊት ቅድስት ቤተ ክርስቲያን መባሏ፤ ከሕገ ልቦና አብርሃማዊ ሃይማኖተ አበው ጀምሮ፣ እምነተ ነቢያትን፣ እምነተ ሐዋርያትን በተዋሕዶ፤ በየጊዜው ሊቃውንት ተሰብስበው በመንፈስ ቅዱስ እርዳታ በእምነታቸው ጽናት አሸናፊነት የደነገጉትን ሁሉ በቀኖና አስተባብራ የምታስተምር እና የምታስፈጽም፤ ነገረ ታሪኩንም የምታመሰጥር፣ የምትዘክር፣ የምታከብር፣ የምታስተምህር በመሆንኗ ጥንታዊት ታሪካዊ ቤተ ክርስቲያን ትባላለች።

ከላይ እንደ ተጠቀሰው ሁሉ የቤተ ክርስቲያን ቅድስና በአብርሃም ዘመን፣ በቅዱሳን ነቢያት ዘመን፣ በቅዱሳን ሐዋርያት ዘመን፣ በቅዱሳን ሊቃውንት ዘመን አልተለየም፣ አይለይም ፤ ሊለይም የማይችል አንድ ቅድስና ነው። እንደ ቤተ ክርስቲያናችን አስተምህሮ ይህ ቅድስና በእኛም ዘመን አለ ብለን እናምናለን።
እግዚአብሔ ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ ቅድስናውን የሚያምኑ ትዛዙን የሚፈጽሙ ቅዱሳን ናቸው። ቅዱስ መባል አንዱ ከአንዱ የሚለያይ አይደለም። የአምላክ ቅዱስ መሆን ለእነ አብርሃም፣ ለነቢያት ለሐዋርያት፣ ለሰማዕታትና ለሊቃውንት የደረሰው ቅድስና አንድ ቅድስና ነው።

ከላይ ባጭሩ የተጠቀሰው የሊቃውንት አባቶቻችን አስተምህሮ እንደ ተጠበቀ ሆኖ፤ የጥንታውያን አበው ሃይማኖት አባት ወይም ፓትርያርክ አብርሃም እንደ ሆነ ሁሉ፤ የነቢያት አለቃ ሊቀ ነቢያት ሙሴ ነው። የሐዋርያት አለቃ እራሱ ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ ሆነ ሁሉ፤ በየጊዜው ሊቃውንት ባደረጓቸው ስብሰባዎችና ደንጋጌዎች ሁሉ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ አለው፤ ከዚህም ሃይማኖታዊ ትውፊት ሊቃውንታዊ ድንጋጌ አንጻር ሲወርድ ሲወራረድ እንደመጣው የሊቃነ ጳጳሳቱ አለቃ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ቅዱስ ፓትርያርኩ ነው።

በርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ወቅዱስ ፓትርያርኩ የሚመራው የሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶስ ነው። ይህን በተዋረድ ካጠናን ዘንድ፤ ለሁሉም በየደረጃው የደረሰውና የሚደርሰው ቅድስና አንድ ቅድስና እንጅ የተለያየ ቅድስና የለም። አብ ቅዱስ፤ ወልድ ቅዱስ፤ መንፈስ ቅድስ ቅዱስ እንደሆነ ሁሉ፤ መንፈስ ቅዱስ የሚመራው ቅዱስ ሲኖዶስ ቅዱስ ነው፣ የቅዱስ ሲኖዶስ ሰብሳቢ ፓትርያርክም ቅዱስ ነው።

ከቅዱሳን ሊቃውንት ድንጋጌ በወረደው መሠረት የቅዱስ ፓትርያርኩ ቅድስና የቅዱስ ሲኖዶስ ቅድስና ነው። በቅዱስ ፓትርያርኩ ቅድስና እና በቅዱስ ሲኖዶስ ቅድስና ከአንድነት በስተቀር መበላለጥ ትንሽና ትልቅ የለም። ቅዱስ ፓትርያርኩ የሌለበት ቅዱስ ሲኖዶስ የለም። ቅዱስ ሲኖዶስ የሌለበት ቅዱስ ፓትርያርክ የለም። ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈስ ቅዱስ በበላይነት የሚመራው ነው ብለን እስከምናምን ድረስ፤ ሦስቱም በተዋሕዶ መኖር አለባቸው፤ ይኸውም እራሱ መንፈስ ቅዱስ፣ ቅዱስ ሲኖዶስ፣ ቅዱስ ፓትርያርክ የማይለያዩ ሦስት አካላዊነት አንድ ቅድስና አላቸው ብለን እናምናለን።

ቅዱስ ፓትርያርኩን ቅዱስ ያሰኘው ቅዱስ ሲኖዶስ ነው። ቅዱስ ሲኖዶስ ቅዱስ ለመባል በቅዱስ ፓትርያርክ ርዕሰ መንበርነት መመራት አለበት። ከዚህም አንጻር ቅዱስ ፓትርያርኩ ቅዱስ ሲኖዶስ በሌለበት የሚናገሩት፣ የሚያስተምህሩት፣ የሚያውጁት ሁሉ የቅዱስ ሲኖዶስ ቃል እንጅ ቅድስና የተለየው “የግላቸው ቃል ነው”ሊባል አይችልም።“የግላቸው” የሚባል ከሆነ ቅድስናቸው ተለይቷቸዋል ማለት ነው። በተጓዳኝም ቅዱስ ሲኖዶስ ያለ ቅዱስ ፓትርያርኩ መሪነት የሚያደርገው የቅድስና ነገር አለመኖሩ መረዳት ይኖርብናል።

በመሆኑም ከቤተ ክርስቲያናችን ተዋሕዶ፣ ቀደምት እምነተ አበው፣ እምነተ ነቢያት፣ እምነተ ሐዋርያት፣ ቀኖና ሊቃውንት አንጻር፤ በተዋረድ ፍትሐ ነገሥቱን እንዲሁም በእኛ ዘመን የተሠራውን ቃለ ዐዋዲን ጨምሮ፤ የቅዱስ ፓትርያርኩ ቃል በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የቅዱስ ሲኖዶስ እና የቅድስት ቤተ ክርስቲያ ቃል ነው። ቅዱስ ፓትርያርኩ የሚናገረው ብቻ ሳይሆን፣ የሚለብሰው ልብሰ-ተክህኖ፣ የሚይዘው መስቀልና መቋሚያ የሚያደርገው አክሊል፣ የሚቀመጥበት መንበር፣ ያለው ንብረት ሁሉ የግሉ ለግሉ የሚሆን ነገር የለውም። ቅርስነቱ ለቅድስት ቤተ ክርስቲያን፤ ንብረትነቱ ለቅዱስ ሲኖዶስ ብቻ ነው።

አንድ ጊዜ ቅዱስ የተባለ አካል የሚናገረው ነገር ሁሉ የሚሠራው ሥራ ሁሉ ቅዱስ እንደ መሆኑ መጠን፤ የቅዱሳን ውክልና ያለው እንጅ “የግል” ውክልናን አያመለክትም። የሚናገረውን፣ የሚያስተምረውን፣ የሚመክረውን፣ የሚያውጀውን ነገር ቅድስና ለማሳጣት እና “የግል ነው” ብሎ ለመናገር የሚቻለው፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ድምጽ አይደለም “የግለስብ ድምጽ ነው” ለማለት የሚያስደፍረው፤ አስቀድሞ ቅድስናውን ከፓትርያርኩ ላይ ማንሳት ሲቻል ብቻ ነው። ይህ ደግሞ ፓትርያርክ አንድ ጊዜ ቅዱስ ተብሎ ከተሾመ በኋላ በሃይማኖት ሕጽጽ፣ በቅድስናው ጉድፈት በቅዱስ ሲኖዶስ ምላተ ጉባኤ ተወስኖ ካልሆነ በስተቀር ከቅዱስ ፓትርያርክነቱ ቅድስናውን መሻር፣ የቅዱስ ሲኖዶስ መሪነቱን መቦርቦር፣ የቤተ ከርስቲያን ተወካይነቱን ማንሳት፣ የሚሰጠውን ቡራኬ የሚናገረውን ቃለ ምዕዳን ቅድስና ማሳጣት የማይቻል መሆኑ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን የሚከለክል እስከሆነ ድረስ፤ በተናጠል የቅዱስ ፓትርያርኩን ንግግር “የግላቸው ነው” ብሎ መፈረጁ እጅግ በጣም ስሕተትና ግድፈት ነው።

ነገር ግን ቅዱስ ፓትርያርኩ ሰው እንደ መሆናቸው መጠን፤ በንግግራቸው ጽርፈትና ግድፈት ካለበት፤ በራሳቸው ሰብሳቢነት ከሊቃነ ጳጳሳት ጉባኤ ቅዱስ ሲኖዶስ በአጀንዳ ቀርቦ፤ የታየው ግድፈት በሃይማኖት ሕግጋት፣ በቀኖና ሚዛን ተመርመሮ፣ በመንፈሳዊ ዳኝነት ተፈትቶ በሚሰጠው የእምነት ክህደት ቃል ላይ ስምምነት ተደርሶ በማረሚያ ብቻ ሊስተካል ይችላል እንጅ፤ ይህ ከመሆኑ አስቀድሞ ሊቃነ ጳጳሳት በተናጠል ተነሳስተው የቅዱስ ፓትርያርኩን ቃለ “የግላቸው ቃል” ነው ብለው ለሕዝባውያን ማጋለጥና ቅድስናውን መንፈግ፤ ቅድስናውን ማቃለል፤ የቤተ ክርስቲያን ውክልናውን ማንሳት፤ የቅዱስ ሲኖዶስ ሰብሳቢነቱን መጋፋት ከቀኖና ቤተ ክርስቲያን አንጻር ፈጽሞ አይቻልም።

#በሌላ ተጨማሪ አስተሳሰብ መንግሥትም ሆነ ቅዱስ ሲኖዶስ በፓትርያርኩ አያያዝ ላይ ከባድ ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል፤ ሕወሀት በሀገር ውስጥም በውጪ ሀገርም የሚገኙ ደጋፊዎቹ ከጥቂት እፍኝ ከማይሞሉ ትግራይ ተወላጆች አልፎም ወደ ኋላ የሚጓዙ የኦሮሞ ጠባብ አክራሪዎች ኢትዮጵያን በጠላትነት በሚያይ ከንቱ ፣ አድካሚእና አሰልች የደካሞች ፍልስፍና የተመረዘ ሕልውና ያላቸው ናቸው ።

ከአሁን በፊት እራሱ ሕወሀት ቅዱስ ፓትርያርኩን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ከመንበረ ክብራቸ በማፈናቀሉ፤ በውጪ ሀገር ከፓለቲካው ጋር ተዳምሮ ተጽኖ ፈጣሪ ቅዱስ ሲኖዶስ ተፈጥሮ ሀገሪቱም፣ ለሕዝቡም፣ ለመዕመናንም፣ ለቤተ ክርስቲያን ሃይማኖታዊና መንግሥታዊ አስተዳደር ሕልወና ፈታኝ እና ተገዳዳሪ ሆኖ ቆይቶ በመጨረሻም ለለውጡ መምጣት ምክንያት መሆኑን መዘንጋት የለብንም።

በሌላ አንጻር ምንም እንኳን የለውጡ ምክንያት የተቃውሞው ጠንካራ ኃይል ሆኖ የቆየ ቢሆንም፤ በተቃራኒው ደግሞ በአንዲት ሀገር፤ በአንድ ሕዝብ.በአንዲት ቤተ ክርስቲያን ማዕከላዊ አስተዳደር ላይ መከፋፈል፣ የወገንተኝነት መካረር ምክንያት ያሳደረው የስነ-ልቡና ቀውስ ፣ የፈጠረው ምስቅልቅል እና መወጋገዝ የበዛበትን ዘመን ተመልሰን ስናስታውስ ያደረሰው ኪሳራ በቀላሉ የሚገመት እንዳልነበረ መካድ አይቻልም።

በቅርብ እንደ ምናስታውሰው ሁሉ፤ በቤተ ክህነቱ ውስጥ ሥልጣን እና ጥቅም አጣን የሚሉ ጥቂት የኦሮሞ ጠባቦች፤ ጊዜ ገጠመን ኃይልና ጉልበት አለን በሚል ዕብሪት “የኦሮሞ ቤተ ክህነት” የሚባል ቤተ ክርስቲያን በመዋዕለ ዘመኗ የማታውቀው ሕገ ወጥ እና አፍራሽ ስሪት አቋቁመው ጥቂት የኦሮሞ ሊቃነ ጳጳሳትን ጭምር አሳስተው፤ ማን ይነካናል በሚል ቁንጽል አጓጉሌ ጉራማይሌ ታላቋን ሐዋርያዊት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ለማፍርስ እና በአናሳ አስተሳሰብ በክልል ለመወሰን የመንግሥት ማዕከላዊ አስተዳደርን ለማቃዎስ መናኛ በሆነ እቅድ መሠረት በሌለው ተስፋ እሩቅ የስህተት ጎዳና ለመጓዝ አስበው እንደነበሩ የቅርብ ጊዜ ትወስታችን ነው።

ለዚህም በዋናነት የታሪክ ብልሽትና ክህደት ተጠያቂ የሚሆነው ቤተ ክርስቲያን ከወደቀበት ትቢያ ያነሳችው፤ ጨምደዶ ይዞት ከነበረው የድህነት አሮንቃ ውስጥ ያወጣችው በሊቀ እሬቻ ቄስ በላይ መኮንን የሚመራው ያልተጻፈበት ብራና ቡድን እኩይ ተግባር መጥቀስ የቅርብ ጊዜ በቂ ማስረጃ ነው።

#ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቅዱስ ሲኖዶስ አርቆ አሳቢነት እጦት፤ በመንግሥት አስተዋይነት ችግር፤ ፓትርያርኩ ይህን ተናገሩ እያሉ ማግለል፣ ማማረሩ፣ ከማበሳጨቱ ጋር ተያይዞ፤ ቅዱስነታቸው ሀገር ለቆ የመውጣት እድል ካጋጠማቸው፤ አጥፍቶ ጠፊ ለሆኑት ሕወሀት መንሠራራት ለኦነግም ማቆጥቆጥ ምክንያት እንደሚሆኑ እና ለቤተ ክርስቲያናችን የጎሮሮ አጥንት ለመንግሥት አስተዳደርም አስቸጋሪ ሁኔታ ሊፈጥር እንደሚችል እሩቅ ሳይሄድ አስቀድሞ ማሰቡ ተገቢ ነው።

ይኸውም ሕወሀት ፓትርያርኩን በእጁ ካስገባ፤ እንደ አባ ሰረቀብርሃን ያለውን ለጽድቅም ለገሀነብም የማይመቹ የሁለት ዓለም መደዴ ስደተኞች እና ማስተዋል የተሳናቸው ዝርው ሌሎችንም ሕወሀታዊ በስሜት የሚነዱ የትግሬን መነኮሳት ሁሉ ጳጳስ እያሾመ የሕወሀት ሠራሽ ስደተኛ ሲኖዶስ መመሥረቱ አይቀርም፤ ነውርም ውለታም የማያውቀው የሊቀ እሬቻ ቄስ በላይ መኮነን “የኦርሚያ ቤተ ክህነት” ቡድንም ጥቅሙ ሲጓደልበት፤ የተሰጠውን ሥልጣን ሲያጣ የኦሮሚያ ቤተ ክህነትም ኦነጋዊ ባህሪውን አውጥቶ፤ እኔም ለኦሮሚያ ክልል ፓትርያርክ ያስፈልገኛል በሚል ቅዥት ከሕወህት ጉያ ሂዶ እንድሚሸወጥ አስቀድሞ መጠራጠር አይከፋም ።


ስለዚህ ብፁዕ ውቅዱስ አቡነ ማትያስ ታፈንኩበት ከሚሉት ነገር ነጻ እንዲሆኑ፤ የሚፈልጉትን ሐሳባቸውን ያለገደብ እንዲገልጹ ቢበረታቱ፤ ለሀገር የሚበጅ፣ ለቤተ ክርስቲያን የሚጠቅም፣ ለሕዝብ የሚመች ሐሳባቸው እና አባታዊ ምክራቸው ተደማጭነት ቢያገኝ፤ የአባትነት ክብራቸው እንዲጠበቅ፤ ቅዱስ ሲኖዶስም የተለመደው አባታዊ አመራራቸውን ሳይነፍጋቸው በጥሩ ሁኔታ ተንከባክቦ፣ ተመካከሮና ተደጋግፎ ይህችን በብዙ ችግርና ፈተና ውስጥ ተተብትባ ያለች ሀገራችን እና በብዙ መከራ በሞት ጥላ ሥር በሰቀቀን እግር ከወርች ታሥሮ የሚቃትተው ሕዛብችን የደረሰበትን አስከፊ ዘመን ለማለፍ፤ ቅድስና ያልተለየው መቻቻል፣ ጥበብ ያማከረው አንድነት፣ ብልህነት ያልተለየው አመራርና ከፍተኛ ጥንቃቄ ማድረግ ውሳኝነት ያለው መሆኑን ለመጠቆም እንወዳለን።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *