ሞሀመድ ሳላህ ለቤተክርስቲያን 3 ሚሊዮን የግብጽ ፓውንድ ሰጠ!


የግብጽ ብሔራዊ ቡድንና የእንግሊዙ ሊቨርፑል ኮከብ ተጫዋች የሆነው ሞሀመድ ሳላህ በእሳት አደጋ ምክንያት ውድመት ለደረሰበት ታሪካዊው የቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተክርስቲያን መልሶ ግንባታ ይሆን ዘንድ የ 3 ሚሊዮን የግብጽ ፓውንድ ( $156,664 የአሜሪካ ዶላር) ድጋፍ አድርጓል።

ከሁለት ቀናት በፊት በዕለተ ሰንበት በግብጽ ካይሮ አቅራቢያ የሚገኘው ቅዱስ መርቆሬዎስ ቤተክርስቲያን ከ 5000 በላይ ምዕመናን የጾመ ፍልሰታ ቅዳሴ ሥርዓት በመከታተል ላይ እያሉ በኤሌክትሪክ ምክንያት በተነሳው የእሳት አደጋ ከ 41 በላይ ክርስቲያኖች ሕይወታቸው ሲያልፍ፤ ከ 55 በላይ የሚሆኑ ላይ ከባድ ጉዳት መድረሱ ይታወቃል።


Leave a Reply

Your email address will not be published.