የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸው ተገለፀ::

የዓለም ምግብ ፕሮግራም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች በትናንትናው ዕለት መቀሌ መድረሳቸውን አስታውቋል፡፡

ፕሮግራሙ ፤ በትግራይ እና አፋር ክልሎች ለችግር ተጋላጭ የማህበረሰብ ክፍሎች የሚሰራጨው የሰብዓዊ እርዳታ ተጠናክሮ መቀጠሉን በኢትዮጵያ በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስነብቧል፡፡

በዚህም በትናንትናው ዕለት የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 85 ተሽከርካሪዎች መቀሌ መድረሳቸውን ገልጿል።

በሚቀጥሉት ቀናትም ወደ ሰሜኑ የአፋር ክልል አካባቢዎች በመጓዝ ላይ ያለ 36 ሺህ ቶን ምግብ እና የሰብዓዊ እርዳታ እንደሚደርስ ተጠቁሟል፡፡

በተጨማሪም የሰብዓዊ እርዳታ የጫኑ ተጨማሪ 130 ተሽከርካሪዎች ወደ ትግራይ ክልል እያቀኑ መሆኑን የገለፀው የዓለም ምግብ ፕሮግራም፤ ይህም በተያዘው የፈረንጆቹ ዓመት ወደ መቀሌ ከተጓጓዘው የሰብዓዊ እርዳታ በመጠን ትልቁ ነው ብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.