ባለፈው ሳምንት በትግራይ ክልል የሚገኙት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ (ICRC) ቡድኖች በግጭት ምክንያት ተፈናቅለው በመቐለ ከተማ ለተጠለሉ ከ900 በላይ ለሆኑ ሰዎች የሚያገለግሉ መሰረታዊ የቤት ውስጥ ቁሳቁስ እና የንጽህና መጠበቂያዎችን በድጋፍ አበርክተዋል፡፡

በተጨማሪም የተፈናቀሉት ሰዎች ከተነጣጠሉት የቤተሰብ አባል እና ወዳጆቻቸው ጋር እንዲገናኙ ለማገዝ ከ180 በላይ ነጻ የስልክ ማስደወል አገልግሎት ተሰጥቷል፡፡

በሌላ በኩል ፦ በአማራ ክልል ላሊበላ ከተማ የሚገኘው የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ ቡድን ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር በመተባበር ከ6,000 በላይ ለሆኑ በግጭት ለተጎዱ ሰዎች የቤት ውስጥ መገልገያ እና መጠለያ ቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል፡፡

ድጋፉ በዋናነት በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ለሚገኙ ነፍሰጡር እና የሚያጠቡ ሴቶች ቅድሚያ የሰጠ ነው፡፡

ተጨማሪ መረጃ ፦ ትላንት የዓለም አቀፍ ቀይ መስቀል ኮሚቴ የኢትዮጵያ ልዑክ ከኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር ጋር ያለውን የሰብዓዊ ተግባራት አጋርነት በማደስ እና በማጠናከር እ.ኤ.አ በ2022 ዓ.ም በግጭት እና ብጥብጥ የተጎዱ ሰዎችን በጋራ ለማገዝ የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.