አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ የአብን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አመራሮች ፣ አባላት፣ ደጋፊዎች ማዋከብ እና አፈና እየደረሰባቸው መሆኑን ገልጹ።

0
0 0
Read Time:54 Second


የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሩና የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባሉ አቶ ክርስቲያን ታደለ ፤ የአብን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አመራሮች ፣ አባላት፣ ደጋፊዎች ማዋከብ እና አፈና እየደረሰባቸው መሆኑን በመግለፅ ይህ ድርጊት በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል አሉ።

ደርሷል ስላሉት ማዋከብ እና አፈና ፣ መቼ ? የት ? እንዴት ? እነማንን ? ስለሚሉ ዝርዝር ጉዳዮችን በግልፅ የሰጡት ማብራሪያ የለም።

አቶ ክርስቲያን በተረጋገጠው የማህበራዊ ትስስር ገፃቸው ላይ ፥ ” አብን ዝቅ ሲል የአባላቱና ደጋፊዎች፥ ከፍ ሲልም የንቅናቄውን ዓላማ የሚጋሩ ኢትዮጵያውያን ንብረት መሆኑን ገዥው የብልጽግና ፓርቲና ያዋቀረው መንግስት በውል ሊያውቁት ይገባል ” ብለዋል።

አክለውም ” የተፎካካሪ ፓርቲ የውስጥ ጉዳይ የፓርቲው አባላትና በየደረጃው ያለው ሕጋዊ መዋቅር ጉዳይ ነው። የአብን ጉዳይ ያገባናል የሚሉ አመራሮችን፣ አባላትንና ደጋፊዎችን ማዋከቡ በአስቸኳይ መቆም ይኖርበታል ” ሲሉ ገልፀዋል።

” እየተደረገ ያለው አፈናና ውርክቢያ ማንንም አይጠቅምም፤ በተለይ ደግሞ ገዥውን ፓርቲ አይጠቅምም ” ሲሉ አፅንኦት ሰጥተዋል።

አቶ ክርስቲያን ፤ ” አብን በሕዝብ ምርጫ በራሱ መንግስት ለመሆን የሚታገል ፓርቲ እንጂ የገዥው ፓርቲ ሁሉንም የመጠቅለል ስካር መደገፊያ ምርኩዝ አይደለም ” ሲሉ ፅፈዋል።

አቶ ክርስቲያን ታደለ ከጥቂት ቀናት በፊት የፓርቲያቸው ስራ አስፈፃሚ ከህገደንብ እና አሰራር ውጭ በመሆን አፍራሽ ድርጊቶችን እና የዲሲፕሊን ጥሰቶችን ፈፅመዋል በሚል የመጨረሻ ያለውን ማስጠንቀቂያ ሰጥቷቸው እንደነበር ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ አቶ ክርስቲያን ፤ መሰል ውሳኔዎችን ለመወሰን የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ሥልጣን የሌለው መሆኑን መግለፃቸው አይዘነጋም።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *