” ኢትዬጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች።”

0
0 0
Read Time:2 Minute, 4 Second

በ ዶክተር መኮንን ተፈሪ

ኢትዬጵያን ያኮራትና የስኮራት፣ ጠ/ሚኒስትር ፣ ዶ/ር፣ ኮሎኔል፣ ኢንጂነር ፣ ኢኮኖሚስት፣ አርኪቴክቸር፣ የኢትዮጵያን 3ቱን ታላቅ ቋንቋዎች አቀላጥፎ የሚያወራ፣ የአለማችንን ትልቅ የሚባለውን የሰላም ሎሬንት ፣ በአለም መድረክ ላይ ወቶ በእንግሊዝኛ ቋንቋ በአለም ብቃቱን ያስመሰከረ ፣ 4 መጽሀፍ ለህዝብ አቅርቦ በፃፈው ርዬተ አለም ህዝቡን የሚመራ፣ በአረንጓዴ አሻራ በአለም 6 ቢሊዬን የዛፍ ተክል አለምን ጉድ ያስባለ፣ የራሱን የስለላ መዋቅር አዘጋጅቶ በአለም ተወዳዳሪ በዘመኑ የሳይበር ቴክኖሎጂ አደራጅቶ ለአገራችን የፀትታ መዋቅር ያደራጀ፣ የኢትዮጵያን የመከላከያ አቋም ፣ የአለባበስ ፣ የሰልፋና ፣ የአወቃቀር ፣ የዘመናዊ መሳሪያ ፣ በድሮንና ባህር ሀይል የተደገፈ ከአፋሪካ አልደፈሬ ከሚባሉት አገር ተርታ ያሰለፈ ፣ የመከላከያ መስርያቤቱን በአለም አሉ ከሚባሉ አገሮች የዘመናዊ ህንፃ ሰርቶ ያዘመነ ፣ ኢትዬያን በሁለት አመት ውስጥ 2 ሳተላይት በጠፈር ላይ አመንጥቆ አደግን ካሉት አገሮች እኩል ያስቀመጠ፣ ከተማችንን ፣ የታሪክ ቅርስ የሆኑትን ቤተመንግሥትቶቻችንን ድንቅ በሚባል ሁኔታ አድሶ አዘምኖ ለአለም ጎብኚዎች ያበቃ፣ በውድ ተወዳጅ ባለቤቱ ከ25 በላይ የሁለተኛና የአንደኛ ደረጃ ት/ቤት በራሱ መጽሀፍ ሽያጭ ያሰራና ያስመረቀ፣ ከሁሉም ከሁሉም በላይ የአባያችንን ግድብ ከመፍረስ አደጋ አውጥቶ እንደገና በአለም ደረጃውን የጠበቀ አድርጎ አስተካክሎ ፣ ባልበገሬነት እምቢ አሻፈረኝ ብሎ የጀግኖች አባቶች አያቶቹን ታሪክ አሰመርኩዞ ግበጽን፣ ሱዳንና መላው የአለምን ጫና ተቋቁሞ ግድባችንን አስሞሉቶ በሚቀጥለው 2 ወር ውስጥ 750ሜጋ ዋት የመብራት ማመንጨት የሚጀምር መሆኑን ለህዝብ የበሰረ፣ ለዘመናት ያላለቁ ትልልቅፕሮጄክቶችን አያስጨረሰ በተደጋጋሚ ሪባን አየቆረጠ።፣

በይቅርታና ሆዱ የሚራራ መንገድ ላይ ከመኪናው ወርዶ የደከሙና ጉዳት የደረሰባቸውን አዛውንት ወገኖቻችንን ድጋፍና የሞራል ጽናት የሚሰጥ፣ የከተማ ጽዳት እራሱ መጥረጊያ ይዞ ቆሻሻን ሳይፀየፍ ዝቅ ብሎ ከህዝብ ጋር ወርዶ ያጸዳ መሪ፣ በመደመርና በመቻቻል አገርን ከመበታተን ያተረፈ፣ ከሩብ አመታት በላይ በጠላትነት ተፈራርጀን ከኤርትራ ወንድሞቻችንን እህቶቻችችንን ጋር ተመልሰን ተላቅሰን በአንድነት እንድንኖር ያደረገን፣ ሀገራችን ከገባችበት የዘር መከፋፈል ቅርቃር ለማፍረስ ከተሰራባት የ50 አመት ደባ ‘ ኢትዬጵያ አትፈርስም እሷን ለማፍረስ ያሰበ ቀድሞ ይፈረሳል’ በማለት ህዝቡ ጭካኔ ውስጥ እንዳይገባ አረጋግቶ ጠላቶቻችንን ድባቅ ከቶ የሳፈረ የዘመናችን በአንደኝነት ከአፍሪካ የፌስቡክ የመሪዎችን በቀዳሚነት የሚመራው ፣ ለመላው የአፋሪካ መሪዎችን ችግራችንም እድገታችንንም በአፍሪካውያን ብቻና ብቻ ነው ብሎ የአፍሪካን ህብረት በሚገርም ቅጽፈት ያስተናበረ፣ በአለም ላይ ብቸኛውና እስከዛሬ በታሪክ የልታየው ድንቅዬ ኢትዬጲያዊው ዶ/ር፣ ኮሎኔል፣ ሎሬንት አብይ አህመድ አሊ፣ ክርስትናን፣ እስልምናን አቀላጥፎ የሚያውቀው ጠቅላይ ሚኒስትራችን ፣ ፈጣሪ ጤናውን እድሜውን ሰቶህ በመጪው ታሪካዊ ምርጫ በህዝብ ድምጽ ተመርጠህ የኢትዮጵያን ትንሳኤን እንድናይ ከልብ ምኞታችን ነው። የሚሰራ ሰው ሁሉ ይሳሳታል ፣ ፍጹም የሆነ ሰው ማንም የለም፣ የሚቀጥለው የስልጣን ዘመንህ ከዘረኝነት፣ ከአድሎ፣ ከጉቦኝነት፣ በዲሲፕሊንና በእውቀትና በብቃት ብቻና ብቻ ላይ የተመርኩዞ፣ በዘመኑ ቴክኖሎጂ የተካነ የመንግስት መዋቅርና የሰው ሀይል በየመዋቅሩ በማድረግ ኢትዮጽያን እንደስሟና እንደቀደመው ታሪኳ ለሚቀጥለው ትውልድ ተሸማቆባትና ፣ አፍሮባት በጥላቻ በባእድ አገር ለመኖር እያለ በየባህሩና በየበረሃው የሚሞትበት ሀገር ሳትሆን፣ ልቡን ባገሩ ላይ ነፍቶ ፣ ተምሮ ስራ ይዞ አግብቶ ወልዶ በሀገር ላይ የሚኖርበት ዘመን እንዲመጣ 7 ቀን እንደምትሰራ ሁሉ፣ ካጠገብህም ያንተን ራእይ የሚገብሩ ሰዎች በማድረግ ኢትዮጵያውያችንን ትንሳኤዋን እንድታፋጥንልን በመትወደው ፈጣሪ ስም እንማፀንሀለን።

” ኢትዬጵያ በልጆቿ ታፍራና ተከብራ ለዘላለም ትኖራለች።”

ጸሀፊው መኮንን ተፈሪ (ለንደን)

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *