ከድምፃዊ ሃጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ ከሰኔ 24 ቀን 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ለ64 ቀናት በእስር ላይ የነበሩት ይልቃል ጌትነት (ኢንጂነር) በዋስ ተፈትተዋል፡፡ በታሰሩበት የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እሥረኛ ማቆያ (በትውስት) ሆነው፣ ከሰብዓዊ መብት አያያዝ ጋር ቅሬታ ሲያቀርቡ ቆይተዋል፡፡ በተለይም በእስረኛ ማቆያ የኮሮና ቫይረስ የያዛቸው ተጠርጣሪዎች በመገኘታቸው ሥጋታቸውን ሲገልጹ የቆዩት የኢትዮጵያ ኃይሎች ንቅናቄ (ኢኃን) ሊቀመንበር ይልቃል (ኢንጂነር) ከተለመደው ወጣ ባለ ሁኔታ የራስ ፀጉራቸውና ፂማቸው ከማደጉ በስተቀር በሰላም መፈታታቸው ታውቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published.