0 0
Read Time:1 Minute, 26 Second

ወ/ሮ ሠናይት ሺፈራው
1963 – 2021
—————–

ውድ ወ/ሮ ሠናይት ከአባታቸው ከአቶ ሺፈራው ደሳለኝና ከናታቸው ከወ/ሮ ሕይወት ጣላርጌ በፈረንጆች አቆጣጠር በመጋቢት 30 ቀን 1963 ዓ/ም በድሬዳዋ ከተማ ተወለዱ።

ዕድሜያቸው ለትምህርት ሲደርስ የኡንደኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በቅዱስ ሚካኤል አንደኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታተሉ። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን ደግሞ በዲሬዳዋ አጠቃላይ ከፍተኛ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት ተከታተሉ። ከዚያ ቀጥለው የኮሌጅ ትምህርታቸውን ስመጥር በነበረው በአዲስ አበባ የንግድ ትምህርት ቤት (Commercial School) ተከታተሉ።

ከተመረቁም በኋላ በዚያ ከባድ ዘመን በሙያቸው አገራቸውን ያገለገሉ አገር አፍቃሪ ዜጋ ናቸው። ጫናው ሲበዛባቸው ግን ውድ አገራቸውን ጥለው ወደ እንግሊዝ አገር ለመኮብለል ተገደዱ።

የሥራ ሰው እንደሙሆናቸው መጠን በእንግሊዝም አገር ብዙ ነገሮች አከናውነዋል። ሙያቸውንም ለማሻሻል በሰሜን ለንደን ዩኒቨርሲቲ (University of North London) ከፍተኛ ትምህርታቸውንም ተከታትለዋል።

ከዶ/ር በቀለ ገሠሠ ጋር ትዳር በመመስረት ስንታየህንና ስናፍቅሽን ወልደው በከፍተኛ ፍቅር ያሳደጉ መልካም እናት ነበሩ።

የግል ሥራ መስኮችን በመክፈት ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረጉ ታታሪ ሠራተኛ ነበሩ።

በበጎ አድራጎት ሥራዎችም ያደረጉት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚከተሉትን ይጨምራል፣

አግሮፎሬፕ የሚባል ምግባረ ሠናይ ድርጅት በ1996 ዓ/ም ከተከፈተ ጀምሮ 1ኛ/ ለአዋቂዎች የቋንቋና የሙያ ሥልጠና፣ 2ኛ/ ለሕፃናት የትምህርት ድጋፍ (Homework Clubs) እና 3ኛ/ አጠቃላይ ምክሮች በሚለገሱባቸው መርሃ ግብሮች ላይ በመሳተፍ እጅግ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደረጉ ወገን ነበሩ።

እንደዚሁም ከጓደኞቻቸው ጋር በመተባበር የቅድስት አርሴማ ማህበር በማቋቋም በኢትዮጵያ አቅመ ደካሞች የሆኑትን ከ400 በላይ የሚሆኑ ሕፃናት የትምህርት፣ የልብስና የምግብ ወጪዎች በመሸፈን ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ አብቅተዋል። ጧሪ የሌሏቸውንም ጥቂት እናቶች በመደገፍ ላይ ነበሩ።

በኢትዮጵያ ምድር ዘርና ኃይማኖት ላይ ያነጣጠር (በተለይ በአማራውና ኦርቶዶክስ ተከታይ ንፁሐን ወጉኖቻችን ላይ የሚካሄደው) ጭፍጨፋና ማፈናቀል ቀርተው ዲሞክራሲና ሰላም እንዲሰፍን ከፍተኛ ፀሎትና ትግል ሲያካሂዱ የቆዩ ከፍተኛ ተቆርቋሪ ንፁህ ዜጋ ነበሩ።

ኦ አዳም አንተ መሬት ውትገብር ውስተ መሬት የተባለው የጌታ ቃል አይቀርምና እኚህ ትልቋ ወገናችን በድንገት ከዚህ ዓለም ተለዩብን። አምላክ ነፍሳቸውን ይማርልን፣ በአፀደ ገነት በአብርሃም፣ በይስሐቅ በያዕቆብ አጠገብ ያሳርፍልን፣ ለዘመድ አዝማድ በሙሉ መጽናናትን ይስጥልን።

ከቤተሰብና ከወዳጅ ዘመዶቻቸው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *