የባንክ ሃላፊው ከ2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ስለመውሰዱ የሚያስረዳ ማስረጃ ስለተገኘበት ክስ ተመሰረተበት።

0
0 0
Read Time:1 Minute, 16 Second

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ከደንበኞች የማይንቀሳቀስ ሂሳብ 2 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ ስለመውሰዱ የሚያስረዳ ማስረጃ የተገኘበት ግለሰብ ክስ ተመሰረተበት።

በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን ሆነው ሲሰሩ የነበሩ ሶስት የባንኩ ሰራተኞችም በዚሁ መዝገብ ክስ ተመስርቶባቸዋል።

➡️ 1ኛ ተከሳሽ አቶ እስጢፋኖስ ሙሉጌታ ገቢሳ (የባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን)

➡️ 2ኛ ተከሳሽ ወ/ሮ አስኩዋል ወልደአብዝጊ ߹

➡️ 3ኛ ተከሳሽ በቀለ ሽፌ

➡️ 4ኛ ተከሳሽ ይልቃል አዳነ ናቸው የሙስና ወንጀል ፈጽመዋል ሲል በጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ዘርፍ የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዐቃቤ ህግ ዳይሬክቶሬት ጄነራል ክስ የመሰረተባቸው።

አንደኛ ተከሳሽ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ” ፒኮክ መናፈሻ ቅርንጫፍ ” ተቀዳሚ ባንኪንግ ቢዝነስ መኮንን የሥራ ኃላፊ ሆኖ ሲሰራ ያልተገባ ጥቅም ለማግኘት በማሰብ በባንኩ ደንበኛ ከሆኑ ግለሰቦች ሳይንቀሳቀስ በመቆየታቸው ምክንያት የማይንቀሳቀሱ ሂሳብ (Inactive) የነበሩ የቁጠባ ሂሳቦች ሃላፊነቱን በመጠቀም ወደ ተንቀሳቃሽ ሂሳብ (Active) በመቀየር ደንበኞች ከሂሳባቸው ጋር ለሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ያስተሳሰሩትን ስልክ ቁጥር ሲስተም ላይ የተቀየረውን በማፅደቅ ከደንበኞች ሂሳብ ላይ በተለያዩ ጊዚያት በራሱ ሥም በተከፈቱ የሂሳብ ቁጥሮች በአጠቃላይ ብር 2,535,000 (ሁለት ሚሊዮን አምስት መቶ ሰላሳ አምስት ሺ) ብር በሞባይል ባንኪንግ በማስተላለፍ ወስዷል።

2ኛ፣ 3ኛ እና 4ኛ ተከሳሾች ደግሞ ደንበኞች ባልቀረቡበት ፣ ማንነታቸው ባልተረጋገጠበት እና የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት መጠየቂያ ቅፅ ባልሞሉበት ሁኔታ የደንበኛውን ሂሳብ የደንበኛው ባልሆነ ስልክ ቁጥር ለሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት በመመዝገባቸው በስራ ሃላፊነታቸው ሊጠብቁት እና ሊከላከሉት የሚገባውን የመንግስት ልማት ድርጅት ጥቅም የሚጎዳ ተግባር በመፈፀማቸው የመንግስት የልማት ድርጅት ሥራን በማያመች አኳኋን መምራት የሙስና ወንጀል ክስ ተመስርቶባቸዋል፡፡

ተከሳሾች ዛሬ ግንቦት 11/2014 ዓ.ም በፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ ፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት ቀርበው የክስ ቻርጁ እንዲደርሳቸው ተደርጎ ክሱ በንባብ የተሰማ ሲሆን የተከሳሾችን የክስ መቃወሚያ ለመጠባበቅ ለግንቦት 24/2014 ዓ.ም ቀጠሮ ተሰጥቷል ።

ምንጭ፦ የፍትሕ ሚኒስቴር

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *