የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ፍቃደኝነቱን የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታትመግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል።

0
0 0
Read Time:39 Second

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀ መንበር ሙሳ ፋኪ መሀመት የትግራይ ክልል መንግስት ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ያለውን ቁርጠኝነት እንዲሁም በአፍሪካ ህብረት መሪነት በሚካሄደው የሰላም ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ፍቃደኝነቱን መግለፁን በደስታ እንደሚቀበሉት ገልፀዋል።

ይህን የገለፁት የትግራይ ክልልን እያስተዳደረ ያለው ህወሓት በአፍሪካ ህብረት መሪነት ከፌዴራል መንግስት ጋር እደራደራለሁ ካለ በኃላ ባወጡት መግለጫ ነው።

ሊቀመንበሩ ይህ አዎንታዊ የሆነ እድገት በኢትዮጵያ ውስጥ ሰላምን ወደነበረበት ለመመለስ ልዩ አጋጣሚ ነው ሲሉ አጽንኦት ሰጥተዋል።

የትግራይ ክልል መንግስት ለድርድር ዝግጁ መሆኑን በመግለፁም ሊቀመንበሩ አመስግነዋል።

ከዚህ ባለፈ ሁለቱም ወገኖች (የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግስት እና የትግራይ ክልል መንግስት) በአስቸኳይ የተኩስ አቁም ለማድረግ እንዲሰሩ እና የፊት ለፊት ንግግር እንዲያደርጉ አሳስበዋል።

ሊቀመንበሩ በአፍሪካ ህብረት በሚመራው የሰላም ሂደት ላይ ሁለቱም ወገኖች የሚስማሙባቸው ዓለም አቀፍ አጋሮች እንደሚካተቱ ጠቁመዋል።

ሙሳ ፋኪ መሀመት በመግለጫቸው ላይ በዚህ ወሳኝ ወቅት የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ በአፍሪካ ኅብረት ለሚመራው የሰላም ሂደት ድጋፉን እንዲያጠናክር ጠይቀዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *