0 0
Read Time:42 Second

ፍርድ ቤቱ ትላንት መጋቢት 27 ቀን 2014 ዓ.ም በዋለው ችሎት ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ በ50,000 ብር ዋስ እንዲለቀቅ መወስኑ ይታወሳል።

የተራራ ኔትዎርክ በይነ-መረብ መገናኛ ብዙሃን ዋና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ ከታሰረ ትላንት 117 ቀናት ቢሆነውም ክስ ሳይመሰረትበትና የዋስ ይግባኝ ጥያቄውም በጊዜ ቀጠሮ እየተላለፈ ዉሳኔ ሳያገኝ እስከ ትላንትና መቆየቱ ይታወሳል፡፡

ጋዜጠኛ ታምራት ነገራ መጋቢት 1 ቀን 2014 ዓ.ም በገላን ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት በቀረበበት ወቅት፣ ፍርድ ቤቱ ባስተላለፈው ውሳኔ አቃቤ ህግ በ15 ቀናት ውስጥ ጋዜጠኛው ላይ ክስ እንዲመሰርት ትዕዛዝ ከሰጠ በኋላ ጋዜጠኛው በጠበቃው በኩል መጋቢት 02 ቀን 2014 ዓ.ም በዋስ እንዲለቀቅ የሚጠይቅ የዋስ መዝገብ ከፍቶ ነበር፡፡

የኦሮሚያ ጠቅላይ ፍርድ ቤት የዋስ መዝገቡን ከተመለከተ በኋላ በተለያዩ ጊዜያት ለመጋቢት 08, 13, 15, 20 እና 27 ተለዋጭ ቀጠሮ እየሰጠ ቆይቷል።

በመጨረሻም ትላንት መጋቢት 27 ቀን 2014 . በዋለው ችሎት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የጋዜጠኛው የዋስትና መብት እንዲከበርለት ውሳኔ አሳልፏል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *