126ኛው የአድዋ የድል ቀን አከባበር በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መኖሪያ ፤ቤት

0
0 0
Read Time:5 Minute, 50 Second

የካቲት 27 ቀን 2014 አ.ም
6 /3/2022 አቶ ከፈያለው

126ኛው የአድዋ የድል ቀን አከባበር በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ መኖሪያ ፤ቤት በነበረውና አሁን ሙዝየም እየሆነ ባለው ቤትና ግቢ፤

በእለቱ ከተለያዩ የዩኬ ክፍሎች የመጡ ኢትዮጵያዊያንን፤ካሪቢያን ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ፤እንዲሁም ፈረንጆች በተገኙበት በሞቀ ሁኔታ ተከብሯል።

የዚህ ስብስብ አባላት ትንሽ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ በችኮላ እንደሚከተለው የቀረበ ሲሆን፤በባለሙያ ቀርቦ ከሆነ ለድግግሞሹና፤ለጥሁፉ ጥራት ይቅርታ።

ጉዞ ከሎንደን ከተማ ወደ ታሪካዊቷ ከተማ ባዝ ከተማ፤ ሲሆን
የመነሻ ቦታው አስቀደሞ በተነገረው መሰረት ከቪክቶሪያ ባቡር ጣቢያ(Victoria station) አጠገብ ካለው መንገድ አጠገብ ነበር።

ጉድ ፈላ ዘንድሮ በ”አበሻ ቀጠሮ”፤
በንኖ ጠፋ መስል ያውም ተደናብሮ።

በሚገርም ሁኔታ ከአያቶች እስከ ልጅ ልጆች ሁሉም ቀድመው ነው።

የእለቱ ቅዝቃዜ የዋዛ አልነበርም፤እግሮችን ድንዝዝ፤ጣቶችን ቁርጥምጥም ፊትንም የሚለጭ ነበር።ወገን ይህን ሁሉ ተቋቁሞ የመገኝተ ምስጢሩ ሁሉም በአድዋው የጀግንነት መንፈስ ከጠዋቱ ቆርጠው መነሳታቸው እንደሆነ ጥርጥር የለውም።

ሁላችንም ቦታችን ከያዝንና የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ከተላለፈ በኋላ “ፈታ ዘና” የሚያደርጉ ፤ከአድዋ ጋር የተያያዙ ዜማወች መሰማት ጀመሩ፤ከትንሽ ጉዞ በኋላ ሻይ፤ቡና ዳቦውና ሌላው ሌላውም ፤በአድዋ ዘመቻ ወቅት ቀርበው የነበሩ የስንቅ አይነቶች ከቋንጣ በቀር ሁሉም ቀረቡ።

ከቁርስ በኋላ ፤የዘመቻው ጉዞ መሟሟቅ ጀመረ።ከፊት ለፊት ተቀምጠው የነበሩት ሁለት ወጣቶች(ሀብታሙና ሲሳይ) ፤ዜማወችን በማቀነባበር ብቻ ሳይሆን ፤ከአጤ ምንይልክ፤እቴጌ ጣይቱና ከአድዋ ድል ጋር የተያያዘ የጥያቄና መልስ ውድድር በማቅረባቸው በጣም ያስደሰቱንና ያስደነቁን ሲሆን፤በዚህ አጭር ግዜ እንዲህ አይነት ዝግጅት እንዴት ቻሉ የሰኙን ሲሆን ፤የፈጠራ ችሎታቸው በአይናችን ያሰኙን ነበር።

ከሁሉም የበለጠ ጉዟችንን ያደመቀው አንዲት የ12 አመት ልጅ ስለ አድዋ ድል በአማርኛና በእንግሊዝኛ፤ያደረገቸው ንግግርና በኋላም ክእድሜ እኩዮቻ ጋር ሆነው ያሰሙን መዝሙርና ዘፈን ነበር።

ምንም ሳይሰማን የአውቶቡሱን መንገድ አጠናቅቀን ከእግር ጉዟችን(የአድዋ ጉዞ መታሰቢያ) መነሻ እንደደረስን ሰንደቅ አላማችንን ከፍ አድርገን መንግዳችንን ቀጠልን።

የሰንደቅ አላማችን ምስጢሩ ምን ይሆን?

በጉዟችን መሀል የአካባቢው ሰወች በአድናቆት ይመለከቱን እንደነበረ። በተለይ በሰንደቅ አላማው ላይ አተኩረው ያዩ ነቡር። ፤የነበራችሁ መመስከር ትችላላችሁ ።ፎቶና ቪዲዮም የሚያነሱ ነበር ።ለንደን ላይ ብዙ ሰላምዊ ሰልፎች ስናደርግ ፤እንዲህ አይነት ነገር ታይቶ አያውቅም ፤ከኮርን ወሉ የG20 ሰልፍ ውጭ።በጣም የሚገርመው እግረኞች የታዘዙ ይመስል ለኛ የቅድሚያ መንገድ ሲሰጡ ማየታችን ነው። በየመንገዱ ጥያቄው ብዙ ነው።who are you? Which country’s flag is this? What the purpise of this journey? Etc ይቀረቡ ነበር ። መንገድ
የሚመሩንና የሚረዱን ካሪቢያዊያን ለጥያቃወቹ በድፍረት መልስ ይሰጡ ነበር።ከኛም ወገንሁሉም በየፊናው የሞከረ ይመስለኛል ።

እኔም የምናገረውን ዲፕሎማሲያዊ የእንግሊዝኛ ቃላት በአእምሮየ አሰላስል ነበር።
“ከማን ላይ ሆነሽ ማንን ታሚያለሽ “የተሰኘው አባባል ትዝ ብሎኝ፤የጣሊያን ቅኝ ግዢወችን በአድዋ ድል ያሸነፍንበትን ለማክበር እንደሆነ ልናገር እያሰላሰልሁ ሳላ እድሉ ቢያመልጠኝም ከጔደኜቻችን አንዱ የሰማውን በእጁ እያሳየን ያ ረጅም ( እንግሊዛዊ)፤”they’re Ethiopians,Ethiopia has never been a colony,It’s the only nation , where colinalism was defeated at the battle of Adwa by king Menelik II” ,we’re here to celebrate that victory where HM Haileslase lived….” ሲል መስማቱን ሲነግረን ሁላችንም ተገርመን ነበር።

አሽከርካሪወች እንኳን ሳይቀር ገና ከሩቅ አይተውን ያለማንም አዛዥ ሲቆሙና የመጨረሻው ሰው እስኪያልፍ መጠበቃቸውም አስደናቂ ነበር ። አንድ በቅርብ ነዋሪ የሆነ ወንድም “የአካባቢው ሰው እንዲህ ነው” ሲል አረጋግጦልናል።
ምናልባች ጃንሆን ይህን አይተው የሆን ባዛን ለመኖሪያነት መርጠዋት የነበር?

ጉዟችን በሆታ ቀጥሉ በግምት 300 ሜትር ያህል ሲቀር፤በሰንደቅ አላማችን ተውቦ የመግቢያ በሩ የተዘጋ ይመስል ነበር።መግቢያው በሌላ ሳይሆን አይቀርም እያልን አጠገቤ ካለው ሰው ጋር እያወራን ፤ሳለ ፊሽካ ሲነፋ አልሰማንምብነገር ግን ልጆች ግን ድንገት እንደነ ሀይሌ ገ/ስላሴና ቀነኒሳ ከንፋስ በፈጠነ መንገድ ሩጠው ፤ሁሉም አሸናፊወች የመሆናቸውን ምልክት ሲያሳዩን ነገሩ ገባን(ሪባን? የሚሉት መሆኑ ነው)

እግቢው ስንደረስ ከመሬት ላይ በተተከለ ብረት(እንጨት) ላይ ሆኖ የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ ሲውለበለብ እየን።የእፕዲስ አበባውን ቤተመንግስትን የማየት እድል ሳላላገጠመኝ፤በዚህ እድሜየ እንደተሳካልኝ ነው የቆጠርሁት።

ከዚያማ በኋላ ግቢው ቀለጠ! በሆታ፤እልልታና ጭፈራ ተደበላለቀ።በልጅነቴ ያሳለፍኳቸው የጥምቀት ቀኖች ትዝ አሉኝ።

በጭፈራው መሀል አንድ እንደኔ ቀላ ያለወጣት የአጤ ቴዎድሮስ ምስል ያለበትን ልብሶ ለየት ባለ ሁኔታ ሲንጎራደድ አይቼው፤በእንግሊዝኛ ላናግረው ቃላቴን እያመራርጥሁ ሳለ ድንገት ፤እንደ መብረቅ ጮሆ ዘራፍ ብሎ ከመሀል ገባና ቀጠለበታ!የአፄ ምንይልክን ታሪክ ከአጎለላ እስከ አድዋ እያነሳ በዚያ ድምፁ የተቀመጠውን ብቻ ሳይሆን የቆመው ሰው ሁሉ የቁመቱን ያህል እንዱዘልል አደረገው።ከጭፈራው በኋላ እራሴን እስተዋውቄ ስሙን ስጠይቅ የሁለታችንም የቅፅል ስሞች አንድ ሆነው ግጥም ጥም አልን። የዚህ ስንስብ አባላት አንድ ቀን እንዲሰሙት አምሳያየን አሰምኜ ማምጣቴ አይቀርም።ብቻ ለሽልማት ተዘጋጁ።

የምሳ ሰአት ቀጠለ፤አየ መስተንግዶ፤የወንዱ የሴት ሽርጉድማለት እፁብ ድንቅ ነበር።

ከዛ ሁሉ ሰው መሀል የአንድ ሰው ጉዳይ እጅግ ማርኮኛል።ፍስሀ ይባላሉ በቀጥታ አቶ ያላልኩት ሌላ ማዕረግ ቢኖራቸው እንዳልዘረጥጥ በማሰብ ነው።ከጉዞው መነሻ ጀምሮ በማስተባበርና በመምራት ችሎታቸው እጅግ ነው የተደነቅሁት፤ልጅ አዋቂ ሳይሉ በትህትና ፤ሲያዳምጡና ሲያስረዱ በማየት እጅግ ነው የኮራሁባቸው፤ኢትዮጵያዊ፤ጨዋነት ይሏል እንዲህ ነው።

ሌላው የሚያስገርመና የሚያስደንቀው ፤የሴቶች ተሳትፎ ከመስተንግዶው ውጭ በአገር ባህል ልብሳቸው ተውበውና ደምቀው መታያታቸው።አውቶቡሱ ውስጥ በተራ ልብስ(ordinary clothes) የነበሩት ሁሉ ፤ሁሉም በጥበባቸው ተውበው መገኘታቸው እስካሁን ምስጢሩን አልተደረሰበትም፤ያም ሆነ ይህ ትልቅ ምስጋና ይገባቸዋል።ልብሱን ከየት አመጡት?

፤የልጆች ነገርማ(ፀባይማ) ተወዳዳሪ የለውም፤ እንደልጅነታቸው እንኳንስ ጭቅችቅና ግጭትት የአንዳቸው ቅጥ ያጣ ድምፅ አልተሰማም፤ ለቁም ነገር ያብቃልን።

በእህል ውሀው መሀል የበአሉ ታዳሚ የሙዝየመን ልዩ ልዩ ክፍሎች ለማየት እድል ያገኙ ሲሆን፤እኔም ከስንት የሰልፍ ቆይታ በኋላ እድል አግኝቼ እየጎበኝሁ ሳለ፤ከፊት ለፊቴ የጃንሆይን ፎቶ ሳይ ሳለውቀው በአይነ ህሊንና ወደ አዲስ አበባ ነግጃለሁ ።

ከርእስ በመውጣቴ ይቅርታ፤ነገሩ እንዲህ ነው፤

ከባላገር(ገጠር) ስመጣ፤ከነቆመጤ (በትር ) ነበር፤የመጣሁት፤በአካባቢያችን ያለው በረት ሌላው በትር ይይዛል እንጂ ሴት እጁን (ባዶውን) አይሄድም።
የአዲስ አበባ(የአራዳ) ልጆች ደግነታቸው ተዝርዝሮ አያልቅም።ታዱያ ሲጣሉም ቡጢያቸው አድርስ፤የእጆቻቸውና የእግሮቻቸው ፍጥነት እኩል ነው ።ቡጢያቸው ደጋግሜ ቀምሻታለሁ፤አነሱም የኔን ቆመጥ ቀማምሰዋታል የጥላችን መነሻ የልጅነት ነገር ነበር፤እኔ በነሱ አማርኛ፤እነሱ በኔ አነጋገር በሚፈጠር ቀልድ ነበር። ፤ተከባብረን እየኖርን እያለ አንድ ቀን”ንጉሰ ቢዚህ እየመጡ ነው ፤ብር ይሰጣሉ ና እንሩጥ አሉኝ።መጀመሪያ ተጠራጠርሀ፤በኋላ አገሩ ሁሉ ሲሮጥ እኔም ከነቆመጤ፤እንደ እረኝነት ዘመኔ ስከንፍ እነሱ አልደረሱብኝም ነበር፤ በኋላ ከነቆመጥ መቅረብ አይቻልም ሲሉኝ ፤አስቀምጬ እንደሁሉም ተሰለፍሁ። የአደግሁበት ሁኔታ እንኳንስ ከንጉስ ፊት ከአረጋዊ ፊት በድፍረት አይቀረብምና እንደተዋጊ በሬ አቀርቅሬ ሄጄ ብሯን ተቀብየ መጣሁ እንጂ ፤ከማን እጅ እንደተቀበልሁ አላስታውስም።ብሩ የጃንሆይ እንደሆነ ጥርጥር የለውም፤ይህ ትዝታ ነው ዥው አድርጎ ወስዶኝ የነበረ።ያ ውለታ!

ወደ ዋናው ነገር ስንመለስ ፤ዝግጅቱ የተዋጣለት ነበር።ለዝግጅቱ፤በእለቱ የተገኙት ሁሉ ምስጋና ይገባቸዋል።

ከሁሉም በበለጠ የሚከተሉት ልዩ ምስጋና ይገባቸዋል፡

1.ከጉዞው መነሻ ጀምሮ፤እስክምንመለስ ድረስ፤እኛን በማዝናናት፤ፎቶግራፍ በማንሳት ያኩሩን ሁለቱ ትንታጎች፤ሀብታሙና ሲሳይ፤

2.ኪነጥበባዊ እውቀትታቸው፤የእነሱ ብቻ ሳይሆን የሕዝብ መሆኑንና ፤በአድዋ ጦርነት ግዜ የኪነጥበብ ሙያ ምን እብደነበረ በተግባር ያሳየች እህትና ሁለቱ ወንድሞች( አንዱ አምሳያየ)፤

3.ሚዲያ በየደሜዳው በበዛበት ዘመን ፤በተግባር ግን ብዘወች በማይታዩበት ወቅት በኢትዮጵያ ጉዳዮች ከመዘገብ አቋርጦ የማያውቀው የኢትዮጵያን ትሩቡን(Ethiopian tribun, Endex?)እጅግ የሚያኮራ ተግባር ያለርፍት እያከናወነ ያኮራ በመሆኑ

4.ራሔል ልጄቿን በሚያስደንቅ ሁኔታ አማርኛ አስተምራ፤ያን የመሰለ ዝግጅት ማቅረባቸው እጅግ የምታኮራ አድርጔታል።

4.ወ/ሮ ብርሀን ዳኜ፤ይህን ዝግጅት ከመጀመሪያው አንስተው በማስተባበር በመምራት አኩሪ ተግባር በማከናወናቸው፤የእለቱ እቴጌ ጣይቱ ቢበሉ የነበሩ ሁሉ የሚስማሙ የመስለኛል።ከዚህ በተጨማሪ በታላቁ ሩጫ ያገኙትን ሜዳሊያ በሁላችን ፊት ለራሔል በማበርከታቸው በጣም ተደንቀናል።

የፌር ፊልድ ሀውስ(Fair Field House) ምስጢር።

ስለዚህ ቀ.ኃ.ስ የነበሩበትን ታሪካዊ ቦታ ለመዘገብ በባለሙያ እንጁ እንዱህ አራምባና ቆቦ በሆነ መልክ ማቅረብ ድፍረት ስለሆነ፤የአዋቂወች እያለህ እይልሁ እሰናበታለሁ።
ኢትዮጵዊያን ምሁራን አላችሁ?
አለን ካላችሁ ሳትውሉ ሳታድሩ ፊታችሁን ወደ ባዝ እንድታዞሩ ከታላቅ አክብሮት ጋር እጠይቃለሁ ።
በተለይ ንጉሳችን በከፈቱ ትልቅ ተቋም አ.አ ዩንቨርሲቲ የተማራችሁ፤
በኋይለ ስላሴ አምላክ ውለታ ከፋይ ሁኑ።አንድ ግዜ ግንኙነት ከጀመራችሁ በኋላ የቅ.ኅ.ሥን መኖሪያ የኛ ብቻ ሳይሆን የአለም ሙዚየም እንደምታደርጉት ጥርጥር የለውም።
አድራሻው
Fairfield House,Kelston Road,Bath,BA1 3QJ
ሲሆን ሌላውን ከመገናኛ መረቡ(website) ማግኘት ይቻላል።

በመጨረሻም የከርሞውን (127ኛውን) የአድዋ የድል ቀን ለማክበር ሁሉም የሚችለውን አሁን በማድረግ ዝግጅቱ መጀመር ይገባዋል፤ይህ ሁሉ ወገን ባለበት በተመሳሳይ ቀን ቢያንስ በ4 ትልልቅ የዩኬ ከተማወች ለማክበር ከሚመለከታቸው ሁሉ ጋር የዝግጅት ምክክር ይጀመር።

አምላክ ኡትዮጵያችንና ሕዝባችንን ከክፉ ይጠብቅልን!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *