27 የክልል እና የተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ድምጽ የሚሰጠው ጷግሜ 01 ቀን 2013 ዓ.ም ይሆናል፡፡

ምርጫ2013

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 3 ቀን 2013 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ ትላንት መግለጫ መስጠቱ ይታወሳል። ዛሬ ላይ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።

በዚህም በተለያዩ ምክንያቶች ሰኔ 14 ድምጽ መስጠት የማይቻልባቸው አካባቢዎችን ገልጿል። በእነዚህ አከባቢዎች ምርጫው ጳጉሜ 1 የሚካሄድ ይሆናል ተብሏል።

እነዚህም፦

– ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል – መተከል፣ ሺናሻ ልዩ፣ ካማሽ እና ዳለቲ

– በኦሮሚያ ክልል -ቤጊ፣ ሰኞ ገበያ፣ አያና፣ገሊላ፣አሊቦ፣ጊዳሚ፣ ኮምቦልቻ

– አማራ ክልል-ማጀቴ (ማኮይ)፣ አርጎባ ልዩ፣ ሸዋሮቢት፣ ኤፌሶን፣ ጭልጋ 1፣ ጭልጋ 2፣ ላይ አርማጭ፣ አንኮበር

– ደ/ብ/ብ/ህ ክልል – ሱርማ ልዩ ፣ ዲዚ ልዩ፣ ቀይ አፈር መደበኛ፣ ማጀት መደበኛ፣ ሸኮ ልዩ፣ ቴፒ

– ሐረሪ ክልል – ጀጎል ልዩ ፣ ጀጎል መደበኛ ናቸው።

በተጨማሪም የድምጽ መስጫ ወረቀቶች ላይ ያጋጠሙ ችግሮችን አስመልክቶ በፍጥነት ህትመት ሊከናወንባቸው የሚችልባቸውን መንገዶችን በመፈለግ ትላንት አስታውቆት የነበረውን 32 የምርጫ ክልሎች ወደ 27 ዝቅ ማለቱን ገልጿል።

በዚህም መሰረት በነዚህ 27 የክልል እና የተወካዮች ምክር ቤት የምርጫ ክልሎች ድምጽ የሚሰጠው ከላይ በተጠቀሰው ጷግሜ 01 ቀን 2013 . ይሆናል።

Ethiopian Tribune editor

Learn More →

Leave a Reply

Your email address will not be published.