የዚህ ዐመት ፳፻፲፫ ልዩ የበጎ ሰው ሽልማት ተሸላሚ ፀሀፊ ትዕዛዝ አክሊሉ ሀብተወልድ ሆነዋል::

በዘንድሮው የበጎ ሰው ሽልማት ትዕዛዝ ስለ ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ መድረክ የፈጸሙት ጀብድ ከታሪክ ማህደራቸው ተነቧል። በዲፕሎማሲው የሠሩት ታሪክ መቼም አይዘነጋም ተብሏል።

አቶ አምዴ አካለወርወቅ የፀሀፊ ትዕዛዝ የወንድም ልጅ ሲሆኑ፤ “በህይወት እያለሁ አጎቴን በዚህ ደረጃ ሲከበር ከማየት በላይ ደስታ የለም” ሲሉ ተናግረዋል።

የጀብደኛውን ሀገር ወዳድ ዲፕሎማት ፀሀፌ ትዕዛዝ አክሊሉ ሃብተወልድ ንግግሮችን ለማስታወሻነት ተናግረዋል። ዛሬም እኚህ አንጋፋ ሰው በክብር በመነሳታቸው ደስተኞችም ነን ብለዋል።

ሽልማቱንም የዕለቱ የክብር እንግደ ፕሬዝዳምት ሳህለወርቅ ዘውዴ ሰጥተዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published.