ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ የኢትዮጵያ ቅርሶች ለንደን ለሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተመለሱ

0
0 0
Read Time:2 Minute, 35 Second

ቅርሶቹ ከአንድ መቶ ሀምሳ ሶስት አመት በፊት ከመቅደላ ተዘርፈው የተወሰዱ መሆናቸውን በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል ፡፡

በአፄ ቴዎድሮስ ዘመን ጦርነት ላይ ይጠቀሙበት የነበረ የጦር ጋሻ ፣ ከቆዳ የተሰራና በእጅ የተጻፈ የብራና መፅሀፍ ቅዱስ እሰከነመያዣው፣ ትልቅ እና አነስተኛ መስቀሎች ፣ ጽዋ የሚወሰድበት ዋንጫ ከነማንኪያዎቹ፣የጳጳስ አክሊል ከቀንድ የተሰሩና በብር የተለበጡ የቀንድ ዋንጫዎችን ከነመስቀሉ በትላንትናው እለት ኤምባሲው ተረክቧል ፡፡

ቬሄራዜድ በመባል የሚታወቀው የዩናትድ ኪንግደም የበጎ አድራጎት ድርጅት ከለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጋር በቅርሶቹ ዙሪያ ወራትን የወሰዱ ድርድሮችን እና ለሽያጭ ቀርበው የነበሩትን ከገበያ እንዲነሱ በማድረግ ቅርሶቹ ለባለቤታቸው የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲመለሱ ውሳኔ ላይ መደረሱን በርክክቡ ወቅት ላይ ተገልጿል።

ለንደን በሚገኘው አቴናም በተባለና የዩናይትድ ኪንግደም ልሂቃን ክለብ በተካሄደ የርክክብ ስነስርአት ላይ በለንደን የኢትዮጵያ አምባሳደር ተፈሪ መለሰ እንደተናገሩት ቬሄራዜድ በጎ አድራጎት ድርጅት ከኤምባሲው ጋር በመተባበር ላደረገው ሰፊ ጥረት ምስጋና በማቅረብ ፣እነዚህ የሀገር ሀብቶች ከቅርስነት በላይ የኢትዮጵያን የጀግንነትና የሀይማኖት ታሪኮች ለትውልድ ጽኑ የሆኑ ማስታወሻዎች በመሆናቸው ኢትዮጵያዊያን እራሳችንን መልሰን እንድናገኝ የሚረዱን መለያዎቻችን ናቸው ብለዋል ፡፡

የኢትዮጵያ ህዝብ አኩሪ የሆነ ጥንታዊ ና ገናና ታሪክ ያለው አንድነቱን ጠብቆ ለመኖር የቅርሶቹ ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

ቅርሶቹ ለሃገራችን መንፈሳዊ ፣ታሪካዊ ና ባህላዊ እሴቶች ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ ሲሆን ሌሎች በዘረፋ የተወሰዱ ቅርሶቻችን በዚህ መልክ በድርድር ለማስመለስ አስተዋፅኦ እንዳለው ያመለከተቱት አምባሳደር ተፈሪ በቀጣይነት በእንግሊዝ ከመቅደላ የተዘረፉ ቅርሶች እንዲመለሱ ከፍተኛ ድርድሮች እየተደረጉ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያና በእንግሊዝ ታሪካዊ የጋራ ግንኙነት ላይ መቅደላ የፈጠረውን መጥፎ አጋጣሚ በአዎንታዊነት ለማደስ እነዚህ በህገወጥ መንገድ የተዘረፉ ቅርሶች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ መደረጉ ፋይዳው የላቀ ነው ብለዋል፡፡

የቬሄራዜድ በጎ አድራጎት ድርጅት ዋና ስራ አስፈጻሚ ጣሂር ሻህ በበኩላቸው ከቅርሶቹ መካከል የተወሰኑት በኤምባሲውና በሚመሩት በጎ አድራጎት ድርጅታቸው አማካይነት ለሽያጭ ከቀረቡበት የታገዱ መሆናቸውን ገልፀው፣ እነዚህ ቅርሶች ለኢትዮጵያ ህዝብ ያላቸው ፋይዳ ትልቅ በመሆኑ ለባለቤቱ እንዲመለሱ መደረጋቸው የሁለቱን ሀገሮች የቆየ ግንኙነት ወደተሻለ ጥልቅ ትስስር የሚያሻግር ነው ብለዋል፡፡

ዶ/ር አሉላ ፓንክረስት በርክክብ ስነስርአቱ ላይ ተገኝተው እንደተናገሩት” ይህ ቀን ለኢትዮጵያ የአንድነት ታሪክ አዲስ ምእራፍ የሚከፍት ነው ፤ጥንታዊ ታሪክ ያላትን ሀገር ቅርሶቿን በአግባቡ እንዲመለሱ ማድረግ መቻሉ የሃገራቱን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ይበልጥ የሚያጠናክር ነው” ብለዋል ፡፡

ገጣሚና የማንቼስተር ዩኒቨርስቲ ቻንስለር ለምን ሲሳይ በበኩሉ “በትውልድ ኢትዮጵያዊ መሆኔ ያኮራኝ እለት ቢኖር ዛሬ ነው ፣ ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊያን እንኳን ደስ አለን” በማለት ታሪክ የሀገር መሰረት በመሆኑ የዛሬው ስነስርአት ለኢትዮጵያ ሌላ ምእራፍ ነው በማለት ተናግሯል፡፡

የተመለሱት ቅርሶች በትላንትናው እለት ወደ በለንደን የኢትዮጵያ ኤምባሲ የገቡ ሲሆን በቅርቡ ወደ ሀገር ቤት እንደሚላኩ ተገልጿል፡፡

Ethiopian artefacts that were looted at the Battle of Maqdala in 1868 officially handed over to Embassy by the Scheherazade Foundation.

The items, which include a handwritten Ethiopian Bible, crosses, an Imperial shield, a set of beakers, an icon and a magical scroll, were procured by the Scheherazade Foundation through a Dorset-based auction house, and private dealers in mainland Europe.

Speaking on the occasion, at a private reception held at the prestigious Athenaeum Club in London, Ambassador Teferi Melesse Desta thanked the Foundation for their work in acquiring the precious items and renewed calls for museums, collectors, and holders of Maqdala heritage to return these items to their rightful home.

Founder of the Scheherazade Foundation, Mr Tahir Shah, on his part, said he knew what the return of the objects would mean to the people of Ethiopia and that through his foundation, he hopes to build bridges between the two nations.

The Embassy will now make arrangements for the items to be returned to Ethiopia in due course.

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *