የኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ ተወልደ ገብረ ማርያም ከጤናቸው ጋር በተያያዘ በገዛ ፍቃዳቸው ከኃላፊነት መልቀቃቸውን አረጋግጧል።

በሌላ በኩል የቀድሞ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የነበሩት አቶ ግርማ ዋቄ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦርድ ሰብሳቢ ሆነው በቅርቡ መሾማቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል።

አቶ ግርማ ፤ በአየር ትራንስፖርት ዘርፍ የካበተ ልምድ ያላቸው ሲሆኑ አየር መንገዱን ዛሬ ለደረሰበት ስኬት መሰረት በጣለ መልኩ ለ7 ዓመታት ዋና ስራ አስፈፃሚ ሆነው አገልግለዋል።

ቦርዱ በቅርቡ አዲሱን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ እና የአቶ ተወልደ /ማርያምን ተተኪ ያሳውቃል ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published.