ምኒልክን እንጠላለን ርስቱን ግን እንወዳለን ማለት አያዋጣም!

0
0 0
Read Time:6 Minute, 18 Second

Achamyeleh Tamiru
አቻምየለህ ታምሩ

ሰማዩንም ምድሩንም የኛ ነው የሚሉ ኦነጋውያንን እሹሩሩ ማለቱ ማብቃት አለበት። «ዳግማዊ ምኒልክን ውደዱ፣ ኢትዮጵያዊ ናችሁ፣ ስለወደፊቱ ብቻ እንስማማ» እያሉ ማባባሉ ምንም ፋይዳ የለውም። «ዳግማዊ ምኒልክን እንጠላለን» ፣ «ኢትዮጵያ አይደለንም» ወዘተ…ሲሉ የሚውሉ ሰዎችን «በወረራ የያዛችሁትን የዳግማዊ ምኒልክ ርስትም አብራችሁ ጥሉና በወረራ የያዛችሁትን የምኒልክ ርስት ልቀቁ»፣ «የኢትዮጵያን ታሪክ ከጠላችሁ አገራችሁ ኢትዮጵያ አይደለም» ሊባሉ ይገባል።

ኦሮምያ የሚባለው በኢትዮጵያ እምብርት ላይ የበቀለው እባጭ ኦሮሞ ኢትዮጵያን ወረራ ከመጀመሩ ከ1522 ዓ.ም. በፊት በተለያዩ የኢትዮጵያ የጥንት አውራጃዎች የተከፋፈለና የዳግማዊ ምኒልክ አባቶች ርስት ነበር። ኦሮሞ በዚህ የኢትዮጵያ ክፍል እንደ ዋርካ የተንሰራፋው ከ1522 ዓ.ም. ጀመሮ በየስምንት ዓመቱ በአባዱላ እየተመራ ባካሄደው ወረራ የዐፄ ምኒልክ አባቶችን አጥፍቶ፣ ማንነታቸውን ቀይሮ፣ የዘር ማጥፋት አካሂዶና ከርስታቸው አፍልሶ ነው። ኦሮሞ የዐፄ ምኒልክን አያቶች ርስት በመውረር እንደተንሰራፋ ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ዘመን ጀምሮ ያለውን የኢትዮጵያ ነገሥታት ትውልድ ታሪክ ብቻ ወስጄ እንደሚከተለው አስረዳለሁ።

ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመውረሩ ከስድስት መቶ ዓመታት በፊት ዘይላ የኢትዮጵያ ክርስትያኖች ምድር እንደነበር የታሪክ ምስክርነታቸውን የሰጡን የዘመኑ የአረብ ተጓዦች ናቸው። ለዚህ ማስረጃ የሚፈልግ ቢኖር ሶማሌው ዶክተር ዐሊ አብዲራህማን ኸርሲ እ.ኤ.አ. በ1977 ዓ.ም. በካሊፎርኒያ ዩኒቨርሲቲ “The Arab Factor in Somali History: The Origins and Development of Arab Enterprise and Cultural Influences in the Somali Peninsula” በሚል ባቀረበው የሦስተኛ ዲግሪ ማሟያ ጥናቱ፣ የ10ኛ እና የ11ኛው መቶ ክፍለ ዘመን የዐረብ ተጓዦች የመዘገቧቸውን የታሪክ ማስረጃዎች በመጥቀስ ገጽ 117 ላይ፡- “Tenth and eleventh century Arab sources all describe Zaila as an Abyssinian Christian city which traded peacefully with the Yamani (sic) ports across the Red Sea.” በሚል ያቀረበውን ያንብብ።

ሐረርጌ ኦሮሞ ኢትዮጵያን ከመውረሩ ከሶስት መቶ ዓመታት በፊት የአማራ፣ የአርጎባ፣ የብሌን፣ የዝይ፣ ወዘተ እንደነበርና የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት “መኳንንት” የሚል ማዕረግ ሰጥቶ አስተዳዳሪ ይሾምበት የነበረ የኢትዮጵያ አውራጃ እንደነበር የታላቁን ንጉሥ የአምደ ጽዮንን ታሪከ ነገሥት ያነቧል። ለዚህ ማስረጃ የሚሻ ቢኖር እንግሊዛዊው የታሪክ ምሑር ፕሮፌሰር ጆርጅ ሐንቲንግፎርድ “Glorious Victories of ‘Amda Seyon, King of Ethiopia” በሚል ርዕስ በ1958 ዓ.ም. ወደ እንግሊዝኛ ተርጉመው ያሳረሙትን የዐፄ አምደ ጽዮንን ታሪከ ነገሥት ገጽ 78 ይመልከት።

ወለጋ ከኦሮሞ ወረራ በፊት የጥንት ስሙ ቢዛሞ ይባል እንደነበር ደግሞ የጻፉት ትምህርት የላቸው ተብለው ባላዋቂዎች የሚሰደቡት «ደብተራ» የታሪክ ጸሐፊዎች ሳይሆኑ የሎንዶን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ ምሩቅ ኦሮሞው ባላባት ልጅ ይልማ ደሬሳ ናቸው። ልጅ ይልማ ደሬሳ ከጣሊያን ወረራ በፊት ከሎንዶን ስኩል ኦፍ ኢኮኖሚክስ በዲግሪ የተመረቁ ሲሆኑ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ለብዙ ዓመታት የገንዘብ ሚኒስትር ነበሩ።

ልጅ ይልማ የወለጋው ባላባት የደጃዝማች በከሬ ጎዳና ኦሞ ፋሮ ሲኒካ ኘአ ዶሮ የልጅ ልጅ ናቸው። የልጅ ይልማ አያት ደጃዝማች አመንቴ በከሬ ይባላሉ። የደጃዝማች አመንቴ በከሬ ልጅ ደግሞ የአቶ ይልማ ደሬሳ አባት ብላታ ደሬሳ አመንቴ ናቸው።
ልጅ ይልማ ደሬሳ በ1959 ዓ.ም. «የኢትዮጵያ ታሪክ በአሥራ ስድስተኛው ክፍለ ዘመን» በሚል ባሳተሙት የታሪክ ጥናታቸው ገጽ 17 ላይ የዛሬው ወለጋ በ17ኛው መቶ ክፍለ በኦሮሞ ተወርሮ ስሙ ወደ ወለጋ ከመቀየሩ በፊት ጥንተ ስሙ ቢዛሞ ይባል ነበር። በግዛቱም አማራ፣ ጋፋት፣ ካፋ [እናርያና አንፊሎ] የሚባሉ ነገዶች ይኖሩበት የነበረ የኢትዮጵያ አውራጃ ነበር።

ባሌ ከጥንት ጀምሮ የአማራ ጭምር ርስተ ምድር የነበረ የጀግናው የአዛዥ ደገልሀን አጽመ ርስት፤ ግራኝ አሕመድ «የባሌ አበሾች ሰይጣኖች ናቸው» ሲል የመከሰረላቸው የባሌ ነጋሹ የትግሬው የራስ ተክለ ሃይማኖት ግዛትና ከግራኝ አሕመድ ጋር ሲዋጉ ለአገራቸውና ለሃ ይማኖታቸው የወደቁት የባሌ ተወላጆች የነ ራስ ነብያንትና የነ አዛዥ ፋኑኤል መቃብር ነው። ደዋሮ [የዛሬው ምዕራብ ሐረርጌ] የልብነ ድንግል የጦር አዝማች የነበረው የቢትወደድ በድል ሰገድ ርስት ነው። ዳሞትና ቢዛሞ [የዛሬው ወለጋ] በሽምግልና እድሜው ግራኝን ለመፋለም ዘምቶ አስደማሚ ተጋድሎ ያደረገው የልብነ ድንግል የጦር አዛዥ የአዛውንቱ የራስ ወሰን ሰገድና የጀግናው ልጁ የባህር ሰገድ እትብት የተቀበረበት አገራችን ነው። ፈጠጋር[ የዛሬው አርሲ] እነ ነጋሽ ተክለ ሐዋርያት ከግራኝ ጋር ሲፋለሙ የወደቁበት ያያቶቻችን ርስት ነው።

ወደ ርስት ዝርዝር ስንመለስ ኦሮሞ በወረራ ባጠፋቸውና በሰፈረባቸው የኢትዮጵያ አውራጃዎች ሁሉ የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክን አያት ቅድመ አያቶች እናገኘዋለን። ከምድር ወገብ ሶስት ዲግሪ እስከ አስራ ስምንት ዲግሪ፤ ከግሪንዊች ሜሪዲያን አስራ ሶስት እስከ አርባ ስምንት በመለስ የነበረውን የኢትዮጵያ መሬት ያስተዳደሩት ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ኢትዮጵያን ከ1314-1344 ዓ.ም. ያስተዳደሩት የዐፄ ዐምደ ጽዮን የልጅ ልጅ ናቸው። ዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ከ1426 – 1460 ዓ.ም. ኢትዮጵያን ያስተዳደሩ ታላቅ ንጉሠ ነገሥት ናቸው። ዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ የተወለዱት ከአባታቸው ከዐፄ ዳዊት እና ከእናታቸው ንግሥት ክብረ እግዚ በ1391 ዓ.ም. ሲሆን የተወለዱት ከአዋሽ ወንዝ አጠገብ ትገኝ በነበረው ትልቅ ተብላ በምትጠራው ቦታ ፈጠጋር አውራጃ ውስጥ ነው። ፈጠጋር ከኦሮሞ ወረራ በኋላ የጥንት ስሙ ተቀይሮ አርሲ ተብሏል። የዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ እናት ንግሥት ክብረ እግዚ የፈጠጋር ባላባት ልጅ ናቸው።

ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ በኋላ ኢትዮጵያን ከ1460-1470 ዓ.ም. ያስተዳደሩት ልጃቸው ዐፄ በእደ ማርያም ናቸው። ዐፄ በእደ ማርያም የተወለዱት በ1440 ዓ.ም. ሲሆን እናታቸው እቴጌ ጽዮን ሞገሷ የደዋሮ ገዢ የነበሩት የጋራድ አሕመድ ልጅ ናቸው። ደዋሮ ከኦሮሞ ወረራ በኋላ የጥንት ስሙ ተቀይሮ ምዕራብ ሐረርጌ ሆኗል።ከዐፄ በእደ ማርያም በኋላ ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት የመጀመሪያ ልጃቸው ዐፄ እስክንድር ናቸው። ዐፄ እስክንድር ኢትዮጵያን ያስተዳደሩት ከ1471-1487 ዓ.ም. ሲሆን እናታቸው ንግሥት ኢሌኒ የደዋሮ ጋራድ ልጅ ናቸው። ዐፄ እስክንድር ከሞቱ ከአንድ ዓመት በኋላ ኢትዮጵያን ማስተዳደር የጀመሩት ወንድማቸውና ሁለተኛው የዐፄ በእደ ማርያም ልጅ የሆኑት ዐፄ ናዖድ ናቸው። ዐፄ ናዖድ ኢትዮጵያን የገዙት ከ1486-1500 ዓ.ም. ሲሆን እናታቸው የዳዋሮ ገዢ ልጅ የሆኑት እቴጌ ናዖድ ሞገሷ ናቸው። ከዐፄ ናዖድ በኋላ የነገሡት ዐፄ ልብነ ድንግል ሲሆኑ ኢትዮጵያን ከ1501-1532 ዓ.ም. ገዝተዋል።

ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ጀምሮ እስከ ዐፄ ልብነ ድንግል ያሉት የኢትዮጵያ ነገሥታት ሁሉ ትውልዳቸው ከደዋሮ [ከኦሮሞ ወረራ በኋላ ምዕራብ ሐረርጌ የሆነው] እና ከፈጠጋር [ከኦሮሞ ወረራ በኋላ አርሲ የሆነው] ይሳባል። ይህ ማለት ቀደም ብዬ ለዘረዘርኳቸው የኢትዮጵያ ነገሥታት ደዋሮ[ ከኦሮሞ ወረራ በኋላ ምዕራብ ሐረርጌ የሆነው] እና ፈጠጋር [ከኦሮሞ ወረራ በኋላ አርሲ የሆነው] ያባቶታቸው ርስት ነው ማለት ነው። ደዋሮና ፈጠጋር ከዐፄ ዘርዓ ያዕቆብ ጀምሮ እስከ ዐፄ ልብነ ድንግል ድረስ ያሉት የኢትዮጵያ ነገሥታት አባቶች ርስት በነበረበት ወቅት ኦሮሞ ገና የገዳ ስርዓትና ወረራ አልጀመረም ነበር።

እንቀጥል! ዐፄ ልብነ ድንግል ከወለዷቸው ልጆች መካከል የመጨረሻው ልጃቸው አቤቶሁን ያዕቆብ ይባላሉ። አቤቶሁን ያዕቆብ አቤቶሁን ሥግወ ቃልን የወለዱ ሲሆን አቤቶሁን ሥግወ ቃል ወረደ ቃልን፣ ወረደ ቃል ደግሞ ነጋሲን ወልደዋል። አቤቶሁን ነጋሲ ሥግዎ ቃል በኢማም አሕመድ ጦርነት የተለያዩትን የደቡቡን የነዐፄ ልብነ ድንግል አባቶች ርስት ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጋር ወደቀድሞው አንድነቱ ለማምጣት በዶቃቂት የተቋቋመው የሸዋ ስርዎ መንግሥት መስራች ናቸው። ከአቤቶሁን ነጋሲ በኋላ ሸዋ የተመሰረተውን ስርዎ መንግሥት የመሩት ልጃቸው አቤቶሁን አብዬ ናቸው።

ከአቤቶሁን አብዩ በኋላ የገዙት ልጃቸው መርድ አዝማች አምሐ ኢየሱስ ናቸው። ከአምሐ ኢየሱስ በኋላ ግራኝ ያጠፋቸውን የኢትዮጵያ ክፍሎች ለማቅናት ሸዋ ላይ የተመሰረተው ሥርዎ መንግሥት መሪ ልጃቸው አስፋው ወሰን ናቸው። ከመርድ አዝማች አስፋው ወሰን በኋላ ሸዋን የገዙት ልጃቸው መርድ አዝማች ወሰን ሰገድ ናቸው። ከመርድ አዝማች ወሰን ሰገድ በኋላ ሸዋንና የተቀሩትን ኦሮሞ የወረራቸውን የነዐፄ ልብነ ድንግል አባቶች ርስት በማስመለ የገዙት ልጃቸው ንጉሥ ሣህለ ሥላሴ ናቸው። ከንጉሥ ሣህለ ሥላሴ በኋላ በስርዎ መንግሥቱ የተሾሙት ልጃቸው ንጉሥ ኃይለ መለኮት ናቸው። ከንጉሥ ኃይለ መለኮት በኋላ ሸዋን [ከዐፄ ቴዎድሮስ ቤተ መንግሥት ከወጡ በኋላ] እና የአባቶቻቸው የነዐፄ ልብነ ድንግል ርስት የሆነውን የዛሬውን ኢትዮጵያ ምድር ያስተዳደሩት ልጃቸው ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ናቸው።

ከፍ ብዬ ከዘረዘርሁት እንደተመለከተው ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ ትውልዳቸው ከዐፄ ልብነ ድንግል ልጅ ከአቤቶ ያዕቆብ ይመዘዛል። ከዐፄ ልብነ ድንግል ደግሞ ትውልዳቸው ከደዋሮ [ ከኦሮሞ ወረራ በኋላ ምዕራብ ሐረርጌ የሆነው]፣ ከሐድያ [የዛሬውን ባሌ በከፊል ያካትታል] እና ከፈጠጋር [ከኦሮሞ ወረራ በኋላ አርሲ የሆነው] እንደሆነ ተመልክተናል። ይህ ማለት ኦሮሞ ነባሩን ሕዝብ አፍልሶ የያዘው ደዋሮና ፈጠጋር የዳግማዊ ዐፄ ምኒልክ አባቶች ርስትና ቅድመ አያቶቻቸው የተወለዱባቸውና የወለዱባቸው አውራጃዎች ነበሩ ማለት ነው። ለዚህም ነበር ዳግማዊ ዐፄ ምኒልክም ሆነ ከሳቸው በፊት የነበሩት በግራኝ አሕመድ ጦርነት የተለያዩትን የደቡቡን የነዐፄ ልብነ ድንግል አባቶች ርስት ከሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ጋር ወደቀድሞው አንድነቱ ለማምጣት በሸዋ የተቋቋመው ስርዎ መንግሥት መሪዎች ሁሉ ወደ ደቡቡ የኢትዮጵያ ክፍል ማለትም ወደ ሐረርጌ፣ አርሲና ባሌ ሲዘምቱ «የአባቶቼን አገር ላስመልስ ነው» ይሉ የነበረው።
እንግዲህ! ዐፄ ምኒልክን የሚጠሉ ሰዎች ከዛሬው ኢትዮጵያ ውጭ ተነስተው የወረሯቸውንና እንደ ዋርካ ተስፋፍተው የያዟቸውን የዳግማዊ ምኒልክ አያቶች ርስትና አውራጃዎች የሆኑትን እነ ደዋሮን፣ባሊን፣ ፈጠጋር፣፥ ቢዛሞን፣ እናርያንና የጥንቱን ዳሞትን አብረው መጥላት አለባቸው። «ወንድ እወዳለሁ፤ ግን ጭኔን ያመኛል» እንዳለችው አይነት ግራ ገባት ሴት አይነት ምርጫ አይሰራም። ኦነጋዊ ሁሉ ዳግማዊ ምኒልክን እንዲወድ አይገደድም። ዳግማዊ ምኒልክን የሚጠላ ግን የዳግማዊ ምኒልክን ርስት መልቀቅና ወደ መጣበት መሄድ አለበት። የጥንቱን ኢትዮጵያን ታሪክ የሚጠላ አገሩ ኢትዮጵያ አይደለችም፤ ስለሆነም አገራችንን ይልቀቅ።
ባጭሩ ዳግማዊ ምኒልክን እንጠላለን እያሉ የዳግማዊ ምኒልክን ርስት ግን እንወዳለን ብሎ ነገር የለም! ዳግማዊ ምኒልክን እንደጠላህ ሁሉ በገዳ ተደራጅተህ በየስምንቱ ዓመቱ እየወረርህ የያዝኸውን የዳግማዊ ምኒልክን ርስትም ጥላና በወረራ ይዘህ እስካሁን ለተጠቀምህበት አፈላማህን ከፍለህ ምድሩን ላፈለስሀቸው ለባለቤቶቹ ለቀህ አገሬ ወደምትለው ሂድ! ምኒልክን ጠልተህ በምኒልክ ርስት ላይ ምን ትሰራለህ?

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *