ልዑል ሚካኤል መኮንን ቅን ❤ ልብ የሆኑትን ጠቅላይ ሚንስቴርን አመስገኑ
ልዑል ሚካኤል መኮንን በ “የኢትዮጵያ ልክ ከግቢ እስከ ሀገር”በተሰኘው የጠቅላይ ሚኒስተር ዐብይ አህመድ ፊልም ተመርኮዞ ያጫወቱን ታሪካዊ ዋቢዋች። ቅን ❤ ልብ ናቸው ጠቅላይ ሚኒቴራችን።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን ይፋ አደረጉ ******************************** ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የገበታ ለሀገር ፕሮጀክትን ዛሬ ይፋ አድርገዋል። የገበታ ለሀገር ፕሮጀክት ቀደም ሲል በባለሀብቶች እና ተቋማት በተሰበሰበ ገንዘብ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በተለያዩ ቦታዎች የተሠሩ የሸገር ፕሮጀክቶችን ወደ ክልሎች ለማስፋት ያለመ ነው። ፕሮጀክቶችን በአገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች እና የቱሪዝም መዳረሻዎች ለማስፋት ጥናት መደረጉም ተገልጿል። በዚህም ጥናት መሠረት በመጀመሪያ ዙር በሦስት ቦታዎች ላይ ተግባራዊ ለማድረግ ቦታዎች መመረጣቸው ታውቋል። እነዚህም በአማራ ክልል፣ ጣና ሐይቅ ምዕራባዊ ዳርቻ የሚገኘው ጎርጎራ፣ በአሮሚያ ክልል፣ ደቡብ ምዕራብ ሸዋ የሚገኘው ወንጪ ሐይቅ እና በደቡብ ክልል፣ ኮንታ የሚገኘው ኮይሻ ናቸው ተብሏል። ፕሮጀክቶቹ በቀጣይ አክሱም እና ላሊበላን ጨምሮ በርካታ ቦታዎች ላይ የሚከናወኑ መሆኑ ተገልጿል። ፕሮጀክቶቹ የግል ባለሀብቶችን ጨምሮ በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚኖሩ ሁሉም ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉባቸው እንደሚሆኑ ተገልጿል። ለዚህም ተሳትፎ የተለያዩ ፓኬጆች የተዘጋጁ ሲሆን፣ ለግል ባለሀብቱ ባለ 10 ሚሊዮን የከበረ ልዩ እራት (VVIP) እና ባለ አምስት ሚሊዮን ልዩ እራት (VIP) መዘጋጀቱ ተጠቁሟል። ሁሉንም ዜጋ ለማሳተፍ ደግሞ በኢትዮ-ቴሌኮም በኩል በአጭር ጽሑፍ መልእክት ባለ 5 እና ባለ 10 ብር ድጋፍ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል። በተጨማሪም በውጭ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን የሚሳተፉባቸው ፓኬጆች መኖራቸውም ተጠቁሟል። ከዚህ ባለፈ የተለያዩ የልማት አጋሮች፣ ዲፕሎማቶች እና ድርጅቶች የሚሳተፉባቸው ፓኬጆች እንደሚኖሩ ታውቋል።