አዲስ አበባ የመጀመሪዋ እንስት ከንቲባ ተሾመላት። ኦቦ ለማ መገርሳ ተተኩ።

0
0 0
Read Time:2 Minute, 0 Second
በቅርቡ በተነሳው አመጽ እና ሃይማኖትና ዘር ተኮር የዘርማጥፋት ጥቃት ብልጽግና መራሹ መንግስት በድርጅቱ ውስጥ የፖለቲካ ግምገማ በማድረግ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ቢሮ ማክሰኞ የሀገሪቱን የመከላከያ ሚኒስትርን ተክቶታል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከቅርብ ጊዜ የመከላከያ አዛዥ የነበሩትን ኦቦ ለማ መገርሳን ከበልጽግና ፓርቲ አግደው የቁም እስረኛ ማድረጋቸው ይታወቃል።

የአማራ ክልል ምክትል ፕሬዚዳንትና የቀድሞ አዴፓ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ የነበሩትንና ከእነ አምባቸው መኮንን (ዶ/ር) ግድያ በኋላ በመለስ ሥራ አመራር አካዴሚ ዋና ዳይሬክተር ተደርገው ቢሾሙም እንደማይፈልጉ በመግለጽ ሹመታቸውን ሳይቀበሉ የከረሙትን አቶ ዮሐንስ ቧያሌውን ደግሞ፣ የኢትዮጵያ የውጭ ግንኙነት ስትራቴጂክ ጥናት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል፡፡

የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፕሬስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ የነበሩትን አቶ ንጉሡ ጥላሁንን ደግሞ በቅርቡ በገዛ ፈቃዳቸው ኃላፊነታቸውን በለቀቁት የሕክምና ባለሙያው ዶ/ር ኤፍሬም ተክሌ ምትክ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው ተሾመዋል፡፡ 

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሯ ሒሩት ወልደ ማርያምን (ፕሮፌሰር) ሳሙኤል ሁርካቶ (ዶ/ር) የተኳቸው ሲሆን፣ እሳቸው ደግሞ በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማኅበራዊ ዘርፍ አማካሪ ተደርገው በቅርቡ ከብልፅግና ፓርቲ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባልነት በታገዱት ወ/ሮ ጠይባ ሐሰን ምትክ ተሾመዋል፡፡

በትናንትናው ዕለት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ሆነው የተሾሙት ወ/ሮ አዳነች ቃለ መኃላ ከፈጸሙ በኋላ የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው በተሾሙት የቀድሞ ምክትል ከንቲባ እንዳወቅ አብቴ (ኢንጂነር) ምትክ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የከተማ ልማት አማካሪና ቀደም ብሎም የከተማ ልማት ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ጃንጥራር ዓባይን በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የአገልግሎት ዘርፍ ኃላፊ ሆነው እንዲሾሙ አቅርበው አሹመዋል፡፡

ወ/ሮ አዳነች ቃለ መሃላ ከፈጸሙ በኋላ ባደረጉት ንግግር እንደገለጹት፣ በአገልግሎት አሰጣጥም ሆነ የአገርን ሀብት በማስተዳደር ግልጽ የሆነና ከሀብት ብክነት የፀዳ አሠራር ይከተላሉ፡፡ ምዝበራን ያስወገደ በታማኝነትና በቅንነት ላይ የተመሠረተ አሠራር በመዘርጋት እንደሚሠሩም ተናግረዋል፡፡ አገልግሎት አሰጣጣቸው ለሁሉም ዜጋ በሁሉም የከተማዋ መዋቅር በእኩል ዓይን እንደሚታየና የሕዝብ አገልጋይ በመሆን በተቻላቸው ሁሉ ተግባራዊ ለማድረግ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ የከተማን ድህነት ለማስወገድ፣ የኑሮ ውድነትን ለመቆጣጠር የከተማዋን ማኅበራዊ ዋስትና ማዕቀፎች ለማስፋፋትና ለማጠናከር እንዲሁም በከተማው የሚታየውን የቤት እጥረት ለመቅረፍ ልዩ አትኩሮት ሰጥተው እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡ የትኩረት አቅጣጫዎቹን  ይዘው የሚሠሩትን ሥራዎች ውጤታማ ለማድረግ የምክር ቤቱና የከተማው ነዋሪ ዕገዛ እንደሚያስፈልጋቸውም ወ/ሮ አዳነች ጠቁመዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባላት፣ የከተማው ነዋሪዎችና መላው ኢትዮጵያውያን ሀብታቸውና ቤታቸው የሆነችውን አዲስ አበባን እንደ ስሟ እንድታብብ፣ የተወጠኑና የተጀመሩ ሥራዎች ውጤታማ እንዲሆኑ ከጎናቸው ሆነው እንዲያግዟቸውም ጥሪ አድርገዋል፡፡ በሐሳብ፣ በምክር፣ በሙያና ሀብት ያለው በሀብቱ እንደሚያግዛቸውም ያላቸውን እምነት ወ/ሮ አዳነች ገልጸዋል፡፡ አዲስ አበባ ከተማ የቤተሰብ ቤት መሆኗን ማለትም ጫማ አፅጅ ወንድምና እህት፣ የቡናና ሻይ ሻጭ ወንድምና እህት፣ የታክሲ ረዳት፣ የባለሀብቱ፣ የምሁሩ፣ የአርሶ አደሩና በአጠቃላይ የለፍቶ አደሩ ከተማ በመሆኗ፣ ለሁሉም የምትመች ከተማ እንድትሆን በትጋት፣ በፍትሐዊነትና በቅን ማገልገል አብሮ መትጋትና መሥራት አስፈላጊ መሆኑን ወ/ሮ አዳነች ተናግረዋል፡፡ በሕዝቡ ዕገዛና በእግዚአብሔር ዕርዳታ ምኞታቸውና ህልማቸው ዕውን እንደሚሆንም ያላቸውን እምነት ገልጸዋል፡

source: Ethiopian Reporter
Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *