ቆይታ ከአቶ አለባቸው ደሳለኝ ጋር በኢትዮጵያ ዳያስፖራ ምክር ቤት ውስጣዊ አለመግባባት ዙሪያ…

0
0 0
Read Time:3 Minute, 0 Second

ታህሳስ 29 ቀን 2013 ዓ ም ከኢትዮጵያ ዳያስፖራ ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ ዙሪያ የሚያመለክተውን ለመዳሰስ የተደረግ ቃለ ምልልስ።

አቶ አለባቸው ደሳለኝ በታላቋ ብሪታኒያ የሚኖሩ መስራች አባል የሆኑበት የኢትዮጵያ ዳያስፖራ ምክር ቤት በገንዘብ ዙሪያ የመበታተን አፋፍ ላይ መሆኑን ምልክቶች የታያሉ።

ከ ፬፻ ሺህ የአሜሪካ ዶላር አስባስበው ለመን ተጣሉ!

በምስሉ ላይ እንደሚመለከትው ጎፈንድ ሚ የሚባለ ድህረ ገጽ እንደሚያመልክተው ሶስትመቶሲድሳ ዓምስት ሺህ ሁለትመቶሰላሣ የ አሜሪካ ዶላር እንደ ተሰበሰበ ያመለክታል።

ኸላይ የሚያመለክተው ደብዳቤ አንድ መቶሰድሳ ሺህ ዶላር ለኢትዮጵያ መንግስት እንደገባ የሚያመላክት ሲሆን ገንዘቡን ለማሰባሰብ የትሳተፉትን ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናት እና ታዋቂ ግለስቦችን ለማመስገን በድርጅቱ አርማ የተሰራ ምስል ነው

ከላይ በሚያሳየው ደብዳቤ መሰረት በቀርቡ ከተወግዱት ምክትል ሰብሳቢ እና የሪጅናል ኮ ኦርዲኔተር እና መስራች አባላት የተሰጠው መግልጫ ይህንን አስነበቦን ነበር…

”…በቅርቡ ከዕለተ ተዕለት ገጠመኝ እንደምንረዳው ጊዜ አቅጣጫ ያለው ይመስላል፦ ያለፈው ጊዜ ተመለሶ ላይመጣ ወደ ኋላ ይቀራል፣ የወደፊቱ ደግሞ ከፊትለፊት እየገሰገሰ ይመጣል። በዚህ ምክንያት የጊዜ ቀስት ካለፈው ወደ ወደፊቱ ያለማመንታት ይገሰግሳል። በዚህ ሁኔታ የሽማግሌዎች ጥረት በከፊል ተሳክቶ በከፊል ሳይሳካ ተጠናቀቀ ::

ሲዳ ከተነሳበት የህብረ ብሔር አደረጃጄት ይልቅ በዘርና በቲፎዞ ተበዎዘ የተግባር ምክር ቤቱን ሊመሩ ይችላሉ ብለን እምነት የጣልንባቸው አባሎቻችንን በአቶ ደምለው አንማው አስተባባሪነት ጥቂት ስም አጥፊዎችንና ህሌናቸውን ለጥቅም የሸጡ ግለሰቦችን ይዘው በማስተባበር አድማ በማስመታት ስራ አስፈፃሚውን ለሁለት በመከፋፈላቸው አብዛኛው የሲዳ ቦርዶፍ ዳይሪክተርስ አባላቶቻችንና የድርጅቱ መስራች አንዱ የሆኑት ስራ እስፈፃሚው ካፒቴን አብይ ከሲዳ ለቀቁ ::

በመቀጠል በርዶፍ ዳይሪክተርስ ሳይሰበሰብና መክርውበት ሳይወስኑ ም/ፕሬዝዳንቱንና የአለም አቀፍ ዳያስፖራ የውጭ ዘርፍ አደረጃጄት ሀላፊውን አባረናል በማለት ሕዝብንና የመንግስት ሀላፊዎችን የሚያሳስት ደብዳቤ በምሀበራዊ ሚዲያ በተኑ ::

እኛም ሲዳን በዚህ አይነት ለመበተን የታቀደው ስውር ሴራን በትኩረት ስንከታተል ስለነበር የሲዳ መስራች አባሎች ጉዳዩ ስላሳሰበን ከሲዳ መስራቾችና ከግሎባል አክቲቪስቶች ጋር በመመካከር ሲዳን ለማዳን ከፍተኛ እርብርቦሽ ማድረግ ጀመርን :: በዚህ ምክኒያት ሲዳን የማዳን ጠንካራ አቋም የወሰዱት ቆራጥ ኢትዮጵያዊያኖች ርብርብ አድርገው የአቶ ደምለው አንማው ሴራ አከሸፉት::

በመጨረሻም ሲዳ በተጠናከረ አስተማማኝ መሰረት ላይ መቆሙን ሲያውቁ የስም ማጥፋትና የሲዳ ቦርድ ኦፍ ዳይሪክተርስ ያልወሰነውን ደብዳቤ ለመንግስት አካላት መበተን ጀመሩ ::

ይህ ህገወጥ ደብዳቤ የተግባር ምክር ቤቱን ለመከፋፈል በአከፋፋይነቱና በሴረኝነቱ በሚታወቀው በአቶ ደምለው አንማው የተፃፈ በመሆኑ ማንኛውም የመንግስት አካል ትክክለኛውን መረጃ ሳታገኙና ነገሮችን በጥልቀት ሳትመረመሩ ጣልቃ እንዳትገቡ የአቶ ደምለውን የስም ማጥፋያ ደብዳቤ እንዳትቀበሉት በትህትና እናሳስባለን ::

ዝርዝር ሁኔታዎችን በቅርቡ በተለያዩ ሚዲያዎችና ምሀበራዊ ገፆች ላይ ለህዝብ ይፋ እንደምናደርግ ቃል እንገባለን ::

ውድ የኢትዮጵያ የተግባር ምክር ቤት አባሎችና ከፍተኛ የለውጡ ሀይል የመንግስት ኃላፊዎች በያላችሁበት ሀገር: እኛ በአዲስ አደረጃጀት የተደራጀነው የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አባላት ትኩረታችን በትናንት ላይ ሳይሆን በነገ ላይ ነው ያደረግነው ባለፈው የተጏዝንባቸው፣ አራት ወራቶች ሁሉ በክፉም በበጎም የሲዳ ታሪክ ሆነው ይቀጥላሉ ::ሆኖም ግን የተነሳንበትን አላማ እንደስማችን በተግባር ለማሳየት የለውጥ ጉዟችን ወደ ኋላ ሳይሆን የታሪክ ጎማውን የምናሽከረክረው ወደፊት ነው፡፡

ፍላጎታችን ሐገራችንን ሌሎች አለማት የደረሱበት ለማድረስና ወገናችንን ከተምፅዋችነት ነፃ ለማውጣት በመሆኑ የምንመለከተው ነገን የተሻለ ለማድረግ በሀገራችን የገፅታ ግንባታና መሰረታዊ ልማቶች ላይ እንሳተፋለን ::

ይህ አለም አቀፍ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት ትናንት በምክር ቤታችን ውስጥ የተፈፀመውን የዘር አደረጃጄት አንጃ ቡድን አከርካሪውን በመስበር ሊሰብሩብን አስበው የነበረውን የአንድነት ድልድይ ጠግነን በመሻገር ያለፈንውን ሰባራ ድልድይ ወደ ዃላ ዙረን አንጠብቀውም፡፡ ፍላጎታችን ባለንበት የስደት ሐገር ሆነንም ቢሆን በዘር ያልተከፋፈለችውን አዲሲቷን ኢትዮጵያን መገንባት ስለሆነ ትናንትን በማሰብ የምናባክነው ግዜ የለንም፡፡

ፍላጎታችን ነገ አዲስ ቀን በመሆኑ አዲስ እቅድ አዲስ ራዕይ ይዘን የተግባር ምክር ቤቱን ከዘረኞች አፅድተን የሁሉም ኢትዮጵያዊ እንዲሆን አድርገን በተሻለ ሁኔታ መመስረት ነው:: እኛ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት አባሎች በትናንት ስራችን እየተቆጨን በነገ ስራችን ማላገጥ አንፈልግም፡፡ በነገ ውስጥ ግን ደስታን ሊያመጣ የሚችል ተስፋ ስላለን ያሳለፍነው የዘረኝነት የጨለማ ግዜ ፤ ዳግም ልናስታውሰው አንፈልግም :: በዛሬ ለውጥ ውስጥ የነገን የህይወት ብርሃን እያሰብን ተስፋ መኖሩን በመልካም ስራችን ስኬታማ ለማድረግ በለውጥ ጉዞአችን እንገፋበት አለን ::

ወ/ሮ ማርታ አሻግሬ

የቦርድ ኦፍ ዳይሪክተር ም/ፕሬዝዳንትና ገንዘብ ያዥ የኢትዮጵያ ዳያስፖራ የተግባር ምክር ቤት

• ግልባጭ ለጠቅላ ሚ/ር ፅህፈት ቤት

• በዋሽንግተን ዲሲ የኢትዮጵያ ኢንባሲ

• በሎሳንጀልስ የኢትዮጵያ ኢንባሲ ቆንስላ፣ፅፈት ቤት

• በሜኖሶታ ለኢትዮጵያ ቆንስላ ፅፈት ቤት

• በዩናይትድ ኪንግደም የኢትዮጵያ ኢንባሲ

• ለኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር

• ለኢትዮጵያ መከላከያ ሚ/ር • ለኢትዮጵያ ሠላም ሚኒስትር…”

ውዝግቡ አሁንም ቀጥሏል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *