0 0
Read Time:1 Minute, 6 Second

የሕወሓት ከፍተኛ አመራር የነበሩትና አቦይ ስብሃት በመባል የሚታወቁት አቶ ስብሃት ነጋ በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የሀገር መከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ አስታውቀዋል፡፡
የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ አያሌው ለኢዜአ እንደገለፁት፣ የሕወሓት ከፍተኛ አመራር ስብሃት ነጋ ከተደበቁበትና ለሰው ልጅ እጅግ አስቸጋሪ ከሆነ ሰርጥ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
አቶ ስብሀት፣ የጥፋት ቡድኑ አባላት በሰርጡ ውስጥ ተሸክመው በማስገባት ደብቀዋቸው እንደነበር ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ገልፀው፣ ጀግናው የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፌዴራል የፀጥታ አካላት በጋራ ባደረጉት ፍተሻና አሰሳ፣ ከተደበቁበት በማውጣት በቁጥጥር ስር አውለዋቸዋልል።
በተጨማሪም ከመከላከያን የከዱ ሌሎች የቡድኑ አመራሮች ከአቶ ስብሃት ጋር አብረው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ሃላፊው ገልጸዋል።
ከመከላከያ የከዱ የቡድኑ አመራሮች ታጣቂ ሀይልን በማዋጋትና በማሰልጠን እኩይ ዓላማቸውን ለማስፈፀም ሲሰሩ መቆየታቸውን ጠቁመው፣ በመጨረሻም ሲያስተባብሩ ቆይተው በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የመከላከያ ሰራዊት ኃይል ስምሪት መምሪያ ኃላፊ ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡
በአካባቢው ጥበቃ ላይ የነበረው ታጣቂ ሀይልም መደምሰሱንና አቶ ፣ስብሃት ነጋ፣ሌተናል ኮሎኔል ፀአዱ ሪች- የስብሃት ነጋ ባለቤትና ቀደም ሲል በጦር ሃይሎች ሆስፒተል ሃኪም የነበረች፣ በኋላም በጡረታ የተገለለች፣ኮሎኔል ክንፈ ታደሰ- ከመከላከያ የከዳ፣. ኮሎኔል የማነ ካህሳይ- ከመለካከያ የከዳ፣. አስገደ ገ/ ክርስቶስ- ከመሃል ሀገር ተጉዞ ቡድኑን የተቀላቀለና ለጊዜው ሃላፊነቱ ያልታወቀ ግለሰ በቁጥጥር ስር መዋላአውንና የሜጀር ጀነራል ሃየሎም አርአያ ባለቤት የነበረችና ኑሮዋን በአሜሪካ አድርጋ የቆየች በኋላም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ወደ ጁንታው ተቀላቅላ የነበረች፣ ወይዘሮ አልጋነሽ መለስ ጁንታውን በመያዝ ኦፕሬሽን ሂደት ውስጥ ለማምለጥ ስትሞክር ገደል በመግባት ህይወቷ ማለፉን ብርጋዴል ጀነራል ተስፋዬ ገልፀዋል

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *