“ሕግን የማስከበር እርምጃ ሕግን የተከተለ መሆን አለበት” – ኢሰመኮ

0
0 0
Read Time:36 Second

የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንደሚያሳስበው ገለጸ።

ኮሚሽኑ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በክልሉ ያለውን የእስረኞችን አያያዝ ሁኔታ በተመለከተ በተለይም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቁጥጥር የዋሉ ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ ሌሎችም “በወቅታዊ ሁኔታ” (“haala yeroo”) የተያዙ የሚባሉ ብዛት ያላቸው እስረኞች ከሚገኙባቸውና ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ከሚቀርቡባቸው መካከል በ21 የተመረጡ ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ክትትል ማድረጉን ገልጿል።

በክትትሉ ከእስረኞች እና የፖሊስ ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን፤ እንዲሁም የክትትሉን ግኝቶች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የክልሉ የሕግ አስከባሪ እና የአስተዳደር አካላት በማሳወቅ ምላሽ እንዲሰጥባቸው እንደጠየቀ አሳውቋል።

ኮሚሽኑ በጎበኛቸው የፖሊስ ጣቢያዎች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እና በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው ብሏል።

* የኢሰመኮ ሙሉ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *