የኤርትራ ማስተባበያ !

0
0 0
Read Time:50 Second

ኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤትና የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ “ተጨባጭ ያልሆኑ ተደጋጋሚ ክሶችን” አቅርበውብኛል ስትል ተቃወመች።

ኒው ዮርክ በሚገኘው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (UN) የኤርትራ ወኪል እንዳለው የጸጥታው ምክር ቤት በጉዳዩ ላይ በሚወያይበት ጊዜ እንዲገኙ ወይም አስተያየት እንዲሰጡ እንዳልተጋበዙ አመልክቶ “የኤርትራን ገጽታ ለማበላሸት ተገቢ ያልሆነና ግልጽነት የሌለው” ያለውን ዘዴ ተቃውሞታል።

ማክሰኞ በተደረገው የጸጥታው ጥበቃ ምክር ቤት ስብሰባ ላይ የተመድ የሰብአዊ እርዳታ ኃላፊ ማርክ ሎውኮክ በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ውስጥ ያለው ሁኔታ ከታሰበው በላይ አስከፊ ደረጃ ላይ መድረሱን ተናግረው ነበር።

ማርክ ሎውኮክ ፥ “ሴቶችን እና ታዳጊዎችን በተቀናጀ ሁኔታ በመድፈር ሽብርና ስቃይ እየተፈጸመ ነው። የኤርትራ ወታደሮች ረሃብን እንደ ጦር መሳሪያ እየተጠቀሙበት ነው። የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎች ይከበባሉ፣ ይደበደባሉ እንዲሁም ማስፈራሪያዎች ይደርሳቸዋል”

ይህንን ተከትሎ ኤርትራ የመንግሥታቱ ድርጅት ባለሥልጣን ለምክር ቤቱ የኤርትራ ወታደሮች ይፈጽሙታል ያሉትን ድርጊት አስተባብላለች።

በተመድ የኤርትራ ወኪል ጽህፈት ቤት ባወጣው መግለጫ ፥ “ኤርትራ በትግራይ ክልል ውስጥ ፈጽሞ የሰብአዊ እርዳታ እንዳይደረስ እገዳ አላደረገችም ብሏል። በተጨማሪ ኤርታራ “ምግብን እንደ ጦር መሳሪያ” ፈጽሞ አልተጠቀመችም፤ እንኳን አሁንና ከኢትዮጵያ ጋር የነጻነት ትግል በሚደረግበትና በድንበር ጦርነቱ ጊዜ እንኳን እንዲህ አይነት ነገር አልተፈጸመም” ሲል አክሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *