በሰሜኑ ጦርነት ፍጻሜ ላይ የምናየው የኋይል አሰላለፍ ምን ይመስል ይሆን??
አቢይ የሰሜን መር ፖለቲካዊ ተጽእኖን ለማፈራረስ በለኮሰው ጦርነት- ሰሜኑ የሀገሪቷን እጣፈንታን ወሰኝ ሆኖ በሚወጣበት ሁኔታ ጦርነቱ ክስተት ተፈጥሮአል፦
* ወንድወሰን ተክሉ*
፠ በሰሜኑ ጦርነት ፍጻሜ ላይ የምናየው የኋይል አሰላለፍ ምን ይመስል ይሆን?? አዲስ የኋይል አሰላለፍ ግን አይቀሬ ነው፦
ከእያንዳንደ ጦርነት በኋላ አዲስ ኋይል አዲስ ህግ አዲስ ማህበራዊ ውልና አዳዲስ ስነ ህይወታዊ ፍልስፍና አሸናፊ ሆኖ ብቅ ይላል። በዓለም አቀፍ ተነባቢነቱ ታዋቂ የሆነው ዘ ኢኮኖሚስት መጽሄት The Economist በ2001 የኒዮርክ መንቲዮቹ ህንጻናWorld Trade center በፔንታገን ላይ በአሸባሪው አልቃኢዲ የአጥፍቶ መጥፋት እርምጃ በተፈጸመበት ማግስት The Day the World has changed በሚል አርእስት ነበር የጥቃቱን ዘገባ ይዞ የወጣው። ምን ለማለት ነው አይደለም በሁለት ተጻራሪ ኋይሎችና ሀገራት መካከል በሚካሄደው ጦርነት ይቅርና የእሸባሪዎች አጥፍቶ መጥፋት እንኴን -ልክ በ1914 ሳሪየቮ ላይ በተገደለው ፈርዲናድ አንደኛው የዓለም ጦርነትንና ቀጥሎ የመጣውን አዲስ የዓለም ህግ- ከመስከረሙ 9-11-01ጥቃት በኋላ ዓለም ሙሉ በሙሉ ተለውጣለች።
ዛሬ ባለንበት በዚህ ዘመን እኛ ኢትዮጲያዊያን በአውዳሚ የእርሰበርስ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቀን ባለንበት ሁኔታ በጦርነቱ ፍጻሜ አዲስ የኋይል አሰላለፍ አዲስ ሀገራዊ ህግና ራእይን ብሎም አዲስ ስነ ማህበራዊ የጋሪዮሽ ውል የምናስተናግድ ስለመሆናችን ብዙዎች ያሰቡት ባይመስልም ተፈጻሚነቱን ግን ማንኛችንም ብንሆን የምናቆመው ግን አይደለም።
ኢትዮጲያ ቡድህረ ጦርነት የምታስተናግደው አዲሱን ኋይልም ሆነ አዲሱን ስነ ማህበራዊ ውል እየፈጠረና እየቀሩጸ ያለው ይህ በመካሄድ ላይ ያለው ጦርነት ሲሆን ጦርነቱ አሸናፊና ተሸናፊ አሊያም ያልተሸናነፉ እኩል አቻ ኋሎችን ማውጣት የመቻሉን ክስተታዊ ሂደት እሳቤ ውስጥ በማስገባት ሊከሰት ከሚችሉ ክስተቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው የሰሜን መር ፖለቲካ አይሎ አሸናፊ ሆኖ በሚወጣበት ሁኔታ ላይ በማነጣጠር ምልክታዬን አስቀምጣለሁ።
ጦርነቱ በህወሃት ተሸናፊነትና ተደምሳሽነት ተጠናቀቀ አልተጠናቀቀ-ወይም ጦርነቱ በአቻ ድርድር ተቌጨ አልተቌጨ ዝርዝር ሳይገባ አሁን ባለንበት የፍልሚያ ደረጃ በአቢይ የሚመራው የኦህዴድ መራሹ ስብስብ አጋር ከሚላቸውና ይህንን የስብስቡን ፖለቲካዊ እስትራቴጂ ፍኖተ ካርታን በመቅረጽ ከተደመሩት ኢዜማዎችና መሰል የፖለቲካ ኋይሎች ጋር ሆኖ የሰሜን መር የፖለቲካ ተጽእኖን ላንዴና ለመጨረሻ ጊዜ በማፈራረስ ወደ ደቡብ የማሸጋገርን ግብ አድርገው የከፈተው ይህ የሰሜን ጦርነት ዘመቻ በሚደንቅ ሁኔታ የግቡን አቅጣጫ በመሳትና ብሎም በተቃረነ አቅጣጫ በመጔዝ ሰሜኑን በጥሩም ሆነ በመጥፎ የሀገሪቷን እጣፈንታ መወሰን በሚያስችለው ደረጃ ላይ ያለበትን ሁኔታ ነው ዛሬ ሆነን ማየትና ማረጋገጥ የሚቻለን።
የሰሜኑ ተጽእኖ እንዲህ በቀላሉና በዋዛ የተገነባ ተጽእኖ የመሆኑን ሀቅ ለማረጋገጥ ቆርጦ የተነሳ ይመስል ብኩርናዬን አሳልፌ አልሰጥም በሚል ጽኑ አቌም ወሳኝነቱን ላለማስነጠቅ ክፉኛ ሲፋለም ይታያል። በተለይም ከሰኔ 28ቀን 2021 ጀምሮ የአቢይ መራሹ መከላከያ ጦር ከትግራይ ተቀጥቅጦ መውጣት ማግስት የሚጀምረው ይህ የተጽእኖ አድራጊነት ሚና አድማሱን አስፍቶ ወደ አማራ ግዛቶች ዘልቆ በመግባት ወረራ ከጀመረ በኋላና የአማራ ክልልም ለወረራው መመከቻ የአጸፋ ክተት ጥሪ ማወጅ ጋር ተያይዞ በእጅጉ ኋይሎና ወሳኝነቱን አረጋግጦ እየወጣ ያለበትን ሁኔታ በጽሞና እየተመለከትን ነው።
የሰሜኑ ጦርነት ስንል አማራ ትግራይ ኤርትራና የአቢይ መራሹ የፌዴራል ሰራዊት የተሰለፉበትን ጦርነት ሲሆን በጠላትነት ስሜት እርሰበርስ እየተዋጉ ያሉት የአማራና የትግራይ ኋይሎች አንዳቸውን ለአንዳቸው በጠላትነት ፈርጀው አንደኛው ሌላኛውን ሙሉ በሙሉ ደምሦሶ ለማጥፋት እየተዋጉ ያሉበት ጦርነት ሆኖ ሳለ እጅግ በሚደንቅ ሁኔታ ይህ የሁለቱ ፍልሚያ የሰሜኑን ፖለቲካዊ ተጽእኖን ከሰሜናዊው የሀገቲቱ ቀጠና እንዳይወጣ በማድረግ ደረጃ የአንበሳውን ድርሻ የሚጫወት ሆኖ መገኘቱ ነው። ሁለቱ ባላንጣዎች ወይም ጠላታሞቻ የሆኑት የአማራና የትግራይ ኋይሎች በጭካኔና በጠላትነት እርሰበርስ እየተዋጉ ባሉበት በዚህ ጦርነት ከሁለቱም እውቅና ውጪ uncounsciouslly በጦርነቱ የሰሜን ፖለቲካን ተጽእኖን በማስጠበቅ ደረጃ እየሰሩ መሆናቸውን ነው መረዳት የሚቻለው።ከ4500 በላይ እድሜን ባስቆጠረውና እስከ 1966 ድረስ አራት ስርወ መንግስታትን ( የመጀመሪያው የኩሽ ስርወመንግስት ለ500ዓመታት የገዛ፣ቀጥሎ የኢትኦጵ ስርወመንግስት ለ1000ዓመታት የገዛ ከክርስቶስ ልደት 1000ዓመት በፊት በቀዳማዊ ምንይልክ የተመሰረተው ሰለሞኖዊው ስርወመንግስት እስከ 1966ድረስ ለ3000ዓመታት የገዛና በመካከሉ በ10ኛው ክፍለዘመን ተመስርቶ ከ260ዓመታት በላይ የገዛው የዛጉዌ ስርወ መንግስትን)
ባስተናገደው የኢትዮጲያ ታሪክ ውስጥ ትግራይ ጎንደር ወሎ ሸዋና ጎጃም የየነገስታቱ መቀመጫ በመሆን የፓለቲካውን ዘዋሪ ከሀገሪቱ ምድር ወገብ (የኢትዮጲያ የምድር ወገብ አዲስ አበባ ናት) በላይ በሰሜን የተወሰነ ሆኖ እንዲቀጠለ የታሪክ መዛግብት ያሳዩናል እንጂ በ16ኛው ክፍለ ዘመን ከምስራቅ ተነስቶ ኢትዮጲያን ለ15ዓመታት በጭፍጨፋና በውድመት ከገዛው አሊ ኢብን አልጋዚ ወይም መሀመድ ግራኝ በስተቀር ስልጣንና የፖለቲካው መዘውር ከኢትዮጲያው ምድር ወገብ ከዛሬዋ አዲስ አበባ በላይ በሰሜኑ የሀገሪቱ ግዛት ውስጥ ተወስኖ የኖረ መሆኑን ነው የምንረዳው።
ከ1966 ወዲህ የተመሰረቱትን ዘውድ አልባ ሁለት ስነመንግስታትን ታሪክ (ደርግ መራሹ የኢህድሪ መንግስትና ህወሃትና ኦህዴድ መራሹ የኢህአዴግና ብልጽግና መንግስታት መሪዎች ከብልጽግናው አቢይ አህመድ አሊና ከኢህአዴጉ ስልጣን አልባው ኋይለማሪያም ደሳለኝ በስተቀር መለስ ዜናዊ ተስፋዬ ገብረኪዳን መንግስቱ ኋይለማሪያም ተፈሪ ባንቲና አማን አንዶም በሙሉ መሰረታቸው ዛሬ የሰሜን ፖለቲካ ኋይል ለማጥፋት ዘመቻ በተከፈተበት ከሰሜኑ የፈለቁ መሆናቸውን ስንመለከት ኢትዮጲያን እንደ ሀገር ከመፍጠር ጀምሮ ሀገረ መንግስቱን ስነ ሀገራዊ ማህበረሰባዊ ውልና ባህልን በመገንባቱ ደረጃ የሰሜን መራሹ ፖለቲካ ከ4500በላይ እድሜንና ልምድን የቆጠረ መሆኑን ነው የምናየው።
የሰሜን መር ፖለቲካ ስንል መቀመጫቸውን ከአዲስ አበባ ጀምሮ በአንኮበር በደብረ ብርሃን በጎንደር በላስታ በሀይቅ በላሊበላ በየሃ በአክሱም በቆሃይቶ በሮሃና ….ወዘተ በመሰሉ ከተሞችና ስፍራዎች አድርገው ኢትዮጲያን ላለፉት አራትሺህ በላይ ዓመታት የገዙትን ነገስታት ታሪክ ማለታችን ነው።
ለምሳሌ የሰለሞን ስርወ መንግስት መሰራች የሆነውን ቀዳማዊ ማንይልክን ለአብነት የወሰድን እንደሆነ በአባቱ ንጉስ ሰለሞን አይሁዳዊ የይሁዳ ነገድ ደም ያለበትና በእናቱ በንግስት ሳባ (ማክዳ) ኢትዮጲያዊ የአማራ ደም (ይህ በእናቱ የአማራ ደም ነው ያለበት የሚለው ታሪካዊ መረጃ በታሪክ ጸሃፊያን ዘንድ እስከዛሬ ድረስ ከስምምነት ላይ ያላደረሰ የውዝግብ ምንጭ ነው) እንዳለበት የሚነገር ሲሆን ከዘመናት በኋላ ግን በዚህ ንጉሳዊ የደም ሀረግ ውስጥ በጋብቻ አቌርጠው በመግባት ከትግሬና ከኦሮሞ ነገድ ተወላጅ የሆኑ ነገስታቶች የሰለሞንን ስርወ መንግስት በማስቀጠል የንግስና ዘውድ እየጫኑ ሀገር ሲገዙ አንዳቸውም መቀመጫቸውን ከኢትዮጲያ የምድር ወገብ ካልኴት የዛራዋ አዲስ አበባ በታች ወደ ደቡብ አዛውረው የገዙበት ታሪክ ያለመኖሩን ከታሪክ መዛግብት መረዳት እንችላለን።
እናም ይህንን ከአራትሺህ ዓመታት በላይ እድሜ ያስቆጠረውን የሰሜን መር የፖለቲካ ተጽእኖን (Center of Political Power) አቢይ መራሹ የኦሮሙማ የፖለቲካ ኤሊት ከአጋራቸው ኢዜማ ከኤርትራው ኢሳያስና ከደቡብ ኢትዮጲያ የፖለቲካ ኤሊቶች ጋር በመስማማትና ብሎም እቅድና ፕላን በማውጣት ወደ ደቡባዊቷ የሀገራችን ግዛት ለማዘዋወር ሰሜንን politically irrelevant ፖለቲካዊ ተጽእኖ የሌለው ምውት ክልል ለማድረግ ብዙ የታቀደለትን አማራንና የትግራይን ኋይሎች እርሰበርስ አከሳክሶ የማውደም ዘመቻን ላለፉት ሶስት ዓመታት ያህል በግልጽ አደባባይና በስውር ሲጧጧፍ በመክረም ዛሬ ወደለየለት ጦርነት ደረጃ ላይ ሊሸጋገር ችሏል።
በ2007 ህዳር ወር ላይ በአሜሪካን በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ላይ አሸናፊ የሆነው ባራክ ኦባማ አሸናፊነት ሲታወጅ በዶ/ር ብርሃኑ ነጋ የሚመራው ግንቦት 7 ንቅናቄ በርእሰ አንቀጽ መልክ ባወጣው የአቌም መግለጫ «በሰሜኖች የሚመራውን የኢትዮጲያን ፖለቲካ ወደ ደቡብ የማዛወሩ ጊዜው አሁን ነው። አማራውም ሆነ ትግራዋዩ ስልጣን ወደ ደቡብ ኢትዮጲያ መዛወር አለበት ብለው ሊያምኑና ሊቀበሉ ይገባል» በማለት ስልጣን በችሎታና በብቃት ሳይሆን በተራ መሆን አለበት በማለት ይፋ አድርጎ ነበር። ለዚህም ነው በ2018 አቢይ ወደ ስልጣን ሲመጣ ጃዋር መሀመድን ጨምሮ ሁሉም ማለት በሚቻል መልኩ የኦሮሞ ፖለቲከኞች «አሁን ተራው የእኛ ነው» በማለት በግልጽና በይፋ ሲያስተጋቡ የተደመጡት።
የአቢይ «እናቴ በሰባት ዓመቴ 7ኛ ንጉስ እንደምሆን ነግራኛለችን »ትርክት መሰረት ያደረገው የስልጣን ርሃብተኝነት ላይ የለየለት ጸረ አማራ እና ጸረ ትህነግ/ትግራይ በመሆን ሁለቱንም ነጥሎና ነጣጥሎ ለማጥፋት የተጋዘበት ርቀት ይህንን ህልሙን ሊያደናቅፉበት የሚችሉ ኋይሎች ፈጥኖ በአጭር ጊዜ የማፍለቅ አቅምና ብቃት ያላቸው ሁለቱ ሰሜናዊ ህዝብ በመሆኑ ይህንን የስልጣን ስጋት ለመቀነስና ብሎም ለማይፋት ላወጠነው ታላቅ ውጥን የእነብርሃኑ ነጋ አንዳርጋቸው ጽጌንና የኢሳያስ አፈወርቂን ሁለንተናዊ ድጋፍ -ማለትም ፖለቲካዊ ሴራ ላይ የተመሰረተ የሰሜኑን አቅም አዳክሞ የማጥፋትን እቅድ ስልትና እስትራቴጂን በገፍ በመቀበል መጀመሪያ አማራን ነጥሎ በመምታት ዘመቻውን ከጀመረ በኋላ ቀጥሎም ትህነግን/ትግራይን በመምታቱ ዘመቻ ላይ ትኩረቱን በማድረግ ሻእቢያን ያሳተፈ ጦርነትን በትግራይ ላይ ለመክፈት ቻለ።
የዚህ ጦርነት ፍጻሜ ከሚፈጥርልን ዘርፈ ብዙ አዳዲስ ክስተቶች ውስጥ አንዱና ዋነኛው ስልጣንን ወደ ደቡብ የማዘዋወሩን አቢያዊን እቅድ እንኩትኩቱን የሚያወጣ መሆኑ ነው።
፠ ሰኔ 28ቀን 2021 ይህ የሰሜኑን ፖለቲካ የማጥፋት ዘመቻ የከሸፈበት ታሪካዊ ክስተትነቱ፦
ዛሬ መስከረም 10ቀን 2021 ላይ ሆነን የሰሜኑን ጦርነት ስንመለከት የምናገኘው ምስል ሁለቱ ኋያላን የሰሜን ፖለቲካ ኋይሎች ማለትም የአማራና የትግራይ ኋይሎች እጅግ ደም አፋሳሽ በሆነ የእርሰበርስ ጦርነት ውስጥ ተዘፍቀው ያሉበት መሆናቸውን ማየት የሚቻለንን ያህል በዚሁ የከረረ የጠላትነት ውጊያ ውስጥ ለሁለቱም ክፍል በውል ባልታወቀና ግንዛቤ ባልተሰጠው መልኩ ሁለቱ እርሰበርስ ለመጠፋፋት እየተዋጉ በአንጻሩም የሰሜን መር የፖለቲካን ተጽእኖን ከህዳር 2020 በፊት ከነበረበት ዝቅተኛ ደረጃ በማንሳት የሀገሪቱን እጣፈንታን በሚወስንበት ወሳኝ ደረጃ ላይ ያደረሱበትን ሁኔታን ነው ዛሬ በግልጽ ማየት የሚቻለው። ለዚህ ደግሞ የሰኔ 28ቱ 2021 የመከላከያው በወያኔ ተቀጥቅጦ ከትግራይ መውጣት ወሳኝ Turning Point ሆኖ እናገኛለን። ወያኔ ጮርቃው አቢይ በፓርላማ ለንፋስ የተሰጠ ዱቄት ሆናል እንዳለው ህልፈተ ህይወቷ ተፈጽሞና ስርዓተ ቀብሯም የተፈጸመ ቢሆን ኖሮ የሰሜኑ ፖለቲካ ዛሬ መፍጠር የቻለውን ውሳኔ ማስተላለፊያ ወታደራዊ ኋይልን አማራውና ትግራይ መገንባት ባልቻሉና በአንጻሩም ከህልፈተ ወያኔ በኋላ አቢይና ግብረ አበሮቹ ሙሉ በሙሉ እያንሰራራ ባለው የአማራ ብሄርተኝነትና በአደረጃጀቱ ላይ በመዝመት ከሰኔ 2019 ጭፍጨፋ የተረፈውን ፖለቲካዊ ኋይልን ለማጥፋት በማን አለብኝነት በዘመተና የአማራን ፖለቲካዊ ኢኮኖሚያዊና ስነ ማህበራዊ ኋይልን በደመሰሰ ነበር።
የወያኔ በአቢይና በሻእቢያ ኋይሎች ያለመጥፋት ይህንን የአቢይ መራሹን ጸረ ሰሜን ፖለቲካዊ ኢላማን ግቡን እንዳይመታ ከማድረጉም በላይ ሌላው የተጫወተው ትልቁ አዎንታዊ ሚና አጠፈዋለሁ ብሎ የተነሳበትን የአማራን ህዝብ እጅግ በሚደንቅ ሁኔታ አማራው የራሱን የሆነ አማራዊን ኋይል በአጭር ጊዜ አደራጅቶ እራሱን እንዲያጠናክር በማድረግ ደረጃ የሰኔ 28ቱ መከላከያው ከትግራይ ተባርሮ መውጣትና ያንን ተከትሎ የወያኔ በአማራ ግዛቶች ላይ የፈጸመቺው ወረራ ትልቁን አስተዋጽኦን እንዳደረገ ከግንዛቤ ውስጥ ያልገባ ግን በትክክል የተፈጸመና እይተፈጸመም ያለ ክስተት ነው።
የወያኔ ከነበረችበት የመቀበሪያ ጉድጔድ ድንገት ተዓምር በመሰለ መልኩ አምልጦ መከላከያውን ከትግራይ እስከማበረር መድረስና ብሎም ዋና መዳረሻ ግቧን አዲስ አበባ በማድረግ የአቢይ መራሹን የብልጽግናን ስርዓት ለመገርሰስ ያለመውን የጦርነት ዘመቻዋን የአማራን መሬቶች…(ይቀጥላል)