የ ሃይማኖት አባቶች የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብን ባርኩ፡፡
Read Time:40 Second
የግድቡ ሁለት ተርባይኖች በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወራት ሃይል ማመንጨት ይጀምራሉ
የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሁለት ተርባይኖች በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወራት ሃይል ማመንጨት እንዲችሉ እየተሰራ መሆኑን የውሃ፣ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ገለጹ።
የህዳሴ ግድብ ድርድር የተለያዩ ፈተናዎች እንደነበሩ አስታውሰው የግድቡ ግንባታ በአስቸጋሪው ጊዜም ተጠናክሮ በመቀጠሉ በአዲሱ ዓመት መጀመሪያ ወራት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች ሃይል ማመንጨት ይጀምራሉ ብለዋል።
በዚህም ቀሪ ስራዎች በጥቂት ጊዜያት አጠናቀው በ2014 ዓ.ም መጀመሪያ ወራት ላይ ሃይል ማመንጨት እንዲችል ሌት ተቀን እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ፈጣሪ የሰጣት ጸጋዋን የመጠቀም መብት አላት ያሉት ሚኒስትሩ፤ ከምፅዋትና ድህነት መውጣት የሚቻለው ጠንክሮ በመስራትና የተፈጥሮ ሃብትን በማልማት ነው ብለዋል።
የሃይማኖት አባቶቹ ወደ ስፍራው የተጓዙት የዘመን መለወጫን ምክንያት በማድረግ ቡራኬ ለመስጠትና የግድቡን ሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌት አስመልክቶ አጋርነታቸውን ለመግለፅ መሆኑንም ተመልክቷል።
አዲሱ ዓመት የመረጋጋትና የተስፋ፣ የሰላም የፍቅርና አብሮነት እንዲሆን ለመላው ኢትዮጵያዊያን መልካም ምኞታቸውን መግለፃቸውን ኢዜአ ዘግቧል።