የብልፅግና መንግስት የሕግ ጥሰትና ማናለብኝነት።
በ ተዘራ አሰጉ
መግቢያ
የሕግ ፅንሰ ሃሳብ እንደሚያመለክተው ሕግ እራሱን የቻለ የዕውቀት መስክ/Regiem/ ነው። ሕግ ሉሃላዊነቱ ተጠብቆ ያለማንምና ያለምንም ጣልቃ ገብነት የሰው ልጆች፣መንግስትና ተቋማት እኩልነትና ርዕትእ፣መብትና ፍላጎት የማህበረሰብን፣ ህዝብንና የተቋማትን ልዕልና አስጠብቆ ለማስኬድ የሚያስችልና በሰላም ተግባብቶ መኖርን የሚያሳልጥ ሂደት ወይም እሴት ነው። ለዚህም ነው ኢትዮጵያ ፍትሃ ነገስት፣ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ፣ የፍትህ ብሄር ህግ፣ የቤተሰብ ሕግ፣ ሕገ መንግስት ወ.ዘ.ተ. ቀርፃ ለዘመናት እየተዳደርችና እየተመራች የዘለቀችው። ኢትዮጵያዊያንም “ በአምላክ ይዥሃለሁ፣ በሕግ አምላክ “ እያልን ለዘመናት አንዱ አንዱን እያከበረ ኑሮዎን ያሳልጥ የነበረው። ህግጋትን የተላለፈ ደግሞ የሚገባውን ቅጣት እየተሰጠው ለዘመናት ዘልቀናል። ታሪክ እንደሚያሳየው የዛሬውን አያድርገውና ኢትዮጵያና ኢትዮጵያውያን በዓለም ፊት እግዚአብሔርን የፈሩና ወንጀልን የሚጠየፉ ተብለው የሚሰበክላቸው ነበሩ። የህግ ፅንሰ ሃሳብ ኢትዮጵያዊያን የሕግ ጠበብትና የዘመኑ ፈረንጆች ሕግን እንዴት እንደሚተነትኑት እንመልከት:
ፍትህ ነገስት / The Law of the king/
ምዕራባዊያን ከእኛ ቀድተው ሕግ ከማርቀቃቸው በፊት የእግዚአብሔር መንፈሳዊውን ሕግና አለማዊውን ሕግጋት አጣምረው በመያዝ በፍትህ ነገስት ይዳኙ ነበር። በቀደምት ዘመን ኢትዮጵያዊያን አምላክን በመፍራትና በቃሉ በመገዛት እንዲሁም በስጋ መድከም የሚከሰቱ የህግ ሰንኮችን አለማዊ የሆኑትን ሕግጋት አጣምረው በመንቀስ ፍትህን ተግባራዊ ያደርጉ ነበር። ሰው በሕገ እግዚአብሔር ታርቆ ሰላማዊ እንዲሆን ይገፋፋል ። በአለማዊው ሕግ ደግሞ እንደ ስተቱና ወንጀሉ አንቀፅ እየተጠቀሰ ይዳኛል። ወንጀለኛ በሕግ አግባብ ሲቀጣ ለማህበረሰቡ አስተምሮትን ይሰጣል። በመጀመሪያ ይቅርባይና ምህረት ሰጪ አምላክ ነው። ይቅርታም ሆነ ምህረት ከአምላክ የሚገኘው የሰው ልጅ ስህተቱን፣ወንጀሉንና መተላለፉን ከጌታ እግር ስር ወድቆ” በድያለሁና ይቅር በለኝ” ሲል ነው። እንዳሁኖቹ ስልጡን ነን ባዮች የሰው ዘር መሆናቸው የሚያጠራጥሩ እንደፋሽን ልብስ ስንት ገደልክ፣ደፈርክ፣ዘረፍክ ወ.ዘ.ተ. ሳይባል ፣“አበሱ ገበርኩ”። ይህ ሁሉ ሆኖ የዘመነኛ ፍርድ ቤቶቻችና መሪዎቻችን ለገደለ፣ላስገደለ፣ለደፈረ ምህረት እየቸሩ ተቸግሮ ኪስ ላወለቀና ሰላማዊ ሰልፍ ለወጣ የእሳት ምድርና የሚገላቱባት ምድር ሁናለች። ህግ የምህረት፣ የአመክሮና የሰብአዊነት ወንጀል ማቀለያ አንቀፆች እያሉት በጓደኛ፣በትግል መስመር ጓደኝነት፣ በትውውቅ የምትመነዘርና የምትቸረቸር ሁናለች።
ስልጣኑን፣ሃብቱን፣ቀደምት ወዳጅነትን ሃስቦ፣”ነግ ለኔ” በሚል ህሳቤ፣በጉቦ ተደልሎ ወ.ዘ.ተ ሕግን የሚያዛንፍ “ወዮለት” ተብሏል። የተበደሉት ድምፅና ደም ለአምላክ “ፍርድ ግን ሥጥ ተው” እያሉ ይጮሃሉ፣ ይቃትታሉና። የኛ ባለስልጣናት ሰሞኑን በሥልጣናቸው ከመታበያቸው የተነሳ አልተገነዘቡትም እንጂ እንደ ዲያቢሎስ
አምላክ ስራ እየገቡ ነው። መሪዎችችን “አጃይብ” ነው የሰማዮንና የምድሩን ሕግጋቶች ንቀውና ጥሰው ይቅር ባይም፣ፈራጅምና መሃሪም እነሱ ሁነዋል። በእኔ ዕድሜ የሃገር መሪ በራስ ተነሳሽነት ለወንጀለኛ ይቅርታ ሲያደርግ አላየሁም።
የፈረንጆች የሕግ መግቢያ ትንተና
/Introduction to Law/ በእንግሊዝኛው “ The Law embodies the story of a nation’s development through many centuries , and it cannot be dealt with as if it contained only the axioms and corollaries of a book of mathematics.” Wendell Holmes.
The law is “ The regime that orders human activities and relations through systematicapplication of the force of politically organized society, or through social pressure ,backed by force, in such society. The law is abstract long for our needs. We should therefore link of the law in more basic terms as rules that govern and guide actions and relations among and between person ,organizations and governments” A Dictionary of Basic legal Terms.
ከላይ የሰፈረው የእንግሊዝኛ ሰነድ የህግን ፅንሰ ሃሳብ ሲተነትን “ሕግ ለዘመናት የሰው ልጅ እንቅስቃሴን ፣ግንኙነትን፣ታሪካዊ እድገቶችን በተለየ ጥበብ በውስጡ አቆራኝቶና ይዞ በዐይን የማይታይና የማይዳሰሱ ፅንሰ ህግጋትን በማስረፅ ህብረተሰብን፣ተቋምንና መንግስት ሳይቀር በማንኛውም የፓለቲካ አስተሳሰብ ተፅዕኖ ሳይደረግበት የሚያዝና የሚመራ ገቢረ ሃሳብ ነው። እንዲሁም የሰው ልጅ ፍላጎቱ ተሟልቶና ሳይዛነፍ እንዲኖር የሚረዳና የሚያሳልጥ ሲሆን እንደ ሂሳብ ትምህርት “አንድ ሲደመር አንድ ሁለት ነው” ብለን የምንተነትነው ፅንሰ ሃሳብ አይደለም ይለዋል።
Wendell Holmes.
የህግ መዝገበ ቃላት መፅሃፍ ህግን እንዲህ በማለት ይተነትነዋል “ ህግ ማህበረሰብ፣መንግስትና
ድርጅቶች ተጣምረው፣ እየተመጋገቡ፣ ዝንፈትንና ችግሮችን አርቆ በመያዝ በተግባቦት እንዲኖሩ የሚራናዳ የሚያስተዳድር ፅንሰ ሃሳቦችን የያዘ መስክ ነው” ይለዋል።
በዚህ አጠር ያለ ዳሰሳ በግርድፉ ሊተች የሚዳዳው ሰሞኑን መነጋገሪያ ስለሆነው ሕጋዊ ለማስመስል በመግለጫ እየተሽሞነሞነ የሚተነተነውን የፍርድ ቤት ፍርድ ገምድልና በጣልቃ ገብነት የተወሰነን ውሳኔ
ሙያዊ በሆነ እያሴ ለመገምገም ነው። የብልፅግና ፍርድ አስፈፃሚ /Law Executive body/ ስለፈፀመው እፀፅ / Transgression of Law/ እንዳስሳለን።
በኢትዮጵያ ከተከሰቱ ለውጦች ጋር አገናዝቦና አንፃፅሮ ለመተንተንም ይሞከራል። በመጀመሪያ የፓለቲካን ጥቅም ለማስጠበቅና ስልጣንን ሙጥኝ አድርጎ ለመያዝ ሲባል ሕግን መጣስ፣ ዕፀፅ ያለው ውሳኔ ማስተላለፍ ያውም ፍትህና ርትዕን ያስጠብቃል ከሚባለው አካል መሆኑ “ታዘብኩሽ ምኔ” እደተባለው የሚያስተዛዝብ ነው። ይህ ፈር የለቀቀ አካሄድ አንድም ሕዝብን በመናቅ የተወሰደ ውሳኔ ሲሆን በሌላ ጠርዝ ተማሩ የተባሉ ሰዎች ሕሊናቸውንና እነሱነታቸውን የሸጡበት ክስተት እንደሆነ ግንዛቤ ውስጥ መግባት አለበት። ኢትዮጵያ በአስራ ዘጠነኛው፣በሃያኛውና በሃያአንደኛው ምህተ አመታት በለውጥ ማህበል እንደተናጠች ልብ ይሏል።
በእነዚህ ቀደምት አብዮታዊ /ነውጣዊ/ና ሰሞነኞቹ ሰላማዊ ሽግግራዊ የመንግስት ለውጦች በአመራርና በስልጣን የነበሩ ሰዎች በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የሰሩት ስሕተቶች እንዴት ተስተናገደ የሚለውን ሙያዊ በሆነ አካሄድ ለመዳሰስ ይሞከራል።
የማህበራዊ ህግጋት የስራ የአፈፃፀም-ስህተት /Civil maladministration/ Jurisdiction and errors of in administration Law values/ የሚለውን ፅንሰ ሃሳብ መሰረት ስንፈትሽ ወያኔ ካከናወነው ግፍና ወንጀል አንፃር ከወያኔ በፊት የነበሩት መንግስታት የፈፀሙት ሰንክ በፃሃፊው ግምግማ ስህተቶች/maladministration/ ናቸው ለማለት ይደፍራል። እስኪ ከኃይለስላሴ ጀምሮ አሁን እስካለው የብልፅግና መንግስት እንዲሁም ከለውጥ ማግስት ወንጀልና ግፍ ፈፅመዋል በተባሉ ባለስልጣኖችና ሹመኞች የተወሰድ ሕጋዊ እርምጃወች፣ የህግ አካሄዶችን በግርድፉ ምን ይመስል እንደነበር እንገምግም።
በአፄ ኃይለስላሴ ስርዓተ መንግስት ፍፃሜ ማግስት
የእኛ ሕዝብ ትንሽ የዋህነት የሚያጠቃው ከመሆኑ ባሻገር፣ የእምባጓሮ/የአመፆች/ መነሻ፣ ዓላማና ግብ ማገናዘብ ይሳነዋል። እንዲሁም “ነገር ከስሩ ፣ ውሃን ከጥሩ” እንዲሉ ለዐፄ ኃይለስላሴ ስርዓተ መንግስት መውደቅ የተማሪዎች እንቅስቃሴ የጎላ አስተዋጽኦ ቢኖረውም ቅድመ ወያኔ የነ መለስ፣ ስብሃትና መሰሎቹ የራሳቸውን የግል ስውር ዓላማ ለማስጠበቅ ሲሉ በሻጥር፣ በተንኮል አመፁን ያጦዙት እንደነበረ ትኩረት ሊሰጠው ይገባል። የተማሪዎች ንቅናቄ መነሳሳትና የኢሕአፓ አመሰራረት በትግራይ ልጆች በነ ብርሃነ መስቀል ተወጥኖ በነመለስ ዜናዊና ስብሃት ሽረባ የተካነ እንደሆነ ስንቶቻችን እናውቃለን? የአፄውን ስርወ መንግስት ከተገረሰሰ በኋላ እንዴት ኢህአፓ፣ኢዲዮንና ምኤሶንን እንደመሰረቱና እንዴትስ ፍርክስክሱን እንዳወጡት ትገነዘቡ ይሆን? ምን ያህል የኢትዮጵያና የአማራ ልጆች በነስብሃት፣ መለስና ወያኔ ሽረባ እንደረገፈ ልብ ይሏል። አሁንም ከዚህ አዙሪት አልወጣነም። የተማሪዎቹ በሻጥር የተተበተበ አመፅ ተሳክቶ የዐፄ ኃይለስላሴ ስርአተ መንግስት ሲገረሰስ የካቢኔ አባላቱና ሚኒስትሮች በደርግ ጊዚያዊ ወታደራዊ መንግስት በቁጥጥር ስር ውለው ነበር። ነገሩና ሽረባው ያልገባው የነተፈሪ ባንቲ፣አጥናፉ አባተና የኮሎኔል መንግስቱ ስርዓተ መንግስት እንደ ጀት በፈጠነ አካሄድ የተከበሩትን ባለ ግርማ ሞገስ ሚኒስትሮችና ባለስልጣኖችን በጦር ፍርድ ቤት አቅርቦ እነዚያን የመሰሉ የተማሩና አሉ የተባሉ ምሁራን መረሸኑ አነጋጋሪና ጥያቄ ውስጥ የሚያስገባ ሆኖ ዘልቋል። ነገር ግን አንፃራዊ በሆነ የህግ አካሄድ/ሂደት/ ዕርምጃ ተወስዶባቸዋል ለማለት ያዳዳል። ይህ የፍርድ ሂደት አሁን ካለው የጅሎች ጥርቅም ውሳኔ አንፃር ሲታይ የደርግ ባለስልጥናትን ያስቆጨና ያወዛገ ቢሆንም ፍርዱ ሕጋዊ አካሄድን /Legal procedure/ የጠበቀ እንደነበረ ልብ ይሏል። ይህ ዘግናኝ ርሸና ቅድመ ወያኔ የነመለስ፣ስብሃትንና ነገሩ ያልገባውን ተማሪ አስቧርቆ ነበር። ይህንን ሂደት ለአንባቢው እንዲነጋገርበት የቤት ስራ ሰጥቸ ለህዝብ ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት የተደረገውን አካሄድ ግን ውሳኔው የሕዝብን፣የብሶተኛውንና የጭቁኑን አርሶ አደር ምሬት ያገናዘበ ነበር ለማለት::
ኢሕአድግ መራሹ መንግስት ስልጣን በያዘ ማግስት ምን ተከናወነ?
እ.ኢ.አ. 1983 ሕወሃት ስልጣን በተቆጣጠረ ማግስት የጊዚያዊ ወታደራዊ መንግስት ታላላቅ ሹማምንቶችና የኢሰፓ አባላትን በሙሉ በሚባል መልኩ በቁጥጥር ስል አውሉአል።
በጣም የሚገረመው ሕወሃት ሕጋዊ አካሄዱን /Legal due processes/ በመከተል በደርግ አገዛዝ ስርዓት ወንጀል ፍፅመዋል የተባሉትን የሰነድ ሆነ የሰው ማስረጃዎችን በማቅረብ ጥፋተኛ ናቸው በተባሉት ላይ ፍርድ እንዲሰጥ አድርጓል።
እሁን ሁነን የደርግ ስርዓትን ወደ ኋላ ሂደን ስንቃኝ ከጥቂቶቹ በስተቀር ሕወሃት ከሰራው አገርን እንደ ሃገር፣ ህዝብን እንደ ህዝብ ከማጥፋትና የኢትዮጵያን ሃብት ንብረት ለትግራይ ምድርና ለትግራይ ሹምምንት መደላቀቂያ ከማድረጉ አንፃር የሕወሃት ወንጀል በጣሙን የገዘፈ ነው ለማለት ያስደፍራል። ያም ሆኖ የሕወሃት አገዛዝ በደርግ ሹማምንት ላይ የሞት ፍርድ ካፀና በኋላ በተደረገው ድርድርና ወንጀልን የማቅለል ሂደት የዕድሜ ልክ እሥራት ተወስኖባቸው የነበረ መሆኑ የሚታወስ ሲሆን ግማሾቹ በእስር ቤት ሕይወታቸው ሲያልፍ፣ ሌሎችም በእስር ቤት ላሽቀው እንዳይሆኑ ሁነው በአሞክሮ ተለቀዋል።
የሰላም የሽግግር፣ የዕርቅና የብልፅግና ምንግስትን አካሄድ ሲዳሰስ
ኢሕአድግ ወደ መጨረሻ ጊዜ ከመጃጃቱ የተነሳ ተአድሶና መተካካት የሚል ፈሊጥ ይዞ ነበር። ከዚያም ጎንደር ላይ በተከናወነው የእምቢ ባይነት ክስተት ጥርሱ ሲነቃነቅ ፋኖና ቄሮ “ወግድልኝ” ብለው ሲገፈትሩት መተካካቱ እውን ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ ብቅ አሉ። ከዚያም በጠቅላይ ሚንስትር ሹመት ማግስት የስህተቶች፣የውንጀሎችና የሴራው ሊቀ ሊቃውንት ሕወሃት ቢሆንም በኢሕአዲግ ስም ዶ/ር አብይ ይቅርታ ጠየቁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆደ ሰፊ ነውና ይቅር አለ። ወገን ያዝልኝ ከዚያ ሽማግሌዎቹ “መቀሌ ትዝ አልኝ እናንት ቀጣዮን ስንኝ ተቀኙት” ብለው የትማመኑትን ተማምነው ነጎዱ። ከዚያም “ ወይ አዲስ አበባ ወይ ቤተመንግስት ፣ ፓርላማየ ሆይ ሸገር እንደ ሰው ይናፍቃል ወይ” ብለው ጦር ሰብቀው የኢትዮጵያን ሰራዊት በጀርባ አረዱት። ሃብት ባከነ፣ወገን ተሰዋ። ከዚያም ተንቤን ገብተው መንግስት መቀሌን ሲለቅላቸው አማራና አፋርን ወረሩ። ሃገርን የሸጠ፣ ሕዝብን ከሕዝብ ያናከሰ፣ በተለይ በአጠቃላይ የአማራን ህዝብ በተለየ መልኩ በወልቃይት ጠገዴ ሕዝብ ላይ የዘር ማጥፋት ወንጀል /Jonocide/ የፈፀመን፣ በትግራይ ለደንበር ጥበቃ የሰፈረን የሃገር ሰራዊት ከጀርባ እንዲረሽን ያደረገን አመራር፣ የአማራና የአፋር ህዝብን በማናለብኝነት ወሮ በሺህ የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዊያንን ለሞት፣ ለስደት የዳረገ፣ ሴት ልጃገረዶች እንዲደፈሩ መርህ ነድፎ ያስቀመጠን፣ ሃገረ ኢትዮጵያን እንደ ሃገር የካደን አገዛዝና አመራር ያውም በጠቅላይ ሚኒስትሩ ቀጭን ትዕዛዝ /Legal intravention/ በይቅርታና ምህረት መልቀቅ እኔም አለሁበትና እኔንም ይቅር ብላችሁ ተውኝ እንደማለት ነው ያሰኛል።
ማጠቃለያ
የፅሁፌን ማጠቃለያ የሚሆነውና የሚያጠጥነው
በብልፅግና ፣ በሕግ አስፈፃሚው በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጋሻ ጃግሬነት የተከወኑትን የሕግ ፅንሰ ሃሳብ ጥሰቶችና አጠቃላይ እፀፆችን አስመልክቶ እያሴየን በመስጠት ነው።
- 1) ሕግ የህብረተሰብን ጥቅም፣ ፍላጎትና ህሳቤ የማስጠበቂያ ቁልፍ መስክ ነው። ከዚህ ላይ የወንጀለኞቹየነስብሃትና መሰሎቹ መፈታት አይደለም ዋናው ቁም ነገሩ።ሕዝብ አንድ የሚፈልገው(Needs)አለ እሱም ፍትህ ነው። ይህን የፍትህና የዳኝነት መሻት የህግ አስፈፃሚው በአግባቡቡ አልመለሰም፣
- 2) ሕግ ማህበረሰብን ፣ ተቋማትንና መንግሥትን ተጣጥመውና ተመጋግበው በስጥቶ መቀበል መርህ እንዲጓዙ የሚያደርግ ነው። ነገር ግን ህግ አውጭው፣ ሕግ አስፈፃሚውና መንግስት ተቋማት / Legal procedures/ ሳይጠብቁናስሜቱን ሳያከብሩ ስላደረጉት አሁን ያለውን ያለመተማመን ኩነት ፈጥሯል፣
- 3) ሕግ አስፈፃሚው ከማንም ተፅህኖ ነፃ (Independet entity) መሆን እንዳለበት የሕግ ሳይንስ ይደነግጋል ፣ ነገር ግን የክስ መዝገቡ ምስክር ቀርቦበት፣ማሰረጃወች ተሰንደው ሳይመረመሩና የፍርድ ውሳኔ ሳይሰጥበት በመንግስት ባለስልጣን ማናለብኝነት በአቋራጭ ክሱ እንዲቋረጥ መደረጉ ከላይ እደጠቀስነው በደርግ ስርዓትም ሆነ በከፋፋዮ የህውሃት ኢሕአድግ ሳይደረግ ምንም ለይስሙላ ቢሆንም ይህ ፈር የለቀቀ ጣልቃ ገብነት መደረጉ ብልፅግና የሕወሃት የእንጀራ ልጅ መሆኑን ያሳያል።4)ይህ አካሄድና ፍርደ ገምድል ውሳኔ ሕወሃት ትግራይ ከአስቀመጣቸው የመደራደሪያ ነጥቦች አንዱ በመሆኑ የአማራ በተለይ የጎንደር ወልቃይት፣ሰቲት ሁመራ፣ ጠገዴ እንዲሁም የወሎ ራያ ህዝብ ውገብህን ጠበቅ ማድረጉ የግድ ይላሃል እንላለን።
በዚህ ላይ የታዘብነው ይሂን ቅጥ ያጣ አካሄድ ሁሉም የኢትዮጵያ ሕዝብ ሊያወግዘው ይገባል “ የአንዱ ቤት ሲቃጠል ዝም ያለ ጎረቤት ፍሙ ለሱ ነውና” ይታሰብበት።
- 5) ይቅርታና ምህረት የሚሉት አባዜ እንደ ዳቦ ለማንም እየተቆረሰ የሚሰጥ አይደለም። “ማርም ሲበዛ ይገለማል” እንደ ኢሕአዲግና ሕወሃት ትግራይ ስንት ጊዜ ይቅር ተባላችሁ። አልበዛም!
- 6) ሰራዊቱ የትግራይ መሬት የኢትዮጵያ መሬት አካል እንደመሆኑ በትኩሱ ገፍቶ ነፃ ማውጣት ከማስቻል ፈንታ ለድርድር ሲባል ድንበር ላይ እንዲቆምና እንዲያፈገፍግ ማድረግ ከሽንፈት የማይተናነስ ሲሆን ያአለፉት የኢትዮጵያ ነገስታት እንዲህ ያለ ድርጊትም አላደረጉም ፣እርማቸውም ነው፣ አልሞከሩትምም። ለሽፍታ ከተማን ለቆ መውጣት እቅም እያለ ምን የሚሉት ነው፣
- 7) ሕዝብን ለመባበል በኢትዮጵያ አንድነት፣ጀግንነት ስምና የወደፊት ተስፋ በማቀንቀን ስህተትን ለማደባበስ መሞከር ትዝብት ውስጥ ይጥላል፣በታሪክም ያስወቅሳል፣
- 8) በአስቸኳይ እርምት ይወሰድ፣ የዚህ ሁሉ ሸፍጥ ምክንያት በግልፅ ለህዝብ ቀርቦ ውይይት በአስቸኳይ ይደረግ፣
- 9) የብልፅግና መንግሥት ስር ነቀል የሆነ ለውጥና መፍትሄ ማምጣት ካልቻለ የሶስት ዓመቱ ስቃይ በየትኛውም ዘመን ያልታየ፣ብዙ ንብረት የወደመበት፣ደም እንደ ጎርፍ የወረደበትና ወ.ዘ.ተ. ስለሆነ እንደ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኃይለ ማርያም ስልጣኑን ለቆ ለጀግኖች፣ለቆራጦች፣የኢትዮጵያን አንድነትና ሰላም ሊያስጠብቁ.
ለሚችሉ ማስተላለፍ “ሳይቃጠል በቅጠል” ነውና ምክራችን ጀባ እንላለን። ሃገርን ማዳን ከቅድስና የበለጠ ቅድስና ሲሆን የኢትዮጵያ አምላክ የሚሻው ገቢር ነው።
ተዘራ አሰጉ- ከምድረ እንግሊዝ