ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እና ካቢኔያቸው ጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ ተገኝተዋል

0
0 0
Read Time:51 Second

የአዲስ አበባ ከንቲባ እና ካቢኔያቸው ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2014 ዓ.ም በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የቅዱስ ሲኖዶስ መሰብሰቢያ አዳራሽ ተገኝተዋል።

ቋሚ ሲኖዶስ የካቲት 4 ቀን 2014 ዓ.ም በመስቀል አደባባይ፣ በወይብላ ማርያም ጉዳይ፣ በጃንሜዳ ባህረ ጥምቀት እና በሌሎች የቤተ ክርስቲያን ይዞታዎች ዙሪያ ተወያይቶ አሉ የሚባሉ ችግሮችን በሰላማዊና በህጋዊ መንገድ ለመፍታት ይዞት የነበረው ቀጠሮ በወቅቱ የከተማ አስተዳደሩ ምክር ቤት ስብሰባ ስለነበረውና ከንቲባዋም በዚያ መገኘታቸው የግድ ስለሆነ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር የነበረው ቀጠሮ ለዛሬ እንዲተላለፍ የከተማ አስተዳደሩ ምክትል ከንቲባና ከአስተዳደሩ የተወከሉ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በአካል ተገኝተው ለቋሚ ሲኖዶስ በገለጹት መሰረት የውይይቱ ጊዜ ለዛሬ እንዲተላለፍ መደረጉ ይታወሳል።

በዚህም መሰረት ከንቲባዋና የካቢኔ አባላቶቻቸው ዛሬ በሰዓቱ በጽርሐ መንበረ ፓትርያርክ የተገኙ ሲሆን ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት በተጨማሪ ሌሎች ብፁአን አባቶች ፣ የህግ ባለሙያዎች ፣ ከመምሪያ ኃላፊዎች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

በውይይቱ አሉ የሚባሉና ቤተክርስቲያን የምታቀርባቸው ጥያቄዎች ሁሉ ፍጹም ሰላማዊና ህጋዊ በሆነ መንገድ መፍትሔ የሚያገኝበትን ሁኔታ ይፈጥራሉ ተብሎ እንደሚገመት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ገልፃለች።

ከዚህ ቀደም በቋሚ ሲኖዶስ አባላት እና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ መካከል ሊደረግ የታሰበው ውይይት በተለያዩ ምክንያቶች እንቅፋት እየገጠመው መቆየቱ ይታወሳል።

መረጃው ፦ የኢኦተቤ ህዝብ ግንኙነት ነው።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *