0 0
Read Time:2 Minute, 34 Second

ሐኪም ወርቅነሀ እሸቴ (ሃኪም ቻርለስ ማርቲን ወርቅነሀ እሸቴ )በ1857 ዓ.ም. በጎንደር ልዩ ስሙ ቈራ በተባለ አካባቢ ከአባታቸው አዛዥ እሸቴ ወ/ማርያም እና ወ/ሮ ደስታ ወ/ማርያም ተወለዱ፡፡ ሐኪም ወርቅነሀ የ3 ዓመት ህፃን ሳሉ ቤተሰባቸው አፄ ቴዎድሮስን ተከትሎ ወደመቅደላ አምባ ሄዶ ነበር፡፡ ከጦርነቱ ፍፃሜ በሁዋላ የአፄ ቴዎድሮስ ልጅ አለማየሁ ቴዎድሮስ እና ወርቅነሀ እሸቴ ተማርከው ነበር፡፡ በዚህም ምክንያት ኮሎኔን ቻርለስ ቻምበርሊን ወደ ህንድ ወስደዋቸው ነበር፡፡ ትምህርታቸውንም ወደ ፑንጃብ ዩኒቨርሲቲ በመግባት በህክምና ሙያ ተመርቀው በረዳት ሐኪምነት ሰርተዋል፡፡ ከሁለት ዓመት አግልግሎት በኋላ ለከፍተኛ ትምህርት ወደ እንግሊዝ ሄደው ግላስኮ ዩኒቨርሲቲ ገብተው በቀዶ ጥገና ሙያ በታላቅ ክብር ተመርቀዋል፡፡ ሲመረቁም ከሀኪሞች ማህበር ’’የመጀመሪያው ባለአንጎል ጥቁር ሐኪም ’’ የሚል የምስክር ወረቀትና መቀስ ተሸልመዋል፡፡

አንደተመረቁም የአንግሊዝ መንግስት ራሳቸውን ችለው ቀዶ ጥገና ስራቸውን አንዲያከናውኑ ያኔ በአንግሊዝ ስር ወደነበረችው በርማ ላካቸው፡፡ በወቅቱ ለአጼ ምኒልክ ቅርበት ከነበራቸው ምሁራን መካከል አለቃ አጽሜና አለቃ ታዬ የሚባሉት ስለሃኪም ወርቅነህ ዝና አውሮፓ ሳሉ የሰሙትን አንድ ባንድ ነገራችው፡፡ አጼ ምኒልክም ሐኪም ወርትነህ ወደኢትዮጵያ መጥተው የህክምና ሥራ ኦንዲሰሩ እንዲፈቅዱላቸው ለእንግሊዝ መንግሥት ደብዳቤ ጻፉ:: የእንግሊዝ መንግሥት “በሁለታችን መካከል ያለውን ወዳጅነት ለማጥበቅ ቻርለስ ማርቲንን ስንልከው ለእርዎም ያለንን አክብሮት ለመግለጥ ነው” በማለት መፍቀዳቸውን በመግለፅ ሐኪም ወርቅነህን ላኳቸው፡፡ ሐኪም ወርትነህ ያኔ የ36 ዓመት ጎልማሣ ነበሩ፡፡ ኢትዮጵያ ውስጥ ገብተው ጥቂት ዓመታት ያህል እንዳገለገሉ በ1894 ዓ ም ኦጋዴን ውስጥ በኢትዮጵያና በሱማሊያ ድንበር ሸፍቶ የነበረ ሰው ለመያዝ በተደረገ ጦርነት፤ በጦርነቱ ቁስለኛችን ከቦታው ድረስ ሄደው ያከሙት ሐኪም ወርትነህ ናቸው፡፡ በ1895 ዓ ም እንደ ገና ወደእንግሊዝና በርማ ሄዱ፡፡ በዚያ አምስት ዓመት ሲቀመጡ ከእንግሊዛዊትና ከበርማ ሴቶች ልጆችን ኦፍርተዋል። በ1903 ዓ ም እንደገና ወደኢትዮጵያ በመምጣት ኢትዮጵያዊ አግብተው 13 ልጆችን አፍርተዋል፡፡ ሐኪም ወርቅነህ በድጋሚ በመጡ ጊዜ አጼ ምኒልክ የአውሮፓን ስልጣኔ ወደአገራቸው እያስገቡ ነበር፡፡ ሐኪም ወርቅነህ በማስተማርና በህክምና የቻሉትን ያህል አጼ ምኒልክን ደግፈዋል፡፡

አጼ ምኒልክ በታመሙ ጊዜ በመጀመሪያ ሙሴ ሃርማኒየር ሲያክሙ ቆይተው በኋላ ሐኪም ወርቅነህ በቦታው ተተአተው ማከም ቀጠሉ፡፡ በ1906 ዓ ም (ከአጼ ምኒሊክ እረፍት በኋላ ሐኪም ወርቅነህ ወደ በርማ ተመለሱ:: ከአንድ አመት በኋላ መኳንንቱ ሁሉ በስልጣን ሽኩቻ ውስጥ ገብተዋል እየተባለ በሚወራበት ወቅት በ1909 ዓ ም ገደማ ወደአገራቸው መጡ፡፡ በዚህ ጊዜ የእንግሊዝ መንግሥት ጉዳያችውን በልዩ ሁኔታ በማየት ጡረታቸው አክብሮላቸው ነበር:: ሐኪም ወርቅነህ በመጨረሻ ወደኢትዮሉያ እንደመጡ በትምህርት ቤት ሥራ አመራር፣ በፍርድ ቤት በህክምናና በዲፐሎማሊ መስኮች እየገቡ ሁለገብ አገልግሎት አበርክተዋል፡፡ሌላው ቀርቶ የአሁኑ ብርሃንና ለላም ማተሚያ ሲቋቋም በነበሩባቸው ኃላፊነቶች ላይ የሥራ አስኪያጅነቱን ቦታ ደርበው በመስራት ቅን ታዛዥነታቸውን ኦሳይተዋል፡፡
ቀጥሎም የተፈሪ መኮንን ት/ቤት በተስራ ጊዜ አስተዳዳሪ በመሆን አገልግለዋል፡፡ ከዚያም በኋላ በጨርጨር አውራጃ ገዥ ሆኑ፡፡፡ ቀጥሎም በእንግሊዝ የኢትቶጵያ ለምባሳደር ሆነው ተሾሙ፡፡ እንግሊዝ አገር እንዳሉ የጣሊያን ወረራ ተጀመረ:: በዚህ ጊዜ ሐኪም ወርቅነህ የገንዘብ መዋጮ እየሰበሰቡ ይረዱ ነበር፡፡ የገንዘቡ ድጋፍ ማድረግ ብቻም አልነበረም ለጦርነቱ ያበረከቱት አስተዋጽዎ:: “ኢልስትሬተድ ለንደን ኒውስ” በተባለ ጋዜጣ ከፎቶግራፋቸወ ጋር “የውጭ አገር የጦር መኮንኖችን ከኢትዮጵያ ወገን ተሰልፈው ለመዋጋት የሚፈልጉ በኢትዮጵያ ለጋሲዮን መጥተው እንዲመዘገቡ” ጥሪ ተላለፈ የሚል ማስታወቂያ እያተሙ ያሰራጩ ነበር፡፡ በዚህ ማስታወቂያ ተስበው ወደኢትዮጵያ መጥተው ከተዋጉት የውጭ ተወላጆች አንዱ የኩባ ተወላጅ የሆኑት ኮሎኔል ኦልኸንድሮ ዴል ባዬ ተጠቃሽ ናቸው፡፡ ሐኪም ወርቅህ የሚያደርጉትን የተቃውሞ ትግል ለመበቀል ይመስላል ጣሊያኖች ዮሴፍ ወርቅህና ብንያም ወርቅህ የተባሉ ልጆቻቸውን በ1929 ዓ ም አዲስ አበባ ላይ ገድለውባቸዋል:: ከሐኪም ወርቅነህ ታዋቂ ልጆች መካከል ዶ/ር ዮሃንስ ወርቅነህ፣ አስቴር ወርቅነህና ኤልሳቤጥ ወርቅነሀ ተጠቃሾች ናቸው፡፡ ከነጻነት መልስ ለተወሰነ ጊዜ መደህንድ ሄደው የቆዬ ሲሆን በመጪረሻ ከቤተሰባቸው ጋር ወደአገራቸው ለመመለስ በቅተዋል፡፡ በ1954 ዓ ም ማለትም በተወለዱ በ95 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተው በየካ ሚካኤል ሥርዓተ ቀብራቸው ተፈፀሟል፡፡

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
100 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *