ብአዴን ቅርጫፍ ነው መገንደስ ግንዱን ከስሩ ነው

0

የዐማራ ብልህነት ፡ ጥበብ አዋቂነት፣ አስተዋይነት፡ ፈሪሃ እግዛብሄርነት ፡ ጀግንነት ሲነገር ነው የኖረው፡፡ እውነቱም ያ ነው፡፡ ነገር ግን ብአዴን የተባለው ስብስብ ከዐማራ እናት መሐፀን የወጣ እስከማይመስል ድረስ ፡ አስመሳዮች፡ አድር ባዮች፡አሽከሮች፡ ሆዳሞች ፡ ከሃዲዎች ፡ የእናት ጡት ነካሾች፡፡

0 0
Read Time:8 Minute, 5 Second

የአማራ ትግል ለድል እንዲበቃ ታጋዩ አና አታጋዩ ከንኡስ ከበርቴው አዙሪት መላቀቅ አለበት

ከኢያሲ ኤፍሬም ፡ የካቲት 28 2014 ፡ ለንደን 2022 ማርች 7, ሰኞ፡ ዐማራ ንቃ ፡፡ አምብቡት ፡ አጋሩት ፡ ተቹት

በዐምሓራ የሕልውና ትግል ውስጥ ያሉ ሁሉ ኢህዴን/ብአዴን/አዴፓ/ የአማራ ብልፅግና የሚባለውን የከዳተኞች ስብስብ አጥበቀው ይጠላሉ ይጠየፋሉ፡፡ የጥላቻቸው መነሻ ምን እነደሆነ የአዳባባይ ሚስጢር ነው፡፡ ብአዴን በዐማራ ገላ ላይ የተጣበቀ አልቅት እና መዥገር ፡ ቅማል እና ቱሃን መሆኑን ተደጋግሞ ተነግሯል፡ አዎ ይህን እራሳቸው መስከረዋል፡፡ ተላላኪ እና አሽከር ነበርን ብለዋል፡ከ60 ሚሊዮን እስክ 2 ቢሊዮብ ብር በጠራራ ፀሐይ ከመዝፈር በላይ ሌላ ማስረጃ አይገኝም ፡፡

የዐማራ ብልህነት ፡ ጥበብ አዋቂነት፣ አስተዋይነት፡ ፈሪሃ እግዛብሄርነት ፡ ጀግንነት ሲነገር ነው የኖረው፡፡ እውነቱም ያ ነው፡፡ ነገር ግን ብአዴን የተባለው ስብስብ ከዐማራ እናት መሐፀን የወጣ እስከማይመስል ድረስ ፡ አስመሳዮች፡ አድር ባዮች፡አሽከሮች፡ ሆዳሞች ፡ ከሃዲዎች ፡ የእናት ጡት ነካሾች፡፡ ወረደው ወርደው ተራ ተራ ሌባ እና ቀማኖች መሆናቸውን ጊዜ ደጉ አጋልጧቸዋል፡፡ አቶ ፀጋ አራጌ ምስጋና ይገባው ዛሬ ብአዴንን በሌቦች መዝገብ ውስጥ በቅሌት እንዲመዘገቡ አድርጓል፡፡ የብአዴንን እኩይ ባሕሪ የአማራ ሕዝብ ጠንቅቆ ቢያቀውም ይህን ጉዳይ የዐማራ ሕዝብ ሲናገር አባይ ሲባል ነበር የከረመው ፡፡ አገኘሁ ተሻገር እና አጋፋሪዎቹ ህዝቡን በውረደት እና በስድብ ሲያጥረገርጉት እንደነበር የቀርብ ጊዜ ትውስታ ነው ፡፡ ዐማራ በባዶ እግሩ እየሄድ፡ ትምክህተኛው አማራ ወዘተ ብአዴን ተብየው የእወክላለሁ የሚለውን ዐማራን የሚገልፅበት ስንኞች ናቸው፡፡ ለብአዴን አመራሮች የሚያሳዩት እኩይ ባሕሪ በድነግት የተከሰተ አይደለም ለነገሩ ጥሩ ሳይሳዊ ትንታኔ አለው፡፡ ተከተሉኝ

በሚያሳዝን መልኩ ብአዴን የተባለው ስብስብ ወደ 3.8 ሚሊዮን አባል ( ካድሬዎች) ያሉት ትልቅ ስብስብ ነው:: ይህ ቁጥር በቀላል የሚገመት አይደለም ፡፡ በትንሹ በትግራይ ወይም በሱማሌ ክልል ሊኖር ክሚችለው አምራች ወይም ከ18 እስክ ከ65 ያለው የሕዝብ ብዛት ማለት፡፡ ይህን በቤተስብ ብናሰላው ወደ 10 ሚሊዮን ሕዝብ የሚወከል ነው (አንድ የትዳር ጓዳኛ እና ሁለት ልጆች በአማካኝ ቢኖረው በሚል እሳቤ)፡፡

አፍንጫ ሲመታ አይን ያለቅሳል ነው እና ብአዴን በክፉ በሚነሳበት እና በሚወቀስበት ወቅት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንግድ ከድርጅቱ ጋራ ንክኪ እና ዝምድና ያለው ነፈስ ሁሉ እንደ ንክኪው ደረጃ እና መጠን ብአዴን ሲቆነጠጥ የማያመው የያማኩረፉ የማይቀየሙ የለም ፡፡ ለምሳሌ በቅርቡ በ60 ሚሊዮን ብር ስርቆት የተጋለጡት የብአዴን አመራሮች ትዳር ያላቸው ልጆችም ያፈሩ በዙሪያቸውም ዘመድ አዝማድ እና የልብ ጓዳኖች ያሏቸው ናቸው፡፡ እነ አገኘሁ ተሻገር 60 ሚሊዮን ብር እንደ ቀልድ ቅርጫ ሲያደርጓት ሲጀመር ከቤተሰባቸው ቀጥሎ በአካባቢያቸው ያሉንት ሰዎች ተጠቃሚ ማድረጋቸው አይቀርም ፡፡ ይህ ውስብስብ ማሕበራዊ ቀመር ወይም ሜትሪክ የዐማራውን የሕልውና ትግል እጅግ ውስብስብ ጥለፍለፍ እና አዳጋች አድርጎታል፡፡ ብአዴን ሌባ ነው ስትል የአገር እና የዐማራ ተቆርቋሪ መስሎ የሚተችህ ሰው ከአገኘሁ ተሻገር እጅ በቅቤ የራሰ ቦዘና ሽሮ የጎረሰ ይሆናል ፡፡ አብይ አሻጋሪያችን ነው ኢትዮጵያ ምትደነው በአብይ ነው ብሎ ማሲንቆ ይዞ የሚቀውጥ ዐማራ ካየህ ከ60 ሚሊዮኑ ላይ በ900 ብር ብሩንዶ የበላ መሆኑ ይገባህ፡፡ ውሻ በበላበት ይጮሀል ይባል የለ፡፡ ብዙ ውሾች አሉ፡፡ የዐማራም አንዱ ፈተና ይህ ነው ፡፡ ይሰመርበት

በዐማራ የሕልውና ትግል ውስጥ ያሉ ኃይሎች ትግላቸውን ሲያራምዱ ከላይ ያስቀመጥኩትን ነጥብ ከግምት ውስጥ ማስገባት ካለቻሉ ለሕልውና የሚደረገውን ትግል ይበልጥ አስቸጋሪ ያደርገዋል ፡፡ ለምን የሚለውን አስረዳለሁ፡፡ ብዙ ጊዜ እንደሚባለው የዐማራ ሁነኛ ደም መጣች እና አስመጣች ቱሃኑ ብአዴን ነው ( ጥርጥር የለውም)፡፡ የዐማራን ደም መፍሰስ እና መመጠጥ ለማስቆም ቱሃኑን ብአዴንን ቀድሞ ማጥፈት የመጀመሪያው መፍትሄ ነው የሚሉ አሰላለፎች አሉ፡፡ ከነ ብሄሉም ፡ ጠላትማ ጠላት ነው ፡ አስቀድሞ መምታት አሾክሻኪውን ነው፡፡ ይባል የለ ፡፡ ከሞላ በጥቂቱ የሰኔ 15ቱ ክስተትም ( ሌሎች ሴራዎች እንደ ተጠበቁ ሆነው) የእዚህ ቅኝት ውጤት ነው፡፡ እነ ዶክ አምባቸው ነፈሳቸውን ይማረው እና ከመሰዋታቸው በፊት በአደባባይ ( በማሕበራዊ ሚዲያ) በወቅቱ የነበሩትን አመራሮች ትቅነደሻለህ ሲሉ የነበሩ ሰዎችም ነበሩ ፡፡ በጆሮዬ አዳምጫለሁ፡፡ ወያኔ ወደ አዲስ አበባ በመገስጋስ ላይ ባለችበት ወቅትም ወያኔን ወደ አዲስ አበባ እንድትገባ ማገዝ እና የዐማራ ሕልውና ተፋላማዊች ደግሞ ወደ ባሕር ዳር ሄደው ብአዴንን በማሶገድ የዐማራን ነፃት ማወጅ አለብን ብለው የሚከራከሩ ወገኖችም አልታጡም፡፡

አሁንም ቢሆን ለዐማራው ሕልውና እንዲሁም ለኢትዮጵያዊነት የሚደረገው ትግል የክልል አመራሮችን በማሶገድ የመጀመሪያው እና ግንባር ቀደም የትግል ስልት ነው ብለው የሚያስቡ ቁጥራቸው ቀላል የማይባል ኃይሎች አሉ፡፡ ከዛም አልፎ በወለጋም ሆነ በተለያየ ቦታ በግፍ የሚገደሉትን ወገኖች ለመታደግ አማራጭ መንገዱ በቀጥታ ወደ ወለጋም ሆነ ወደ መተከል መዝመት ነው ብለው የሚያሳስቡ የኃይል አሰላለፎች አሉ ፡፡ ይህንንም ማስታወሻ እንድፅፍ ያነሳሳኝ ይህ ግድፋታዊ አካሄድ ነው፡፡ ለም በሉኝ ፡፡

ታሪከን ለማጣቀስ ፡ በማርክስ እና በማአ ፍልስፍና የተጠመቀችው ኢሕአፓ የትጥቅ ትግል አካሄዳለሁ ብላ የሆቺሚን ፈለግ በመከተል አሲምባ ላይ ከትማ ነበር (አስታውሱ መዝሙሩም ፋኖ ተሰማራ ፋኖ ተሰማራ እንደ ሆቺሚን እንደ ቼጎቬራ ነበር)፡፡ ነገር ግን በፓርቲው በውስጥ በተፈጠረው የፖለቲካ ሽኩቻ እና የትግል ስልት አሰላልፍ ልዩነት የከተማ ሽብር በማካሄድ ስልጣን እንረከበለን ብላ በመነሳቷ የደረሰባት ውድመት ብዙዎቻችን እናውቃልን፡ ደርግም ዲሞን በዲምትፎር ብሎ ወጣቱን አረደው፡፡ የአዲስ አበባም ጎዳናዎች በደም ታጠቡ፡፡ ይህን አስመልክቶ የጎንደር እናት ይህን ብላ ነበር ፡ መላኩ ተፋራ የአምላክ ታናሽ ወንድም ፡ ይህንን ማርልኝ ደግሜ አልወልድም፡፡ ጎንደሬም አገር ነቅሎ ዴንቨር ከተመ፡፡ በተመሳሳይ ሂኔታም መኢሶን ( የሙሁራኖች ስብስብ) ደርግ ጉያ ውስጥ ተወሽቆ ስልጣን ሲቀላውጥ በመጨረሻው ተስልቅጦ ቀረ፡፡ እሱም ተሰብስቦ ሚኖሶታ ኬኛ አለ፡፡ የሁለቱ አንጋፋ የፖለቲካ ድርጅቶች ስህተት እና ውድቀት ብዙ ያስተምረናል የሚል እምነት አለኝ ፡፡ የሚማር ካለ፡፡

ይህንን እይነቱን ክስተት ማርክሲስቶች ሲተነትኑት የንኡስ ከበርተው ባሕሪ ውጤት ነው ይላሉ ፡፡ ንኡስ ከበርቴው በባሕሪው ቁርጠኝነት የሌለው ፣ ጀብደኝነት የሚያበዛ ፣ ከተጨባጭ ሁነታ የራቀ እና በተሰፋ እና በሕልም የሚገላወድ ፣ አቋራጭ መንገድ ፈላጊ፣ መደባዊ ታማኝነት የሌለው፣ ዝርክርክ ፣ ወላዋይ እና የሚዋዥቅ ነው ብለው ያበራዩታል፡፡ ይህ መደብ ለፖለቲካ ትግል ዋንኛ መሳሪያ ግን አደገኛው መደብ ነው ብለው ይፈርጁታል ፡፡ ይህ መደብ ባንዳ እና አድር ባይ ለመሆን በጣም ቅርብ ነው፡፡ የኢሕአፓ ሆነ የመኢሶን እንዲሁም የብአዴንኑ ክህደት እና የ60 ሚሊዮን ብር ቅሌት ምንጩ መደባዊ ባሕሪያቸው ነው፡፡ በሌላም በኩል ወጣ ወጣ እና እንደ ሻምበቆ ተከባለለ እንደ ሙቀጫ የተባለለትም ትህነግ ውድቀት ታሪካዊ ምንጩ ይህ መደባዊ ባሕሪው ነው፡፡ በነገራችን ላይ ወያኔ ይህ የውድቀቷ ምንጭ እንደሚሆን ጫካ ሆነ ተብያለች፡፡ ግን አልቀረላትም ውስኪ፡ አቶሞቢል እና ኮረዳ የወያኔን ትግል በላው፡፡

ዛሬ የአገሪቱን ባንክ እና ታንክ የተቆታጠረው የኦሮሙማው ኃይል አራት ኪሎ ተቀምጦ ስልጣኑን በማናቸውም ዋጋ ለማስጠበቅ ከፍተኛ የስነ ልቦና፣ ቁሳዊ ፣ ወታደራዊ፣ ማህበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ዲፕሎማሳዊ ዝግጅት አድርጓል እያደረግም ነው፡፡ አብይ ከወያኔ በወረሰው ሴራ እና ተንኮል እንዲሁም ከሚኖሶታ ፈልሶ በመጣው በኦነግ ባጠናከረው መዋቅር በኦሮሙማ ስም የራሱን እና የገዳን የበላይነት ለሚቀጥሉት አመታት እንዲያውም ሺ ( እንደ ሌጮ ግምት) ለማስጠበቅ እየሰራ ነው፡፡ ለእዚህም እንደ ብአዴን ያሉ አገለጋይ እና ሎሌ ድርጅቶች በማጠናከር እና እንደ አብን እና ኢዜማን የመሳሰሉት ትኩስ አገልጋዮች በመመልመል የኢትዮጵያን ሕዝብ በተለይ ዐማራውን በእገረ ሙቅ ቀፍድዶ አስሮታል ፡፡ ኢትዮጵያንም መቀመቅ እያወረዳት ነው፡፡

ቅርንጫፉ እንዲወድቅ ግንዱን ቁረጠው

የዐማራ ሕዝብ ሆነ የኢትዮጵያ ሕዝብ ከታሰረበት የእገረ ሙቅ ለመላቀቅ ከፈለገ አንድ ብሎ ከታሪክ እና ከሌሎች ጥፋት መማር አለበት፡፡ ሁለትንም በመሬት ላይ ያለውን ወቅታዊ እውነታ በቅጡ መረዳት ፡ ማጥናት እና በተንተን ያስፋለገዋል፡፡ ሶስተኛም የዐማራውን ፖለቲካ የሚዘውሩት ስብስቦች መደባዊ ባሕሪያቸው ከብአዴን፡ ከትህነግ ወይ ከኦሮሙማ የተለየ ባለመሆኑ ያንን መደባዊ ባሕሪያቸውን በእንዶድ አጥበው መንፃት አላበቸው፡፡ በእርግጥ ቁጥሩ ትንሽ የማይባለው የዐማር ፖለቲካኛ እኔንም አክሎ ስልጣን እንደ ቡና ቁርስ ቂጣ ተጋገሮ እና በኑግ ተለውሶ ከአቦል ቡና ጋራ ጀባ እንዲባል የሚሻ ነው ፡፡ ሌላውም በትንሽ ዝና ተኩራርቶ በአገር ሰላም በኮማንዶ ታጅቦ ሲጎባለል ታገኘዋልህ፡፡ አንድ ሰው እንዳለው በማህበራዊ ሚዲያ ያገኙትን ዝና እና ስልጣን እንደ ግብ የቆጠሩም ቀላል የማይባልሉ የዐማራ ፖለቲካ አቀንቃኞች አሉ፡፡

ከላይ እንደጠቀስኩት አንዳንድ የዐማራ የሕልውና ትግል ኃይሎች ብአዴንን ነጥሎ በመምታት ነፃነት ይገኛል ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ አካሄድ ከአዚህ ቀደም ኢሕአፓ በመደባዊ አሰላለፏ ቆሜለታለሁ ክምትለውን የማሕበረስብ ክፍል የተመለመለውን የቀበሌ አብዮት ጥበቃ ከመግደል ወይም ከማሰገደል ጋራ ተመሳሳይነት ያለው ነው ፡ ይህን ወደ የብአዴን ስንወሰደው የሚከተለውን ምስል ይሰጠናል ፡፡ ለምሳሌ አንድ የብአዴን አባል ማስወገድ ማለት በመጀመሪያ ደረጃ ሚስቱን እና ልጆቹን ደመኛ ማድረግ ሲሆን ቀጥሎ ደግሞ ከዘመድ አዝማዱን ጋራ ደም መቃባትን ያስከትላል፡፡ ያ ማለት ለዐማራ ሕልውና እታገላለሁ የሚለው ክፍል ከአማራ ወገኑ ጋራ ደም በመቃባት እቆምለታለሁ ካለው ዐማራ ላይ በሕልውናው መጣ ማለት ነው፡፡ በእዚህ በኩል ኦሮሞቹ የተሻለ እሳቤ እንዳላቸው አሳይተዋል ፡ በተግባር ይተርጎም አይተርጎም ሌላ ነገር ሆነ ( የአጫሉን መገደል ሳንረሳ) ኦሮሞ ኦሮሞን አይገልም የሚለው ምልከታ ሊያስተምረን የሚገባ ቁም ነገር አለ፡፡ አብይ ጁዋርን እና ለማን ካለመግድል አተረፈ እንጂ አላጎደለም፡፡ ከእዚህ መማር ያለብን በፅንሰ ሐሳብ ደረጃ ዐማራ ዐማራን መግደል የለበትም የሚለውን ነው፡፡

ዛሬ በዐማራ ሕልውና ትግል ውስጥ እንደ ትለቅ ድክመት ተደርጎ የሚታየው በእኛ ውስጥ ያለው መካፋፈል መጠላለፍ እና ለግድያ መፈላለግ ነው፡፤ በአዚህ በኩል እንደ ብአዴን የተካነ እና በዐማራም ላይ መርገምት ሆኖ የተፈጠረ የለም ፡፡ ወያኔ ወይም ኦሮሙማ ከገደለው ዐማራ በላይ እነ ደመቀ መኮንን ፡ እነ አገኘሁ ተሻገር፡ እነ ተመስገን ጥሩነህ የገደሉት ያስገደሉት ፡ ያሳደዱት፡ ያፈናቀሉት ፡ ያጎሳቆሉት ዐማራ ቁጥሩ እጅግ በጣም ብዙ ነው፡፡ በኦሮሚያ እና በመተከል ለሚገደለው ዐማራ አለመቆም እና ከሰለባዎች ጎን አለመሰለፍ ዐማራን ከጀርባ ከማረድ የሚተናነስ ተግባር አይደለም፡፡ ለነገሩ ከክልሉ ውጭ ያለውን ዐማራ ምንታገለለት ሳይሆን ምንታገለው ነው ያለው ብአዴን አይደለምን፡፡ የዐማራን ገዳዬች ካባ እያለበሱ ፡ እያሞገሱ ፡ ዐማራን በአደባባይ እያዋረዱ እየሰደቡ የዐማራ ሕዝብ ተወካይ ነኝ ፡ ዐማራ ነኝ ማለት ይሁዳ ክርስቶስን በዲናር አልሸጠም የማለት ያህል ያስቆጥራል፡፡

ከላይ የጠቀስኩት መራራ ሃቅም እንደለ ሆኖ ብአዴንን ነጥሎ በመምታት ከሚገኘው ጥቅም ይለቅ ጉዳቱ ያመዝናል የሚል መከራከሪያ ነጥብ አለኝ በመጀመሪያ ደረጃ 3.8 ሚሊዮን ብአዴን አንድ አይነት ነው ብሎ ማሰብ አስቸጋሪ ነው፡ ሌላው ቢቀር በከፍተኛ አመራር ፡ በመካከለኛ እና በታችኛው አመራር መካከል ብዙ የልዩነት መስመሮች አሉ ፡፡ ከእነዚህም ውስጥ ፖለቲካዊ ሽኩቻ፡ ኢኮኖሚያዊ ( የጥቅም ሽኩቻ) ፡ የስልጣን ሽኩቻ፣ ወንዛዊነት፣ የትውልድ ዘመን ልዩነቶች ፤ የግንዛቤ ልዩነቶች ከብዙ በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ስለሆነም ሁሉንም በአንድ ቋት አስገብቶ ክመፈረጅ በውጣቸው ያለውን ልዩነት በማጥናት ለዐማራ ሕልውና ትግል መጠቀም አስፈላጊ እና ብልሃተኝት ብዬ እሞግታለሁ፡፡

በሌላም በኩል ብአዴን የትልቁ ብልፅግና ዛፋ ቅርጫፍ ነው ፡፡ ብአዴን እራሱን ችሎ የበቀለ አይደለም ሲጀመር በወያኔ ዛፍ ላይ የበቀለ ፍሬ አልባ ፍሬም ቢኖረው መርዛማ ቅርጫፍ ነው ሲቀጥል ያንን ዛፍ እና ቅርጫፍ የተረክበው ኦሮሙማ ነው፡፡ ልክ እንደ ዐማራው ብልፅግና ፡ የአፋር ፡ የትግሬ ፡ የደቡብ ፡ የሱማሌ ፡ ወዘተ ብልፅግናዎች አሉ፡፡ እነዚ ሁሉ ቅርጫፎች አንድ ላይ ተባበረው እንደሚሰሩ እንገዝብ፡፡ ቅርጫፍ ቢቆረጥ ቅርጫፍ ያድጋል፡ ይህ ደግሞ የሰኔ 15 አሳዛኝ ክስተት አስተምሮን ያለፈው እውነታ ነው፡፡ ብአዴን ቅንርጫፍ መሆኑን ለመረዳት አብይ ከመጣ ጀምሮ የተፐወዙድ የክልሉ አመራሮችን መመልከት በቂ ነው፡፡ የሐብታም ቤት ዘበኛ እና የቤት ሰራተኛ እንኳን ለብዙ ዘመን ያገለግላሉ፡፡

እንግዲህ ከላይ ባቀረብኩት መከራከሪያ ነጥብ ከተስማማን ( ላለመስማማትም ይቻላል) እውነተኛ ለውጥ ለማምጣት ከተፈለገ ከስሩ መገንደስ ያለበት አራት ኪሎ ያለው ዋርካ እንጂ ባሕር ዳር ያለው ቅርጫፍ አይደም፡፡ የትግሉ መጥረቢያ መሳል እና መቈረጥ ያለበት አራት ኪሎ ያለውን ግንድ ነው ፡፡ ግንዱ ተቆርጦ ሲወደቅ ቅርጫፉ ይወድቃል ከዛፉም ላይ ያሉ ተባዮች አብረው ይረግፋሉ፡፡ ቁራም እባቡም ካለ አብሮ ይከሰከሳል፡ዛፉም መልሶ እንዳያቆጠቁጥ ከስሩ መንግሎ ማቃጠል ግድ ይላል፡፡ ይህ እንዳይሆን ግን ከላይ ለማብራራት እንደሞከርኩት በዐማራም የሕልውና ትግል ውስጥ ያሉት እና በግንባር ቀደምትነት የሚታገሉ( ሙሁራን ማለት ይቻላል) መደባዊ ባሕሪያቸውን ተከትሎ የሚመጣ ተግዳሮቶች አሏቸው ፡፡ እነዚህን ተግዳሮቶች ጠንቅቆ በመረዳት የተግዳሮቶቹ ሰለባ ላለመሆን መሰራት ያስፈልጋል፡፡ ዛሬ አብይ የአብን አመራሮችን በአንቀልባ ያዘላቸው እና እነሱም የታዘሉት አብይ በተሻለ መልኩ መደባዊ ባሕሪያቸውን ስለተረዳ ነው፡፡ አብይ ተውሶ እንዳለው ሰው የሚፈለገውን እያደረክለት ወደ ምትፈለገው ቦታ ውስደው ወይም በሬ ሆይ በሬ ሆይ የሚለውን መርሆ በመከትሉ ነው፡፡ የዐማራ የሕልውና ትግል ከእዚህ አዙሪት ውስጥ እንዲወጣ ከተፈለገ የንኡስ ከበርቴው መደባዊ ባሕሪያቶችን ከትግሉ ማፅዳት አለብን ፡፡ የፖለቲካ ትግል እና ስልጣን በቅርብ ተዥርግጎ የተጠለጠለ የወይን ፍሬ አይደለም ይልቁንም አመታትን ጠብቆ እንደ ሚበቀል ቀሰ ብሎም እንደሚያጎመራ መልካም የዛፍ ፍሬ እንጂ፡፡ በተለይ ወጣቱ ሊያውቅ እና ሊረዳው የሚያስፈለገው ነገር አየር በአየር ፖለቲካ አለመኖሩን ነው፡፡ ብአዴንን ብቻ በማስወገድ የሚገኝ ድል አይኖርም፡፡ ጉዞ ወደ 4 ኪሎ

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *