የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር መፈፀሙን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር አስታወቀ።
Read Time:28 Second
በጦርነት ሳቢያ ለተጎዱ አካባቢዎች የሚውል የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት ከዓለም ባንክ ጋር መፈፀሙን የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በጦርነት ለተጎዱ ክልሎች ማቋቋሚያና ፈጣን ምላሽ ለመስጠት ይውላል የተባለው ይኸው የ300 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስምምነት በዓለም ባንክ የኢትዮጵያ፣ የሱዳን፣ የደቡብ ሱዳንና የኤርትራ ካንትሪ ዳይሬክተር ኦስማን ዲዮን እና በገንዘብ ሚኒስትር አህመድ ሽዴ ተፈርሟል።
ፕሮጀክቱ በአማራ፣ አፋር፣ ትግራይ፣ ኦሮሚያ እና ቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች የሚተገበር ሲሆን በጦርነት የተፈናቀሉ ማሕበረሰቦችን ለማቋቋም፣ መሰረታዊ አገልግሎታቸው የተናጋባቸው የሕብረተሰብ ክፍሎች ቀጥታና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት የሚስችል ነው፡፡
በተመረጡና በጦርነትና ግጭት ምክንያት በተጎዱ ክልሎች፣ ወረዳዎች በሙሉ ተግባራዊ ይደረጋልም ተብሏል።
መረጃው የኢትዮጵያ ገንዘብ ሚኒስቴር / ኢፕድ ነው።