የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከታክስ በፊት 27.5 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቷል ተባለ።
ከታክስ በፊት 27.5 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቷል
Read Time:39 Second
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ካለፈው ዓመት የ 43 በመቶ ብልጫ ያለውን ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ
ከታክስ በፊት 27.5 ቢሊየን ብር ትርፍ አግኝቷል
ባንኩ የ2014 በጀት ዓመት ጠቅላላ ጉባኤውን በተያዘው ዓመት ባስመርቀው አዲሱ ህንፃ ዛሬ የጀመረ ሲሆን ጉባኤው በነገው ዕለት ይጠናቀቃል።
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዋና ፕሬዝዳንት አቶ አቤ ሳኖ በጉባኤው መክፈቻ ላይ ባደረጉት ንግግር ባንኩ በ2014 በበጀት ዓመቱ 27.5 ቢሊየን ብር ትርፍ ያገኘ ሲሆን ይህም ከእቅዱ የ116.3 በመቶ ብልጫ እንዳለው አስታውቀዋል።
ትርፋ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ43.9 በመቶ ብልጫ አሳይታል።
የባንኩ አጠቃላይ ሀብት በበጀት ዓመቱ መጨረሻ አንድ ነጥብ ሁለት ትሪሊየን መድረሱም ተነግሯል።
በመላው ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያ ውጪ 1,824 ቅርንጫፎች ያለው ንግድ ባንክ 7.7ሚሊየን የኤቲኤም ተጠቃሚዎች እንዳሉት አቶ አቤ ሳኖ ተናግረዋል የሞባይል ባንኪንግ ተጠቃሚዎቹ አምስት ነጥብ ዘጠኝ ሚሊየን ሲደርሱ ኢንተርኔት ባንኪንግ ተጠቃሚዎች ደግሞ ከ39ሺ በላይ መሆናቸውን ገልፀዋል።