” ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመሩን በበጎ እቀበለዋለሁ ” – ኢሰመኮ
Read Time:33 Second
የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) በአፋር ክልል ሰመራ ከተማ በሚገኙት አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች የነበሩ ሰዎች ወደ ቀዬአቸው መመለስ መጀመር እንዲሁም የሰብአዊ ድጋፍ አቅርቦቱን በበጎ እንደሚቀበለው ገልጿል።
ዋና ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ኮሚሽኑ ቀደም ሲል በአፋር ክልል፣ ሰመራ ከተማ የሚገኙትን አጋቲና እና ሰመራ ካምፖች በተመለከተ ያካሄደውን ክትትል እና ያወጣውን ሪፖርት አስታውሰዋል።
ይህንኑ ተከትሎ በካምፖቹ የነበሩ ሰዎችን ወደ ቀዬአቸው የመመለሱ ተግባር መጀመር እና የባንክ አገልግሎት ማግኘትን ጨምሮ ሌሎች እየተደረጉ ያሉ ሰብአዊ ድጋፎችን ኮሚሽኑ በበጎ እንደሚመለከተው ገልፀዋል።
በሌላ በኩል ኮሚሽኑ በአማራ ክልል፣ ወሎ ይገኛሉ ያላቸውን የጃራ እና የጃሬ ካምፖች በተመለከተ ምርመራ እያካሄደ እንደሚገኝ ፤ ከአስተዳደራዊ እና የፀጥታ አካላትም እያሰባሰበ ያለውን መረጃ የሚያካትት ሪፖርት በቅርቡ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን ዶ/ር ዳንኤል ገልፀዋል።