በዩኒቨርሲቲ መምህራን ማህበራት በኩል የቀረቡ ጥያቄዎች

#የዩኒቨርሲቲ_መምህራን
• መንግሥትን የደመወዝ ጭማሪ እና የዕርከን ዕድገት እንዲያደርግ ጠይቀዋል።




• ለዩኒቨርሲቲ የአካዳሚክ እና ቴክኒካል ረዳቶች የተሰራውን አዲሱን የስራ ደረጃ ማሻሻያ JEG በተመለከተ ቅሬታ አላቸው።
• የመምህራን የቤት አበልን በተመለከተ በፍጥነት አሁን ያለው የቤት ኪራይ ዋጋ ከግምት አስገብቶ ተሻሽሎ ተግባራዊ እንዲደረገ ጠይቀዋል።
• በመንግስት የተደረገው የደረጃ ማሻሻያ ረጅም ጊዜ በዩንቨርሲቲ ያስተማሩ መምህራንን ልምድ ያላገናዘበ በመሆኑና በመምህራን መካከል በቀጣይ ፍትሀዊ የደምወዝ ልዩነት እንዲኖር ስለማያስችል የደረጃ ማሻሻየው የመምህራንን ልምድ እና ማዕረግ ያገናዘበ እንዲሆን ጠይቀዋል።
• የረዳት ፕሮፌሰር የአካዳሚክ ማዕረግ ዝቅተኛ ተፈላጊ ችሎታ የ3ኛ ዲግሪ መደረጉን በተመለከተ ያለን ቅሬታ አላቸው።
• የአካዳሚክ ቴክኒክ ረዳቶች ዝቅተኛው ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ የመጀመሪያ ዲግሪ መሆኑ ላይ አቤቱታ አላቸው።
• የቺፍ ቴክኒካል ረዳት II የትምህርት ደረጃን ፒ ኤችዲ ዲግሪ መሆኑም ላይ አቤቱታ አላቸው።
ጥያቄዎቻችን መልስ ይሰጣቸው እያሉ የሚገኙት መምህራኑ ይህ ካልሆነ እስከ ስራ የማቆም አድማ መምታት ድረስ ዕርምጃ እንደሚወስዱ ገልፀዋል።
ትምህርት ሚኒስቴር ለሪፖርተር ፥ ” ጥያቄ እንዳለ እናውቃለን። ነገር ግን አሁን ላይ ለውጦች ለማምጣት ጥናት እየተካሄደ ነው። ከዚህ ባለፈ የምንለው ነገር የለም። የደመወዝ ጉዳይ የትምህርት ሚኒስቴር ብቻ አይደለም የሲቪል ሰርቪስ ጉዳይም ነው “