እንዳልካቸው ዘነበ እህት ስለ ወንድሞቿ እስር | የስለት ልጇ እንዳልክ በመታሰሩ እናታችን ክፉኛ ህይወቷ ተመሰቃቅሏል
እንዳልካቸው ዘነበ
*************
እንዳልካቸው ዘነበ
ተወልዶ ካደገበት ከአርባ ምንጭ ባህር ዳር ድረስ ሄዶ በአማርኛ ቋንቋና ስነ ፅሁፍ ትምህርት ክፍል የመጀመሪያ ዲግሪውን ጨርሶል ፡፡ ለሶስት ዓመት ያህል ሳይማር ወደ ወደ አስተማረው ማህበረሰብ ተመልሶ በመሄድ መብራትና ውሀ በሌለበት ገጠራማ አካባቢ ለሁለት አመት አስተምሯል።
በቆየበት ሁለት አመት ውስጥ ያጠራቀመውን ጥቂት ገንዘብ ይዞ አዲስ አበባ መጣ ።አዲስ አበባ እንዳሰባት ኣላገኛትም ። ዘመድ ጓደኛ ወዳጅ አልነበረውም ለሶስት ወራት ያህል ስራ በመፍለግ ተንከራተተ ጀሞ አካባቢ አንድ ትምህርት ቤተ ተቀጠረ ወዲያው የሰራተኛ ቅነሳ ብለው አሰናበቱት ተመልሶ ወደ አርባምንጭ መሄድ አልፈለገም።
JTV Ethiopia የነበረበት ህንፃ ስር አሁን የሚሰራበት መስሪያ ቤት ህንፃ ስር የያዘውን ገንዘብ ስለጨረሰ እዚያው የሊስትሮ ዕቃውን ገዝቶ ስራ ጀመረ ። ምን አልባት የአለቃውን ጫማ ከአንድም 8ግዜ የመጥረግ አጋጣሚ ነበረው። እዚያው ማስታወቂያ አወጣከ 7ሺህ ተወዳዳሪዎች ከሚፈለጉትም 6 ሰዎች በሁለተኝነት አለፈ።
በአንድ ሺህ ስምት መቶ ብር ደሞዝ ተቀጠረ ትዝብት የተሰኘ የፕሮግራም ዲዛይን ቀረፀ።
ፕሮግራሙ እንደ ነገ ሊተላለፍ እንደ ዛሬ ያጠፋውን ስልኩን ከፈተ ሞቷል ብላ ለደመደመችው እናቱ ደወለ እሁድ 10በጄ ቲቪ ጠብቂኝ አለ:: ዛሬ በሺዎች የሚቆጠሩ ገንዘቦችን ያገኛል:: የራሱ event organize office አለው::
በ Arts Tv “ትዝብት” ፕሮግራም አዘጋጅ የሆነው አቶ እንዳልካቸው ዘነበ እና ወንድሞቹ አቶ ተከተል ዘነበ እና ቴዎድሮስ ዘነበ ” በሃሰተኛ መረጃ ማሰረጨትና ፣ የጥላቻ ንግግር በማህበራዊ ድህረ —ገፅ ማሰረጫት ” ወንጀል ተጠርጥረው እንዲያዙ ፍርድ ቤት ወሰነ ።
ታሪኩ ዘውዱ
እንዳልካቸው ዘነበ በተገኘበት በፖሊስ እንዲያዝ በጋሞ ዞን ምዕራብ አባያ ፍርድ ቤት ትእዛዝ ሰጠ።
ጉዳዩ በቅርቡ በጋሞ ዞን የብርብር ከተማ ከንቲባ ሆና ከተሾመችዉ እና ከሌሎች የም/ዓባያና ብርብር ከተማ ካድሬዎች ጋር የተያያዘ እንደሆነ እየተነገረ ነዉ።
በብርብር ከተማ እና በም/ዓባያ ወረዳ በካድሬዎች አጭር ትዕዛዝ ዜጎች እየታሰሩ እና በፓሊስ እየተደበደቡ ነዉ። በቅርቡ የብርብር ከተማ ነዋሪ በሆነዉ አስማመዉ ደሳለኝ ላይ በካድሬ ትዕዛዝ የተፈፀመዉ ከባድ ድብደባ ምሳሌ ነዉ።