ከምስራቃዊ የአማራ ክልል የተነሱ ተሳፋሪዎች አዲስ አበባ ለመግባት እንደሚንገላቱ ገለፁ

0
0 0
Read Time:54 Second

መንግሥት በፀጥታ ሥጋት ምክኒያት የሚደረግ ፍተሻ ነው ብሏል

ከሰሜንና ደቡብ ወሎ እንዲሁም ከዋግ ኽምራ ዞኖች ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ ተሳፋሪዎች ኦሮምያ ክልል ከተሞች ሲደርሱ “የአዲስ አበባ መታወቂያ አልያዛችሁም” በሚል ምክንያት ወደ መጡበት እንዲመለሱ መደረጋቸውን ለአሜሪካ ድምፅ ገለፁ፡፡

ተሳፋሪዎቹ “የምንኖርበት እየታወቀ የማንኖርበትን ከተማ መታወቂያ እንድናመጣ መጠየቁ አግባብነት የለውም” ይላሉ፡፡

የአማራ ክልል መንግሥት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ የተፈጠረው መጉላላት ከፀጥታ ጉዳይ ጋር የተያያዘ ቢሆንም አፈጻጸሙ ብዙሃኑን ተሳፋሪ ለእንግልትና ለአላስፈላጊ ወጭ የዳረገ እንደሆነ ጠቁሟል፡፡

ከኦሮምያ ክልል እስካሁን በጉዳዩ ላይ የተሰጠ ማብራሪያ የለም፡፡ የአሜሪካ ድምፅ ራዲዮም አስተያየት ለማካተት ሞክሮ ለጊዜው አልተሳካለትም፡፡

በጉዳዩ ላይ ምላሽ የሠጡት የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዲኤታ ሠላማዊት ካሣ ሁኔታው ከጥብቅ የፀጥታ ቁጥጥር ጋር የተያያዘ መሆኑን ተናግረዋል።

መታወቂያ ለመሥራት የሚያስፈልጉትን ጨምሮ የተለያዩ ሰነዶች በህወሓት ተይዘው ከነበሩ የአማራ ክልል አካባቢዎች መወሰዳቸው ደግሞ ለጥብቅ ቁጥጥሩ መነሻ መሆኑን ጠቅሰዋል።

አፈጻጸሙን በተመለከተ ግን ማሻሻያዎች መደረግ እንዳለባቸውና የደህንነት እና የፀጥታ መዋቅሩን ማጥራት እንደሚያስፈልግም ዛሬ የወጣውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የደህንነት ምክር ቤት መግለጫ በመጥቀስ አብራርተዋል።

በሚኒስትር ዴታዋ ማብራሪያ ስማቸው የተጠቀሰው ህወሓት እና ራሱን የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ብሎ የሚጠራው ሸኔ እስካሁን በጉዳዩ ላይ የሠጡት አስተያየትም ሆነ ያወጡት መግለጫ የለም። በኛ በኩል ምላሽ ለማግኘት ሙከራ እያደረግን ነው።

source: https://amharic.voanews.com/

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *