መልካም ልደት!

0 0
Read Time:1 Minute, 43 Second

ጎንደር ላይ የነገሡት 19 ነገሥታት አጼ #ቴዎድሮስን ጨምሮ የዘር ሐረጋቸው ከመንዝ ነው።

ክፍል_ሁለት

አፄ ልብነ ድንግል ሞጆ ላይ በግራኝ አህመድ ከተሸነፈ በኋላ፥ “ያ ይነብር” – “ያዕቆብ ይኖራል” በተባለው ትንቢት መሰረት ከአራቱ ልጆች #ያዕቆብን ለሃገር ባለውለታው እና ቃሉን ለሚጠብቀው ለመንዝ ሕዝብ ከነ ልብሰ መንግሥቱ #ገሜ ጊወርጊስ ዙፋኑን አደራ ሰጥተውት ሄዱ።

ዓፄ ልብነ ድንግል የዓፄ ናዖድ ልጅ የዓፄ በእደ ማርያም የልጅ ልጅ ናቸው። ዓፄ ዘርዓ ያዕቆብም ቅድመ አያታቸው ናቸው ።

አቤቶ ያዕቆብ መንዝ ውስጥ አጋንቻ አካባቢ ገወል በተባለ ቦታ አራት ልጆች ይወልዳል፤ እነርሱም፥

1ኛ. ገራም ፋሲል
2ኛ. ስገወ ቃል
3ኛ. ተዝካረ ቃል
4ኛ. ወለተ ማርያም ናቸው።

ገራም ፋሲል ከመንዝ ተነስቶ ጎንደር አጎቱ ልጅ አፄ #ሰርጸ_ድንግል ጋር በመሄድ ከጎጃሟ የባላባት ልጅ ከሆነችው ከሐመልማል አፄ #ሱስንዮስን ይወልዳል።

ከመንዝ የተወለደው አጼ #ሱስንዮስ መንዜዋን ሥልጣን ሞገሣን አግብቶ አፄ #ፋሲልን ወልዷል።

ጎንደር ላይ የነገሡት 19 ነገሥታት አጼ ቴዎድሮስን ጨምሮ የዘር ሐረጋቸው ከመንዝ ነው።
የጎጃም ባላባቶችም የትውልድ ሐረጋቸው ከመንዟ ከወለተ ማርያም ይመዘዛል።

ለዚያ ነው በኢንሳይክሎፒዲያ ኢትዮፒካ “…Yacob as the ancestor of two branches of Solomonic Dynasty of GONDERIAN dynasty … and of the Shewan Dynasty as the great grand father… Negasi krstos” ያለው (page 752)።

የመንዙ አቤቶ ያዕቆብ፥ የታላላቆቹ የጎንደርና የሸዋ ነገሥታት አባት ነው ያለው።

እንዲሁም ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን እንዲህ ይላል፤ “Menz was the birth place of aline of ruler which culminated in the present imperial family of Ethiopia.”

መንዝ የኢትዮጵያ ነገሥታት የትውልድ ቦታ ነች ይላል። (Wax and GOLD, Donald Levin page 30)

የሸዋ ነገስታት እስከ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ድረስ የዘር ግንዳቸው ከመንዝ ይመዘዛል።

እነሱም

➣ አቤቶ ያዕቆብ
➣ አቤቶ ሥግወ ቃል
➣ አቤቶ ወረደ ቃል
➣ አቤቶ ልብሰ ቃል
➣ አቤቶ ነጋሢ ክርስቶስ
➣ መርእድ ስብስቴ
➣ መርእድ አብየ
➣ መርእድ አምሃየስ
➣ መርእድ አስፋ ወሰን
➣ ራስ ወሰን ሰገድ
➣ ንጉሥ ሣሕለ ሥላሴ
➣ ንጉሥ ኃይለ መለኮት
➣ አፄ ምኒልክ
➣ አፄ ኃይለ ሥላሴ

ሁሉም የሸዋም፣ የጎንደርም፣ የጎጃምም፣ የትግራይም መሳፍንትና ነገሥታት የዘር ሐረጋቸውን ከመንዝ ይቆጥራሉ።

ለዚህም ነው የታሪክ ፀሐፊው ቀኛዝማች ታደሰ ዘወልዴ “የመንዝና የመረሃቤቴ አውራጃዎች የኢትዮጵያ ነገሥታት ቤተ መቅደስ ናቸው… ከእነርሱ የተወለደ ምነኛ ክብር ይሰማው ይሆን” ያሉት።

ፕሮፌሰር ሌቪን “… መንዝ ታላቅ ታሪክ ያለው ሲሆን አብዛኞቹ መጻሕፍቶች ታሪኩን አይጠቅሱትም” ይላል። ቀኛዝማች ታደሰ ዘወልዴም “መንዝ ከታሪክ ጸሐፊዎች የሚዘለልና ቸል የተባለ ነው” ይላሉ።
ክፍል ሦስት ይቀጥላል……..
Tsegaw Mamo ጥናታዊ ፅሁፍ የተወሰደ
ለበለጠ ወዳጅነት

Source: https://www.facebook.com/profile.php?id=100067963113614

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *