ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በጋዜጠኛና ደራሲ ፍቅሩ ኪዳኔ የፀሎትና የሽኝት መርኃ ግብር ላይ በመገኘት የአበባ ጉንጉን አኑረዋል።

0
1 0
Read Time:1 Minute, 8 Second

የጋዜጠኛ እና ደራሲ ፍቅሩ ኪዳኔ የመታሰቢያ መርኃ ግብር ዛሬ በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ተካሄደ።

ጋዜጠኛና ደራሲ ፍቅሩ በሕክምና ሲረዱ ቆይተው ከቀናት በፊት በ88 ዓመታቸው ሕይወታቸው ማለፉ ይታወቃል።

በዛሬው እለትም በመናገሻ ገነተ ጽጌ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ-ክርስቲያን ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅን ጨምሮ የመንግስት ባለስልጣናት፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው፣ አድናቂዎቻቸውና ሌሎች ጥሪ የተደረገለቸው እንግዶች በተገኙበት የአበባ ጉንጉን የማስቀመጥና የማስታወሻ መርኃ ግብር እንደተካሄደ ኢዜአ ቤተሰቦቻቸውን ጠቅሶ ያወጣው መረጃ ያመለክታል።

በ1927 ዓ.ም በአዲስ አበባ የተወለዱት ጋዜጠኛና ደራሲ ፍቅሩ ኪዳኔ በኢትዮጵያ ሬዲዮና የተለያዩ የአገር ውስጥ የሕትመት ውጤቶች ስለ አገር ውስጥ ስፖርት ገና በለጋ እድሜያቸው መዘገብ የጀመሩ ሲሆን በዚህም በ1943 ዓ.ም በሱዳን እና ኢትዮጵያ መካከል የተደረገውን ጨዋታ በቀጥታ በሬዲዮ ማስተላለፍ የቻሉ የመጀመሪያው የስፖርት ጋዜጠኛ ናቸው።

ጋዜጠኛና ደራሲ ፍቅሩ የኢትዮጵያ የስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር በ1961 ዓ.ም ሲመሰረት የመጀመሪያው ፕሬዝደንት የነበሩ ሲሆን በብስክሌት ፌዴሬሽን፣ ቴኒስ ፌዴሬሽን እና በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ ኮሚቴ በዋና ፀሐፊነት፣ በኢትዮጵያ የእግር ኳስ ፌዴሬሽን የሕዝብ ግንኙነት በመሆን አገራቸውን አገልግለዋል፡፡

በዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እና የአፍሪካ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ውስጥም በአመራርነት ፣ የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የቀድሞ ፕሬዝደንት የነበሩት የኢሳ ሃያቱ አማካሪም ጭምር የነበሩ ናቸው፡፡

ከ1969 ዓ.ም ጀምሮ ኑሯቸውን በፈረንሳይ መዲና ፓሪስ ያደረጉት ፍቅሩ በሀገሪቷ ለሚገኘው ዕለታዊ የስፖርት ጋዜጣ ለኪፕ እና ሳምንታዊ የእግር ኳስ መጽሔት ፉትቦል ፍራንስ፣ ዶቼቬሌ (የጀርመን ድምፅ) እና ሌሎች የአለም አቀፍ ታዋቂ መገናኛ ብዙሃን መስራት ከመቻላቸው በተጨማሪ “የፒያሳ ልጅ” እና “የስፖርት ጨዋነት ምንጮች” የተሰኙ መጻሕፍት መጻፍ ችለዋል፡፡

ጋዜጠኛና ደራሲ ፍቅሩ ኪዳኔ የአንድ ልጅ አባት ሲሆኑ ሁለት የልጅ ልጆችንም አይተዋል።

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *