ሂሩት!! “አባቱዋ ማነው?”
ሒሩት አባቷ ማነው? የ1957ዓ.ም. የመጀመሪያው የኢትዮጵያ የፊልም ታሪክ ለንደን ለሚገኙት ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች በክብር. በሲኒማ ቤት የፊታችን ቅዳሜ ይቀርባል ።
“ሂሩት አባቷ ማነው?” የተሰኘው ፊልም በኢላላ ኢብሳ ተጽፎ በግሪካዊ ላምብሮስ ዮካሪስ ዳይሬክት የተደረገው ባለነጭና ጥቁር ቀለም ፊልም በኢትዮጵያ ፊልም ታሪክ የመጀመርያው ሲሆን መርቀው የከፈቱትም ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ንጉሰነገስ ነበሩ: : ይህም የፊልም ጽሑፍ በመጻፍ እንዲሰራ ያደረጉት ኢላላ ኢብሳ ናቸዉ፡፡
ይህ ፊልም በኢላላ ኢብሳ ብቻ የሚሆን ባለመሆኑ ጉዳዩን በጥብቅ እየተከታተሉ ወደ ፊልምነት እንዲቀየር ትልቁን ሥራ ያከናወኑት በትውልድ ግሪካዊ የሆኑት የፊልሙ አዘጋጅ ላምብሮስ ዮካሪስ ናቸው፡፡
ፊልሙን ደግሞ ያቀረበው “ያገር ፊልምና ማስታወቂያ ድርጅት” ነበር፡፡ የፊልሙ ታሪክ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ አድርጎ ጠንካራ ሐሳብ ይዞ የተሰራ በመሆኑ እጅግ በጣም መሳጭና አጏጊ ነው: :
እነሆ ከ 57 ዓመታት በኋላ ሂሩተ አባቷ ማነው? ፊልም ዳግም ለንደን ለሚገኙት ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የፊታችን ቅዳሜ ኦክቶበር 15 /10/22 ይቀርባል ይህ በአለም ቅርስነት ሊመዘገብ የታሰበ የመጀመሪያው ፊልም እንዳያመልጠወ በቦታው በመገኜት ትኬቱን ይግዙ አድራሻ
(address) Rich Rich Mix cinema 35-47 Bethnal Grn Rd, London E1 6LA