በሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲ ሚዲያ የተዘጋጀ የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል በለንደን የፊታችን ዐርብ ለ፫ ቀን ፫ የተለያዪ ፊልሞችን ሊያቀርብ ነው።

0
1 0
Read Time:1 Minute, 24 Second

ሐበሻቪው ቴክኖሎጂና መልቲሚዲያ “ሂሩት አባታ ማነው?” የተሰኘውን ጥንታዊ ኢትዮጵያዊ ፊልም ለመጀመሪያ ጊዜ ከሀገር ውጪ በዮናይትድ ኪንግደም (ሎንደን) ከተማ እጅግ ድንቅና ዘመናዊ በሆኑ ሲኒማ ቤቶች በሶስተኛው አመታዊ የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ለማቅረብ ከአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ኢንተርፕራይዝ ጋር የውል ስምምነት ፊርማ ፕሮግራም አዘጋጅቷል፡፡


ይህ የፊርማ ስነ-ስርአት ሰሜን ሳሎን ተብሎ በሚጠራው ሸራተን አዲስ ሆቴል አዳራሽ ውስጥ ሐሙስ መስከረም 26 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡30 አስከ 7፡30 የሚከናወን ሲሆን የጋዜጠኞች ጥያቄና መልስ ፕሮግራም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 3፡30 የሚደረግ ይሆናል፡፡


በዚህ ባሳላፍነው ዓመት ይህንን “ሂሩት አባቷ ማነው?” የተሰኘውና በ1965 እ.አ.አ የተቀረፀ ድንቅ ልብወለድ ፊልም እንደገና ተቀነባብሮና ከ57 ዓመታት በኋላ ዲጂታላይዝ ተደርጎ በቅርቡ በሸራተን አዲስ ሆቴል ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ታዋቂ ግለሰቦችና ባለሙያዎች በተገኙበት ለእይታ እንዲቀርብ በማድረግ በእኛ፣ በአዲስ አበባ ሲኒማ ቤቶች አስተዳደር ኢንተርፕራይዝ፣ በአዲስ አበባ ባህልና ቱሪዝም ቢሮና በአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት መካከል ቀናና አስተዋይነት የተሞላበት መልካም የትብብር ስምምነት ለማድረግ ተችሏል፡ ፡ “ሂሩት አባቷ ማነው?” ፊልም የሀገር ሀብት እንደመሆኑ እኛ ሐበሻቪው ከሀገር ውጪ ለመጀመሪያ ጊዜ በሎንዶን (ዩናይትድ ኪንግደም) አመታዊ የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ለማቅረብ በመቻላችን ከፍተኛ ክብር ይሰማናል ፡፡


ይህንን ታሪካዊ ፊልም ወደ ሎንዶን ለመውሰድ ስንዘጋጅ የፊልሙን ታሪካዊነት በመገንዘብ አብረው የሚጓዙ የመንግስት ተወካዮች እንዲሁም ከኢትዮጵያ የፊልም ኢንዱስትሪ ተወካዮች በዚሁ በሎንዶን የኢትዮጵያ ፊልም ፌስቲቫል ላይ ገኝተው የኢትዮጵያን የፊልም ታሪክ ደረጃና እድገትን ለማስተዋወቅ መልካም አጋጣሚ እንደሚሆን እናምናለን። ይህ የፊልም ፌስቲቫል ከፍተኛ የህዝብና የመንግስት መ/ቤቶችን ድጋፍ ያገኘ ሲሆን በተለይ የኢትዮጵያ ልማት ባንክና በሎንዶን የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ያደረጉት አስተዋጸኦ ሳይጠቀስ የሚቀር አይሆንም፡፡
በሎንዶን የሚደረገው የሐበሻቪው የኢትዮጵያዊያን የፊልም ሳምንት ላይ የተለያዩ አዲስና ቀደምት የሀገር ውስጥ ፊልሞችን ከሀገር ውጪ ላለፉት ሶስት አመታት ያቀረብን ሲሆን በተለይ ባለፈው ዓመት የተዘጋጀነው የፊልም ፌስቲቫል ልዩ አድናቆትን ያገኘና እጅግ በጣም ብዙ ሕዝብ የታዘበው ነበር፡፡

Happy
Happy
100 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *