“የአለም ፀሐይ ሁሉ ጠልቃ ትወጣለች፣የ’ኔ ፀሐይ ብቻ ምነው ጠልቃ ቀረች።”
ይኼንን ያሉት ሚስታቸውን በሞት የተነጠቁት ሌ/ጄኔራል ዐብይ አበበ ናቸው።ከሥር ያለው ፎቶ ውብ ወጣት ልዕልት ፀሐይ ኃይለሥላሴ ናቸውቀዳማዊ አፄ ኃይለሥላሴ ከ እቴጌ መነን አስፋው ከሚወልዷቸው ልጆች አንዷ ናቸው
ልዕልቷ በጣሊያ ዳግም ወረራ ወቅት ከአባታቸው ጋር ወደ እንግሊዝ ስደት በኼዱበት ጊዜ ለንደን ከተማ ውስጥ በሚገኘው ‹‹Great Ormond Street Hospital for Sick Children›› ተቋም ሕክምና አጥንተው ተመልሰው ኢትዮጵያን አገልግለዋል።
ከስደት መልስ ሜ/ጄኔራል ዐብይ አበበን አግብተው ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህመም ህይወታቸው አለፈ። ልዕልቷ በኢትዮጵያ የራዲዮ ፕሮግራም ላይ በእንግሊዝኛ ቋንቋ መልዕክት በማስተላለፍ የመጀመሪያ እንደሆኑ ይነገራል። ከሞታቸው ማግስት ጃንሆይ “ልዕልት ፀሐይ መታሰቢያ ሆስፒታል” በሚል በስማቸው መታሰቢያ ይሆን ዘንድ ሆስፒታል አሰርተው ነበር። ደርግ ሲገባ ሥያሜውን “ጦር ኃይሎች ሆስፒታል” ብሎ ቀየረው።
ሜ/ጄኔራል ዐብይ አበበ የቀዳማዊ ኃይለሥላሴ ገነት ጦር ትምህርት ቤት ምሩቅ ነበሩ። በተለያዩ የኃላፊነት ቦታዎች አገልግለዋል። ከታህሳሱ ግርግር በኋላ በ1955 ዓ/ም ” አውቀን እንታረም” የሚል ድንቅ መፅሐፍ ለሕትመት አብቅተወሸል። መፅሐፉን ማንበብ ያተርፋል። በተልይ ለፖለቲከኞች ጥሩ ትምህርት ይሰጣል።
ሜ/ጄኔራል ዐብይ አበበ ህዳር 14 ቀን 1967 ዓ/ም በደርጎች ሚዛናዊነት የጎደለው የፖለቲካ ውሳኔ በግፍ ከተገደሉት 60 ሲቪል እና የጦር ባለስልጣናት መካከል ናቸው።