የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካፒታሉን ወደ 300 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ አቀረበ።

0
0 0
Read Time:57 Second

#EthiopianAirlines

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ካፒታሉን ወደ 300 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ማቅረቡን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

አየር መንገዱ አሁን ያለውን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ለማሳደግ ያቀረበው ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ ሲሆን ቦርዱ ተወያይቶ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ ” አሁን ያለንን 100 ቢሊዮን ብር ካፒታል ማሳደግ የፈለግንበት ምክንያት፣ ወሮታችን ከፍ እያለ በመምጣቱ ሲሆን፣ በቅርቡ ያፀድቁልናል ብለን እናስባለን ” ሲሉ ተናግረዋል።

የአየር መንገዱ የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄ ለኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ቦርድ ቀርቦ እየታየ እንደሚገኝ ጋዜጣው ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ግሩፕ ማረጋገጡን አመልክቷል።

አቶ መስፍን የካፒታል ማሻሻያ ጥያቄውን ምክንያት በተመለከተ፤ ” የምናንቀሳቅሰው ገንዘብ እያደገ በመምጣቱና የካፒታል ማሻሻያ ከሌለ ትክክለኛ የፋይናንስ አያያዝ ለመፍጠር ስለሚያስቸግር ” ነው ብለዋል።

” በተጨማሪም አሁንም አዳዲስ አውሮፕላኖች እያስመጣን ነው፡፡ በምናስመጣበት ወቅት የዕዳና ካፒታል ምጣኔ መመጣጠን አለበት፡፡ አብዛኛውን ጊዜ የአውሮፕላን የሚገዛው በብድር ስለሆነ አበዳሪዎቹ ጋ ተቀባይነት እንዲያገኝ ከፍ ያለ የሀብት መጠን መድረስ አለበት። ብለዋል፡፡

የዕዳ እና ካፒታል ምጣኔ ተቋሙ ካለው ካፒታል አንፃር ሲታይ ምክንያታዊ ካልሆነ አበዳሪዎቹ ለማመን እንደሚቸገሩ አቶ መስፍን መግለፃቸውን ሪፖርተር ጋዜጣ አስነብቧል።

Source: Ethiopian Reporter

ለፈጣን መረጃዎች፦
ፌስቡክ https: https://www.facebook.com/TheEthiopianTribune
ቴሌግራም https://t.me/TheEthiopianTribune
ዩቲዩብ https://youtube.com/c/TheEthiopianTribune
ቲዊተር https://twitter.com/EthTribune
አብራችሁን ስለሆናችሁ እናመሰግናለን!

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *