1 0
Read Time:1 Minute, 23 Second

የጀዌሪያ ሽኝት
(ሙክታሮቪች ኦስማኖቫ)

ዛሬ ጂጂጋ ጥልቅ ሀዘን ውስጥ ነች። የወ/ሮ ጀዌሪያ በፀጥታ ሀይል ነፍሷ መቀጠፉ ብዙዎችን ለቁጭትና ለከፍተኛ ሀዘን ዳርጓል። የተገደለችበት ሁኔታ እጅግ አሳዛኝ ነው። ከቃል በላይ ነው፤ ልብ ይሰብራል።

ጀዌሪያን ማጣት ቀላል አይደለም። ለምን?

የተማረች ነች። ህዝብና ሀገሯን የምትወድ ነች። መምህርት ነች። ህዝብ ለማገልገል ደከመኝ ሰለቸኝ የማትል ብርቱ ሴት ነች። የህዝብ ተወካይ ነች። የብልፅግና ማዕከላዊ ኮሚቴ ነች። ሴቶች ለመብታቸው እንዲቆሙ፣ ወደ ህዝባዊ አገልግሎት ፊታቸውን እንዲያዞሩ በምሳሌነት ከፊት ቀድማ ያሳየች የተገባር ሰው ነች። ነበረች ለማለት ከበደኝ።

ያሳዝናል።

የጀመረቻቸው ሁሉ ነገሮች መንገድ ላይ ቀሩ።

ኢና ሊላሂ ወ ኢና ኢሌሂ ራጂዑን

አዋሬ ተወልዳ፣ ሀረር ተምራ ጂጂጋ ዩኒቨርሲቲ ድግሪና ማስተርስ ይዛ፣ አሜሪካን ጨምሮ በበርካታ ሀገራት የተለያዩ ስልጠናዎችን ወስዳለች።

ለህዝብ አገልግሎት እራሷን ለማብቃት ከልጅነቷ ጀምሮ ለፍታለች። እሷ ያሰበችው ሳይሆን ቀረ። ወንጀል ተሰራባታ። እሷ ላይ የተፈፀመው ግድያ ለክልሉ ህዝብ እና ለሀገራችን ከፍተኛ ጉዳት ነው። ያሳዝናል

ዛሬ ጂጂጋ በጥልቅ ሀዘን ውስጥ ናት ያልኩት ጀዌሪያ የሁሉ ሰው ልብ ውስጥ የገባች እጅግ መልካም ባህሪን የታደለች በመሆኗ ነው። ከሁሉ ሰው ጋ ተግባቢ ነች። ስብዕናዋ ለሳቅ ለጫወታ ቅርብ ነበረ። አዛኝ ነበረች። ሰው ሲቸገር ያላትን የምታካፍል ነበረች። የበጎ አድራጎት ድርጅት መስርታ ለደሃ የቆመች ቁምነገረኛም ነበረች። ህልሟ ሩቅ ነበረ። ባጭሩ ቀረች። አላህ የፈቀደው ሆነ።

ክቡር አቶ ሙስጠፌ በተሰበረ ልብ የሚከተለውን መልዕክት አስተላልፏል፣

“የጀዌሪያን ከኛ መለየት ለመቀበል ይከብዳል። በጣም አዝኛለሁ። አሟሟቷ የሚያሳዝን ነው። የተፈፀመባት ግድያ አሳፋሪና ወንጀልነቱ እጅግ የሚያበሳጭ ነው። አላህ ነፍሷን በጀነት ያኑረው። ገዳይዋ የኤርፖርት የፀጥታ አካል በቁጥጥራችን ስር ነው። ህዝብ ፍትህ እየጠየቀ ነው። እኛም ለተፈፀመው አስከፊ ወንጀል ተመጣጣኝ ቅጣት እንዲጣልበት ለማረጋገጥ እንሰራለን። የግድያውን መንስኤ መርምሮ የሚያሳውቅ ኮሚቴ መስርተናል። ጊዜው ሲደርስ ለህዝብ ይፋ እናደርጋለን። ወንጀለኛው ለሰራው ወንጀል አሳማሚ ቅጣት እንዲፈረድበት በፍርድቤት እንከራከራለን። ህዝቡ የተሰማው ሀዘን ተመልክተናል። ከህዝቡ ጋር አዝነናል። መፅናናትን ለሁላችን አላህ ይስጠን”

ጀዌሪያ የጂጂጋ ዩኒቨርሲቲ የስራ ባልደረባዬ ነበረች። በጣም አዝኛለሁ

አላህ ነፍሷን በጀነት ያኑረው 🙏

Happy
Happy
0 %
Sad
Sad
0 %
Excited
Excited
0 %
Sleepy
Sleepy
0 %
Angry
Angry
0 %
Surprise
Surprise
0 %

Average Rating

5 Star
0%
4 Star
0%
3 Star
0%
2 Star
0%
1 Star
0%

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *