በኢትጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት 12 ነጥቦች

Read Time:30 Second

ዛሬ በፕሪቶሪያ ፤ በኢትጵያ መንግስት እና ህወሓት መካከል የተፈረመው የሰላም ስምምነት 12 ነጥብ የያዘ ነው።
ከዚህም ስምምነት መካከል ፦
– ህወሓት #ትጥቅ_እንዲፈታ ከስምምነት ተደርሷል።
– የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት ለማረጋገጥ እና የኢፌደሪ ሕገ-መንግሥቱን ለማስከበር የኢትዮጵያ መንግስት እና ህወሓት ተስማምተዋል።
– ኢትዮጵያ #አንድ ብሔራዊ መከላከያ ኃይል ብቻ አላት በሚለው ስምምነት ተፈርሟል።

– በመሬት ላይ ያለውን የፀጥታ ሁኔታ ከግምት ውስጥ በማስገባት የህወሓት ተዋጊዎችን ትጥቅት ለማስፈታት፣ ተዋጊዎችን ከሠራዊቱ እንዲወጡ ለማድረግ እና መልሶ ወደ ማኅበረሰቡ ለመቀላቀል ስምምበት ላይ ተደርሷል።
– #የጥይት_ድምጽ_በዘላቂነት_እንዳይሰማ በመስማማት፣ ጦርነቱ እንዲያበቃ የሚያስችል ዘላቂ የግጭት ማስወገድ ስምምነት ተፈርሟል።

– የጥላቻ ፕሮፓጋንዳ ለማቆም ስምምነት ላይ ተደርሷል።
– በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎት ወደ ነበረበት እንዲመለስ ስምምነት ተፈፅሟል።