በእነዚህ በ4ቱ አትታወቅ
1_በአልቃሻነት
ጊዜያዊ ቁስሎችህ ወዳልሆንከው ማንነት እስከወዲያኛው እንዲለውጡህ አትፍቀድላቸው፡፡ ጠንካራ ሰው ማለት የማያለቅስ ሰው ማለት አይደለም፡፡ ጠንካራ ሰው ማለት በግልጽ ለአፍታ ያህል አልቅሶ የሚነሳ እና ላመነበት ነገር እንደገና የሚፋለም ነው፡፡
2_ከችግሮች_በመሸሽ
ከችግሮችህ መሮጥ ፈጽሞ የማታሸንፈው ሩጫ ነው፡፡ ድሮ ባደረግካቸው ነገሮች ሁሉ ላትኮራ ትችላለህ፤ አሁን ግን እንደ አዲስ መጀመር ትችላለህ፡፡ ዋናው ነገር ማን ነበርክ የሚለው ሳይሆን፣ ዛሬ ማነህ የሚለው ነው፡፡ ዛሬ የምታደርገው ነገር ነገዎችህን በሙሉ ማሻሻል ይችላል፡፡ ስለዚህ አትሽሽ፤ ይልቁንም አዎንታዊ ለውጥ ሊያመጣ የሚችል ነገር አድርግ፡፡
3_ምስጋናቢስበመሆን
እጅግ ሰላማዊ በሆነ አካባቢ ውስጥ እንኳ ምስጋና ቢስ ልብ ችግር ፈልጎ አያጣም፡፡ እጅግ ችግር በበዛበት አካባቢ ውስጥ ደግሞ አመስጋኝ ልብ ሰላም ያገኛል፡፡ ዓለምን በአመስጋኝ ዐይኖች ተመልከታት፡፡ ፈጽሞ አንድ ሆና አትታይህም፡፡
4_በቁጡነት
ለዚህ ፍቱን መድኃኒቱ ጠንካራ መጠን ያለው ፍቅር፣ ሳቅና መተው ነው፡፡ ተቆጣ ግን ቶሎ ልቀቀው፡፡ ቅንጣት ታክል መጠን ያላት መርዝ በምግባችን ላይ እንድትገባ የማንፈልገውን ያህል፣ ቅንጣት ታክል ቁጣም በልባችን ውስጥ እንድትኖር አንፍቀድ፡፡
ወዳጄ..አንተስ. የምትታወቀው በየቱ ነው? ለመቀየርስ ምን አደረግክ? ሀሳብህን እንድታካፍለን ጋበዝንህ?